June 24, 2019

ትንቢታዊ ቃልኪዳን? “ራሴን ለአማራ ሕዝብ ሰጥቻለሁ።” – ዶ/ር አምባቸው መኮንን

ከዶ/ር አምባቸው መኮንን፤ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጋር የዛሬ ሁለት ሳምንት ተነጋግረን ነበር። ዛሬ በሕይወት የሉም። ከሁለት ቀናት በፊት ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ለስብሰባ በተቀመጡበት ቢሮ የጸጥታ አስከባሪ ኃይል አባላት መለያ ልብስ በለበሱ ሰዎች በተከፈተ ተኩስ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

ዶ/ር አምባቸው በቃለ ምልልሳችን ወቅት “ራሴን ለአማራ ሕዝብ ሰጥቻለሁ” ብለውን ነበር።

በእርግጥ ያ ቃል ትንቢታዊ ቃልኪዳን ይሆን?

ቃለ ምልልሱን ለዝክረ መታሰቢያነት ደግመን አቅርበነዋል።