23 Jun 201923 Jun 2019
በትናንትናው ዕለት የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ግድያዎችን በተመለከተ ቢቢሲ አማርኛ ቀጥታ ዘገባ ይዞላችሁ ይቀርባል።
ጭምቅ ሃሳብ
- በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት
- ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ተገድለዋል
- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን መገደላቸው ተረጋገጠ
- የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ከመፈንቅለ መንግሥቱ ጀርባ መሆናቸው ተገልጿል
- ባህርዳር ውስጥ ትናንት ምን ተከሰተ?
- አቶ ላቀ አያሌው የአማራ ክልል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆነው ተሹመዋል
- የስራ ኃላፊነታቸውን “ከባድና የሚያስጨንቅ… ነው” ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ናቸው?
- አራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገድለዋል
- የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ መጎዳታቸው እየተነገረ ነው
ቀጥታ ዘገባ
ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የአማራ ክልል ገለፀ
በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል የተደረገውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ግድያ ጀርባ አሉ ተብለው የተጠረጠሩት ብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የክልሉ የሰላም ግንባታና ህዝብ ደህንነት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በትናንትናው ዕለት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ብርጋዲየር ጄኔራሉ በልዩ ኃይሎች ታጅበው እንደመጡና በመጀመሪያም አጃቢዎቻቸው ላይ ተኩስ እንደተከፈተ ከዚያም አመራሮቹ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሶስቱ እንደተመቱ አቶ ገደቤ ይናገራሉ።
“ጥቃቱ በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው” ያሉት አቶ ገደቤ የፀጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮና የአዴፓ ፅህፈት ቤትም ላይ ጥቃት እንደደረሰ ገልፀዋል።
“ጥቃቱ ያልተጠበቀ ነው” የሚሉት አቶ ገደቤ በወቅቱም የክልሉ ፀጥታ ኃይል አካባቢውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ጥረት ብርጋዲየር ጄኔራሉ እንዳመለጡ ገልፀው ፤ የርዕሰ መስተዳድሩ አጃቢዎች የተገደሉ ሲሆን እስካሁን ባለው ሁኔታ የሟቾች ቁጥር እንደማይታወቅ ገልፀዋል። በባህርዳር ሁኔታዎች ቢረጋጉም የርዕሰ መስተዳድሩን ሞት ተከትሎ ከተማዋ በድንጋጤ መዋጧን አቶ ገደቤ ተናግረዋል።
“ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ህዝብ ሌት ተቀን የሚሰራ ሰው ነበር፤ እንዲህ ባለ ሁኔታ መሰዋቱ በጣም አስደንጋጭና አሳዛኝ ነው” በማለት አቶ ገደቤ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ሰኔ 16 እና ዕሁድ ሰኔ 17 ምን ተከሰተ?
አዲስ አበባ
ቅዳሜ ሰኔ 16/2011 ዓ.ም
• ምሽት ሁለት ሰዓት ከመሆኑ በፊት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹሙ ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉን የሚያመለክቱ መረጃዎች መውጣት ጀመሩ።
• በከተማዋ ውስጥም የተኩስ ድምጽ መሰማቱን ነዋሪዎች ሲገልጹ፤ የአሜሪካ ኤምባሲም ለሰራተኞቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጠ።
• በአዲስ አበባ መግቢያና መውጫዎች እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ የጸጥታ ኃይሎች ከሌላው ጊዜ በተለየ በስፋት ተሰማርተው ቁጥጥር ማድረግ ጀመሩ።
• በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ሊካሄዱ የነበሩ የተለያዩ ሕዝብን አሳታፊ ዝግጅቶች እንደተሰረዙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳወቀ።
• ከዕኩለ ሌሊት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በወታደራዊ የደንብ ልብስ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በአማራ ክልል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መደረጉንና በጄኔራል ሰዓረ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አረጋገጡ።
ዕሁድ ሰኔ
17/2011 ዓ.ም
• ጠዋት የትግራይ ክልል መገናኛ መገናኛ ብዙሃንና ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙና ጄነራል ገዛኢ ህይወታቸው ማለፉን አመልክቶ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰማውን ሃዘን ገለጸ።
• የአማራ ክልል መንግሥትም በተፈጸመው ጥቃት ርዕሰ መስተዳድሩና አማካሪያቸው ሲገደሉ ሌሎች ባለስልጣናት መቁሰላቸው ተነገረ።
• የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት በባህር ዳርና በአዲስ አበባ በተፈጸሙ ጥቃቶች አራት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደተገደሉ ይፋ ሆነ።
• ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት በተሰጠ መግለጫም ሁለቱ ጄነራሎች የተገደሉት በኤታማዦር ሹሙ ጠባቂ እንደሆነና ገዳዩም መያዙ ተገለጸ።
• አቶ ላቀ አያሌው የተገደሉትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንን መንበር ተክተው ጊዜያዊ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር መሆናቸው ተነገረ።
• የተለያዩ ክልሎችም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውንና ግድያውን አወገዙ።

አዲስ አበባ
ቅዳሜ ሰኔ 16 ባህር ዳር ውስጥ ምን ተከሰተ?
ባህር ዳር
ቅዳሜ ሰኔ 16/2011 ዓ.ም
• ከሰዓት በኋላ በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት ለስብሰባ ተቀምጠው ነበር።
• አመሻሽ ላይ የክልሉ ጸጥታ ተቋም ውስጥ ካሉ ኃላፊዎች መካከል ናቸው የተባሉ ሰዎች ወደ ስብሰባ ስፍራ በመግባት ጥቃት ፈጸሙ።
• በጥቃቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።
• ይህንንም ተከትሎ በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ ስፍራዎች የተኩስ ልውውጦች ተደረጉ።
• ምሽት አንድ ሰዓት ሊሆን ሲል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው በክልሉ አመራሮች ላይ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መደረጉን ይፋ አደረጉ።
• በባህር ዳር ከተማና በዙሪያዋ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ክስተቱን ለመቆጣጠር መሰማራታቸው ተነገረ።
• ከባድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ጋብ ያለ ቢሆንም ምሽቱን አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማ ነበር።
• ምሽት ከአምስት ሰዓት በኋላ የክልሉ ገዢ ፓርቲ አዴፓ በብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ የተመራ ክልላዊ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መደረጉን አሳወቀ።

ባሀር ዳር፤ የጣና ሃይቅ ዳርቻ
በክልል ደረጃ መፈንቅለ መንግሥት እንደሌለ አብን ገለፀ
በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተካሂዷል የሚለውን የፌደራል መንግሥት መግለጫ ተከትሎ ብዙዎች በክልል ደረጃ እንዴት መፈንቅለ መንግሥት ይካሄዳል የሚል ጥያቄን አንስተዋል።
በዚህም ጉዳይ ላይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀ መንበር አቶ ደሳለኝ ጫኔ “መፈንቅለ መንግሥት ለማለት አንደኛ በቂ መረጃ የለም፤ በሁለተኛ ደረጃ በክልሉ የተከሰተው በከፍተኛ አመራሩ ላይ የተደረገ ጥቃት ነው እንጂ በክልል ደረጃ እንዴት መፈንቅለ መንግሥት ይባላል” በማለት ጠይቀዋል።
የአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ክስተቱን ‘በከፍተኛ አመራሩ ላይ የተደረገ ጥቃት’ እንዳሉ የገለፁት አቶ ደሳለኝ የፌደራል መንግሥት መፈንቅለ መንግሥት የሚለውን ቃል መጠቀሙ ግራ የሚያጋባ እንደሆነ ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰዓት አብን ጥቃቱን ማን እንደፈፀመውና ከኋላ ሆኖ ማን እንዳቀነባበረው መረጃ እየሰበሰቡ መሆኑን የተናገሩት አቶ ደሳለኝ፤ ለሞቱት ባለስልጣናትና ጄኔራሎች ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሃዘን በፓርቲያቸው ስም ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አወገዘ
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በትላንትናው ዕለት በአማራ ክልል የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥትና ግድያዎችን አወገዘ። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ድርጊቱ “የአማራ ክልል ህዝብ ሉዓላዊነትን የተፃረረ” ነው በሚል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አውግዘዋል።
“የተፈፀመው ግድያ በመላው የኦሮሞ ህዝብና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እንደተፈፀመ እንቆጥረዋለን” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ከአማራ ክልል መንግሥትና ህዝብ ጎን እንደሚቆሙ ተናግረው መላው የሃገሪቱ ህዝብም በኅብረት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
“መላው የሃጋሪቱ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዘቦች በዚህ ፈታኝ ወቅት በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፋለሁ። የተፈፀመው ጥቃት የተጀመረውን ትግል ወደ ኋላ የሚመልስ ሳይሆን የሚያጠናክር ነው” ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው እንቅስቃሴም ክልሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
በትናንትናው ዕለት የተደረገውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እንዲሁም የሃገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮነን ጄኔራል ገዛኢ አበራ ተገድለዋል።

“የመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ የሃገሪቱን ሥርዓት ለማፍረስ ያለመ ነው” ዶ/ር ደብረፅዮን
በትላንትናው ዕለት በአማራ ክልል የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እንዲሁም የሃገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮነን ጄኔራል ገዛኢ አበራ ተገድለዋል።
ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል። “ድርጊቱን የፈጸሙት በምርጫ ማሸነፍ እንደማይችሉ የተረዱና በጉልበት ሥልጣን ለመያዝ የሚሚፈልጉ ጸረ-ሕገ መንግሥት ኃይሎች ናቸው” ብለዋል።
የጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ግድያም ከመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ጋር በቀጥታ እንደሚገናኝ የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን “በአመፅ ስልጣንን ለመቆጣጠር የሞከሩት ኃይሎች የመከላከያ ኃይሉን የሚመሩት ሰዎች ለአላማቸው መሳካት እንቅፋት ናቸው በማለት ገድለዋቸዋል” ብለዋል።
ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙን ለመግደል በመጡበት ወቅት ጡረታ የወጡት ሜጀር ጄኔራል ገዛኢም አብረው ስለተገኙ መገደላቸውንም ገልፀዋል። “ይሄ በአንድ ወይም በሁለት ሰው ላይ የተቃጣ ሳይሆን ማንነትን መሰረት ያደረገ እንዲሁም ሥርዓትን ለማፍረስ ያለመ ነው” ብለዋል።
ይህ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራም ሆነ ግድያዎቹ የታቀደበት እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን “እንደዚህ አይነት ጥቃት ሊፈፅሙ እንደሚችሉ ሲያደርጉ ከነበሩት እንቅስቃሴዎች መረዳት ይችላል፤ በዚህም አያቆሙም። ትግል ላይ ነን፤ መጨረሻም እናሸንፋቸዋለን” በማለት ተናግረዋል።
ጄኔራል ሰዓረ ለግላቸው ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ እንዳበረከቱ የተናገሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተሰማቸውን ሃዘንም በክልሉ ሕዝብ ስም ገልፀዋል፤ ከዚሀም በተጨማሪ ከአማራ ክልል ሕዝብም ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል።
“ከአማራ ህዝብ ጋር በደስታ ጊዜው እንደነበርን በኃዘኑም ከጎኑ ነን” ብለዋል።

ስለብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ በጥቂቱ
ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተወለደው ያደጉት ወሎ ላስታውስጥ ነው። አሳምነው ወደ ትግል በመግባት የወቅቱን ኢህዴን በኋላ ብአዴን የተባለውን የአማራ ድርጅትን ከመቀላቀላቸው በፊት በደሴ ከተማ በሚገኘው የመምህራን ኮሌጅው ስጥ መምህር ሆነው አገልግለዋል።
ወታደራዊው መንግሥት በአማጺያኑ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በትውልድ አካባቢያቸው አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ነበር።
ስለብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ በጥቂቱ
ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተወለደው ያደጉት ወሎ ላስታውስጥ ነው። አሳምነው ወደ ትግል በመግባት የወቅቱን ኢህዴን በኋላ ብአዴን የተባለውን የአማራ ድርጅትን ከመቀላቀላቸው በፊት በደሴ ከተማ በሚገኘው የመምህራን ኮሌጅው ስጥ መምህር ሆነው አገልግለዋል።
ወታደራዊው መንግሥት በአማጺያኑ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በትውልድ አካባቢያቸው አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ነበር።
በማስከተልም ወደ መከላከያ ሠራዊቱ ገብተው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ነበር። ወደ አሜሪካ በመሄድ ወታደራዊ ትምህርት የተከታተሉት አሳምነው ከጦርነቱ በኋላ የጄኔራልነት ማዕረግ አግኝተው በሠራዊነቱ ውስጥ በኃላፊነት ሲያገለግሎ ቆይተዋል።
ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የመከላከያ ሠራዊቱን ኮሌጅ በበላይነት በመምራትና በማስተማር እንዳገለገሉ ይነገርላቸዋል። ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው በ2001 ዓ.ም ከሌሎች ወታደራዊ መኮንኖች ጋር መፈንቅለመንግሥትለማድረግ በማሴር ታስረው ነበር።
ጄኔራሉ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ስለተባሉ ማዕረጋቸው ተገፎ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ለዘጠኝ ዓመታት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከእስር ተፈትተው ለሃገራቸው የከፈሉት መስዋዕትነትን እውቅና በመስጠ ትማዕረጋቸው እንዲመለስና የሚያገኙት ጥቅም እንዲከበርላቸው አድርገዋል።
የአማራ ክልልም ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለአጭር ጊዜ በቆዩበት የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ሰጥቷቸው ነበር።
ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ትናንት ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተሞከረውና የክልሉን ፕሬዝዳንትና የሃገሪቱን ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹምንና የሌሎች ሁለት ከፍትኛ ባለስልጣናትን ህይወት ከቀጠፈው የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ጀርባ እንዳሉ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስታውቋል።
የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ኃላፊነቱን የተረከቡት አቶ ላቀ አያሌው ለክልሉ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ጄኔራሉንና ሌሎች የድርጊቱ ተሳታፊዎችን ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎች እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።

ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መግለጫ
በመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ስርዓተ ቀብር የሚያስፈፅም ኮሚቴ መዋቀሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

Office of the Prime Minister – Ethiopia ✔ @PMEthiopia
በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የተሰጠ ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ::
Press release regarding current issues. #PMOEthiopia 328 5:06 AM – Jun 23, 2019Twitter Ads info and privacy 484 people are talking about this
የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል
‘ሃገሪቱ ባለመረጋጋቷ’ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል
ዛሬ ሊካሄዱ ዕቅድ ተይዞላቸው የነበሩ የኢትዯጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ‘በወቅታዊ ሁኔታ’ ምክንያት መቋረጡን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ነግረውናል።
በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ-መንግሥትና የባለስልጣናት ግድያ እንዲሁም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከባልደረባቸው ጋር አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መገደል ለጨዋታዎቹ መቋረጥ ምክንያት እንደሆኑ ተረድተናል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ የሊግ እና ሌሎች በፌዴሬሽኑ ሥር የሚካሄዱ ጨዋታዎች እንደማይካሄዱ አቶ ባህሩ አክለው ነግረውናል።
ጨዋታ ለማድረግ የመጡ እንግዳ ቡድኖች ወደየመጡበት እንዲመለሱም ፌዴሬሽኑ አሳስቧል።
ፕሪሚዬር ሊጉና ሌሎች ውድድሮች ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጣቸውን የነገሩን ኃላፊው ጨዋታዎቹ መቼ እንደሚከናወኑ ነገሮች ይበልጥ ሲረጋጉ እናሳውቃለን ብለዋል።

በአዲስ አበባ የፀጥታ ጥበቃ እንደተጠናከረ ነዋሪዎች እየገለፁ ነው
በአዲስ አበባ የፀጥታ ጥበቃ እንደተጠናከረ ነዋሪዎች እየገለፁ ነው
አዲስ አበባ ዋና ዋና አካባቢዎች ጠበቅ ያለ የፀጥታ ጥበቃ እንዳለ የአዲስ አበባ ወኪሎቻችን ነግረውናል። ከአዲስ አበባ መውጣት እና መግባት እንደበፊቱ ቀላል እንዳልሆነም ማወቅ ችለናል። ምንም እንኳ እንቅስቃሴዎች በተለመደው መልኩ እየተከናወኑ ቢሆንም ‘አንዳች የሚከብድ ነገር አለ’ ሲሉ ነዋሪዎች ነግረውናል።
አዲስ አበባ ከተማ ላይ ሊከናወኑ ቀጠሮ የተያዘላቸው ክንውኖች አብዛኛዎቹ መሰረዛቸውንም ማወቅ ችለናል። ወደ አዲስ አበባ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ሰዎች ከሌላው ጊዜ በተለየ ጠበቃ ያለ ፍተሻ እንዳጋጠማቸው ማወቅ ችለናል።
የአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳርም ከበድ ያለ የፀጥታ ጥበቃ ውስጥ መሆኗንና ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በተጨማሪም የባህርዳር ነዋሪዎች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን ቤትም በመሄድ ኃዘን በመድረስ ላይ መሆናቸውንም የባህርዳር ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልፀዋል።

አቶ ላቀ አያሌው የአማራ ክልል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆነው ተሹመዋል
አቶ ላቀ አያሌው የአማራ ክልል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ሆነው ተሹመዋል
ትላንት በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ተሞከረ በተባለው መፈንቅለ-መንግሥት የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ አምባቸው መኮንን መገደላቸውን ተከትሎ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ላቀ አያሌው ተጠባባቂ ሆነው ተሹመዋል።
በመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ላይ እጃቸው አለበት የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት እሁድ ጠዋት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ምን ያክል ሰዎች እንዲሁም እነማን በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ግን የተሰጠ ማረጋገጫ የለም

የሥራ ኃላፊነታቸውን “ከባድና የሚያስጨንቅ… ነው” ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ናቸው?
ትናንቱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተገደሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት ከአራት ወራት በፊት ነበር።
በወቅቱም በክልሉ ምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ሲፈፅሙ የተጣለባቸው ኃላፊነት “ከባድ፣የሚያስጨንቅና በውስብስብ ፈተናዎች የተሞላ…” ሲሉ ነበር የገለጹት።
ደቡብ ጎንደር ጋይንት ያደጉት ዶ/ር አምባቸው መኮነን ሲሳይ የ48 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ።
በልጅነታቸው የፊዚክስና የሒሳብ ትምህርቶችን አብልጠው ይወዱ እንደነበር የሚነገርላቸው ዶ/ር አምባቸው ሕልማቸው መምህር መሆን ነበር።
የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወቅቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት ለማቋረጥ ተገደዋል። ከዚያም ትግሉን ከተቀላቀሉ ከ5 ዓመታት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በርቀት አጠናቀዋል።
የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ነው። የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን ደግሞ ደቡብ ኮሪያ በሚገኘው ኬዲአይ የፐብሊክ ፖሊሲና አስተዳደር ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።
በቅድመ ምረቃም ሆነ በድኅረ ምረቃ ያጠኑት የትምህርት ዘርፍ ምጣኔ ሐብትን ነው።
ከኮሪያ ተመልሰው ለ11 ዓመታት በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ካገለገሉ በኋላ ለሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ወደ እንግሊዝ አቅንተዋል።
የሥራ ኃላፊነታቸውን “ከባድና የሚያስጨንቅ… ነው” ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ናቸው?
ትናንቱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተገደሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት ከአራት ወራት በፊት ነበር።
በወቅቱም በክልሉ ምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ሲፈፅሙ የተጣለባቸው ኃላፊነት “ከባድ፣የሚያስጨንቅና በውስብስብ ፈተናዎች የተሞላ…” ሲሉ ነበር የገለጹት።
ደቡብ ጎንደር ጋይንት ያደጉት ዶ/ር አምባቸው መኮነን ሲሳይ የ48 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ።
በልጅነታቸው የፊዚክስና የሒሳብ ትምህርቶችን አብልጠው ይወዱ እንደነበር የሚነገርላቸው ዶ/ር አምባቸው ሕልማቸው መምህር መሆን ነበር።
የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወቅቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት ለማቋረጥ ተገደዋል። ከዚያም ትግሉን ከተቀላቀሉ ከ5 ዓመታት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በርቀት አጠናቀዋል።
የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ነው። የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን ደግሞ ደቡብ ኮሪያ በሚገኘው ኬዲአይ የፐብሊክ ፖሊሲና አስተዳደር ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።
በቅድመ ምረቃም ሆነ በድኅረ ምረቃ ያጠኑት የትምህርት ዘርፍ ምጣኔ ሐብትን ነው።
ከኮሪያ ተመልሰው ለ11 ዓመታት በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ካገለገሉ በኋላ ለሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ወደ እንግሊዝ አቅንተዋል።
ሦስተኛ ዲግሪያቸውንም እንዲሁ በምጣኔ ሐብት ዙርያ ከእንግሊዙ ኬንት ዩኒቨርስቲ ነው ያገኙት።
በበጀት እጥረት ምክንያት ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ለማቋረጥ ጫና እንደነበረባቸው፤ ደኞቻቸው ገንዘብ በማዋጣት ጭምር ያግዟቸው እንደነበር ከዚህ ቀደም ካፒታል ለተሰኘው ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
ዶ/ር አምባቸው ከትጥቅት ግሉ በኋላ ከወረዳ ጀምሮ አስተዳደራዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። ዋናነት ከሚጠቀሱት መሀል በአማራ ክልል የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር፣ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ለአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር፣የአማራ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊነቶች ይገኙባቸዋል።
በፌዴራል ደረጃ ደግሞ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኾነው ለአንድ ዓመት ያህል አገልግለዋል።ከዚያ በኋላም የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር በመሆን ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ጊዜ ሰርተዋል።
ከግንቦት 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሲሆን፣ ከሕዳር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የመሠረተ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ኾነው አገልግለዋል።
ዶ/ር አምባቸው ከለውጡ በኋላ ለርዕሰ ብሔርነት ታጭተው እንደነበርና ሕዝቡም ሆነ ፓርቲያቸው በፖለቲካው ተሳትፏቸው እንዲቀጥሉ በመፈለጋቸው ሐሳባቸውን መቀየራቸው ሲነገር ነበር።

አራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገድለዋል
አራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገድለዋል
በአማራ ክልል ከተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጋር በተያያዘ እስካሁን አራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት መገደላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አረጋገጡ።
ቃል አቀባዩ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ ባህር ዳር ውስጥ እንዲሁም የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን የሆኑት ጀነራል ገዛኢ አበራ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ አንደተገደሉ ተገልጿል።
ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖቹ የተገደሉት በጄነራል ሰዓረ መኮንን ጠባቂ መሆኑንና በጄነራሉ ቤት መሆኑ እንዲሁም ጥቃት ፈጻሚው በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል።


አቶ ምግባሩ ከበደ መጎዳታቸው እየተነገረ ነው
በአማራ ክልል በተፈፀመው ጥቃት ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንዱ አቶ ምግባሩ መሆናቸው እየተነገረ ነው
ትላንት አማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ውስጥ ተሞከረ በተባለው መፈንቅለ መንግሥት ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አንዱ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ መሆናቸው እየተነገረ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ‘የከሸፈ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ’ ብለው በገለፁት ጥቃት ላይ ነው አቃቤ ሕጉ መጎዳታቸው የተነገረው።
ትላንት አመሻሹን የተኩስ ድምፅ መሰማቱን የባህርዳር ወኪላችን አረጋግጦልናል።
የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊቀ መንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለሥራ አሜሪካ እንዳሉ ተሰምቷል።

DEVELOPING STORY: Fortune has learnt that the person who has sustained severe wound in Bahir Dar is the Attorney General of the Regional State, Megbaru Kebede. http://ow.ly/fe4650uKzli 11 3:38 PM – Jun 22, 2019Twitter Ads info and privacy See Addis fortune’s other Tweets
በአማራ ክልል ተፈፀመ የተባለውን መፈንቅለ-መንግሥት አስመልክቶ የጠ/ሚር ፅ/ቤት የሰጠው መግለጫ
በአማራ ክልል ተፈፀመ የተባለውን መፈንቅለ-መንግሥት አስመልክቶ የጠ/ሚር ፅ/ቤት የሰጠው መግለጫ

Office of the Prime Minister – Ethiopia ✔ @PMEthiopia
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ላይ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚፃረር፣ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ለረጅም ጊዜ የታገሉለትን ሰላምን ለመንጠቅ የተደራጀ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት ሙሉ በሙሉ ያወግዘዋል። 1/4 288 2:04 PM – Jun 22, 2019Twitter Ads info and privacy 228 people are talking about this
ባህር ዳር ውስጥ ትናንት ምን ተከሰተ?
ባህር ዳር ውስጥ ትናንት ምን ተከሰተ?
የአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርን ዳር ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አካባቢ ሲሰማ የነበረው ተኩስ ለአጭር ጊዜ የቆየ አልነበረም እየበረታ በመሄዱ በአቅራቢያው ያለው መንገድ ተዘግቶ የከተማዋን እንቅስቃሴ ክፉኛ አቀዘቀዘው።
ነገር ግን ተኩሱ ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አካባቢ በተጨማሪ በሌሎች የክልሉ መንግሥት ተቋማት ዙሪያ በተለይ በርካታ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በሚገኙበት የከተማዋ ክፍል ውስጥ በሚገኘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት አካባቢ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የተኩስ ልውውጡ በነማን መካከልና ለምን እንደሆነ ሳይታወቅ የከተማዋን እንቅስቃሴ በመግታት ነዋሪውን ስጋት ላይ ጥሎ ቢቆይም ከክልሉ መንግሥት በኩል ስለክስተቱ ምንም አይነት መረጃ ሳይወጣና ችግሩ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ ቆይቷ።
አመሻሽ ላይ ግን ምን እንደተከሰተ የሚገልጸው ቀዳሚ መግለጫ የተሰጠውባህር ዳር ከተማም ከክልሉ ባለስልጣን ሳይሆን ከአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ በኢትዮጽያ ቴሌቪዥን በኩል ነበር።
የተሰማውም ነገር ያልተጠበቀና በበርካቶች ዘንድ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ያስከተለ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት የክልሉን መንግሥት በኃይል ለመቆጣጠር ሙከራ መደረጉንና የፌደራል መንግሥቱ የጸጥታ ኃይሎች ጣልቃ በመግባት ድርጊቱን እንደተቆጣጠሩት ተናግረዋል።
አቶ ንጉሡ እንዳሉት የመፈንቅለ መንግሥቱ ሞካሪዎች የክልሉን መንግሥት መዋቅሮች ኢላማ ማድረጋቸውንና የጸጥታ ኃይሎች ክስተቱን ለመቆጣጠር እደተስማሩ ቢናገሩም ገልጸው፤ መንግሥት ሁኔታውን ቁጥጥር ስር ለማዋል አስፈላጊው ሁሉ እርምጃም እንደሚወስድ የተናገረዋል።
የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ትናንት አመሻሹ ላይ በባህር ዳር ከተማ ተሰማርተዋል።
የተኩስ ልውውጡን ተከትሎ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ ለማጣራት ቢቢሲ ባደረገው ሙከራስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፈለገ ህይወት ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ በጥይት ተመተው የቆስሉ ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ መግባታቸውን ገልጸው ማንነታቸውንና የጉዳት መጠኑን ከመናገር ተቆጥበው ነበር።

ባህር ዳር
ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ከመፈንቅለ-መንግሥቱን ሙከራ ጀርባ መሆናቸው ተገለፀ
በቅርቡ የአማራ ክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ትላንት አማራ ክልል ውስጥ ተፈፀመ ከተባለው መፈንቅለ መንግሥት ጀርባ መሆናቸውን የክልል ምክትል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለበል አማረ ለአማራ መገናኛ ብዙኃን አሳውቀዋል።
ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ የፀጥታ ኃይል አባላትን አስተባብረው መፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን አካሂደዋል ሲሉ መግለጫ የሰጡት።
ቀደም ሲል በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተከስሰው ዘጠኝ ዓመታትን በእስር ያሳለፉትና ባለፈው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ የአማራ ክልል ፅጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት ጥቅምት ወር ላይ ነበር።

የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ዶ/ር አምባቸው መኮንን መገደላቸው ተገለፀ
የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አምባቸው መኮንን መገደላቸው ተገለፀ
የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አቶ አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ትላንት በነበረው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተከትሎ መገደላቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አስታውቋል።
አቶ አምባቸውን ጨምሮ የርዕሰ መስተዳድሩ አደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ የሆኑት አቶ እዘዝ ዋሴም በደረሰው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸው ታውቋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ግለሰቦቹ ትላንት ስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት እንደሆነ ኢቲቪ አስታውቋል።
አቶ አምባቸውን መኮንን የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዝደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት የተሾሙት የካቲት 29/2011 ነበር።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ትላንት ተፈፀመ በተባለው የመንፈቅለ መንግሥት ሙከራ እጃቸው አለበት የተባሉ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉም ተሰምቷል።
የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ መንፈቅለ መንግሥቱን አቀነባብረዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፓርቲው አስታውቋል።
