June 19, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/125636

የኢትዮጵያ መዳኛ መንገድ የኢትዮጵያውያን የኖረ የዴሞክራሲ እሴት እና አብሮነት መሆኑን ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ገለፁ፡፡ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ ጉዞ በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።የሰላም እና ልማት ማእከል የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ባዘጋጀው መድረክ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና የውጭ ሀገር ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እሳቤን በማንፀባረቅ እና በመተግበር የረዥም የዘመን ታሪክ ባለቤት ሀገር ናት ብለዋል።የህዝቦቿ የአብሮነት ታሪክም ዘመናትን የተሻገረ ነው ብለዋል ፕሮፌስር ኤፍሬም።ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር መውጣት የምትችልበት አንዱ መንገድ ኢትዮጵያውያን የኖረ የሰላም እና አብሮነት እሴትትን መተግበር ሲቻል ነው ብለዋል።

በህዝቦች ግንኙነት ሁለት አይነት መቀራረብ አለው ያሉት ፕሮፌሰሩ እነሱም የልብ እና የአእምሮ መሆናቸውን ገልፀዋል።ለእኛ የሚሆነው መቀራረብ የልብ ነው ይህም መቀራረብ የፍቅር፣ የይቅርታ እና መዋወደድ ነው ብለዋል።የኢትዮጵያ ፓለቲከኞች አእምሮ በስልጣን እና ገንዘብ ፍቅር ተሞልቷል የሚል ወቀሳ የስነዘሩት የታሪክ ተመራማሪው ከእዚህ አጥፊ ሁኔታዎች እንዲወጡም ጠይቀዋል ።

Source – ኤፍ ቢ ሲ