June 28, 2019

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/95811

( በእርግጥ እውነቱን ተናግረነዋልን??”አለባብሶ ማረስ ዋጋ እንደሚያስከፍል የኢትዮጵያ  ገበሬ አሳምሮ ያውቀዋል።)

በኢፌድሪ መንግሥት የአማራ  ክልላዊ አሥተዳደር  መንግሥትን በኃይል ማሶገድ ና ሥልጣነ   መንግሥቱን መያዝ ነው ፣የአዴፖ አንጃዎች ፍላጎት፣ወይስ የእኛን ሃሳብ ካልተቀበላችሁ ና ካልተገበራችሁ በህይወትም አትኖሩም ነው?ወይስ “ከእኛ ሰልፍ ጋር የመሰለፍ ወይም ያለመሰለፍ ፣በህይወት የመኖር ወይም ያለመኖር ምርጫ ነው።” ተብሎ ተነግሯቸው፣ሰልፋቸውን ለመሰለፍ ሥለአንገራገሩ ወይም  ለመሰለፍ ባለመፈለጋቸው በምርጫቸው መሰረት “ምርጫችሁን አሳውቁን” ያሏቸው  ሰዎች በህይወታቸው ላይ ጨክነውባቸዋል?ወይስ ሟቾቹ ለምሳ ሲያስቧቸው ገዳዮቹ ቁርስ አድርገዋቸዋል? ወይስ ከነሱ ውጪ  ሌላ ረቀቅ ያለ ሴራ ነው፤ እየተከናወነ ያለወ? በሴራ ቲዎሪ(conspiracy theory) አግባብ የተፈፀመ???ልክ እንደ ፕሪሰን ብሬክ (prison break ) ፊልም አይነት ፣እጅግ የረቀቀና የተቀነባበረ  ሴራ?    ” የአማራ ክልል መንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ የተደረገ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው።” ብለን ለመናገር አማራ ክልል ራሱን የቻለ ግዛት የሌለው በአሥተዳደራዊ ወሰን ብቻ የሚታወቅ የኢፌዲሪ  መንግሥትን ካዋቀሩት ክልሎች  አንዱ ነው። በመሆኑም በአማራ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ላይ ፣የነሱን ሥልጣን በማይፈልጉ ግለሰቦች፣ቡድኖች ወይም በህቡ በተደራጁ ኃይሎች  ፖለቲካዊ ግድያ “poltical assassination ” ተፈፀመ ማለት አንችላለን እንጂ ፣የአንድ ሀገር አሥተዳደራዊ ክልል አሥተዳዳሪዎችን ወይም ቆንጮ መሪዎችን በመግደል የነሱን ሥልጣን በመያዝ የሚፈልጉትን ለመተግበር የሚያሥችል ኃይል እንደማይኖራቸው እያወቁ ይህንን ግድያ ለመፈንቅለ መንግሥት ብለው ፈፀሙ ማለት ከነባራዊው የኩፕዴታ “coup d’etat” ትርጉም ያፈነገጠ ነው።ምክንያትም በሀገር መሪዎች ላይ የተፈፀመ ወይም የአንደ ሀገር መንግሥትን አገዛዝ ለማሶገድና በሌላ ለመተካት የተፈፀመ ባለመሆኑ።  coup d’etat a sudden decisive exercise of force in politics; especially : the violent overthrow or alterationof an existing government by a small group a military coupd’état of the dictator.   ይህንን ትርጉም አያሞላም።የክልል መንግሥትንም በመለወጥ በመንግሥትነት የመቀጠል የሰዓታት ዕድሜ እንኳን አይኖራቸውም።በዜያው ፍጥነት ፌደራል መንግሥቱን ለመገልበጥ አቅደው ከሆነ ግን ፣ “የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” ለማለት እንችላለን።ይሁን እንጂ ድርጊቱ፣ከፍተኛ የሥልጣን ኃይል ባላቸው ግለሰቦች በሴራ ትወራ የተመራ መሆኑን መጠርጠር እንችላለን።  እንደሚታወቀው ከፍተኛ የመንግሥት  ባለሥልጣን የሚመራው በሥልጣን የታገዘ ሴራ ና የሴራ ትወራው (conspiracy theory ) እጅግ የረቀቀ ና ተራው ሰው የማይገምተው ነው።በተለይም የመንግሥት የደህንነት መዋቅር ውሥጥ ያሉ ሰዎች የሚተገብሩት ሴራ ከሆነ ፣ የከፍተኛውን የመንግሥት አመራር ጭምር የሚያቄል ነው።     እነዚህ ሥለህግ ና ሥለወንጀል ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው የሚሸሩበት ሴራ ፍንጭ አልባ የሚያደርገው ፣በደህንነት፣በፖሊሥ፣በልዩ ጥበቃ ሥም ፣የሴራቸው ሰለባ በሚያደርጉት ባለሥልጣንም ይሁን ማንኛውም የሴራቸው አደናቃፊ ኃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ የሚወስዱ ፤ ባሥ ሢልም እርምጃ ውሰድበት ብለው ያዘዙትን  የሴራ አባል የማያዳግመውን እርምጃ ቃታ ሥቦ ከገደለው በኋላ፣ በሌላው የሴራ አባል የሚያሥገድሉ ናቸው።አሥገድለው ሲያበቁም   ማንንም ሊያሳምን የሚችል ዜና የሚፈጥሩ ናቸው።ሃሰተኛ ዜናውንም ቦታው ድረስ ወስደው ለሚመለከተው የመንግሥት ባለሥልጣን እና የምርመራ ክፍል በማሳየት ተአማኒነት ያለው ዜና ይፈጥራሉ።(ዱካቸውንም ከወንጀሉ በኋላ  ፈፅመው ሥለሚያጠፉም ማንም መርማሪ መረጃ ና ማሥረጃ አያገኝባቸውም።)     እንደዚህ አይነት የሴራ ቲዎሪዎች በማንኛውም ሀገረ  መንግሥት ውሥጥ አሉ።አውሮፖ፣አሜሪካ፣ኢሲያ ፣አፍሪካ፣አውሥትራሊያ ፣ባሉ መንግሥታት ውሥጥ ትላንት በጣም በረቀቀ መንግሥታዊ ሴራ ብዙ ዜጎች የሀገርን ሥም ያጠፋሉ፣ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ  ሊያደርሱ ይችላሉ ተብለው በተቀነባበረ ሴራ ተገድለዋል።     በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ታሪክም ፣ አያሌ መፈንቅለ መንግሥት ተካሄዷል።      የአዲስ አበባው የሀገር መከላከያ ኢታማጆር  ሹሙ እና የባህር ዳሩ በኢፌድሪ መንግሥት    የአማራ ክልላዊ መንግሥት ላይ  የተፈፀመ  ግድያ ግን የዘር  ፖለቲካው እና ሥርአቱ  የወለደው የግድያ   ተግባር ነው። እናማናቸው የፈፀሙት?? ለምን እና ለነማን ወይም ለማን ጥቅም ?? ይህንን ጥያቄ ጊዜ በወቅቱ ይመልሰዋል። ..ለሁሉም ጊዜ አለው።     ይህንን በህዝብ ውሥጥ አያሌ ጥያቄ ያነሳ የግድያ ተግባር ግን፣  አለባብሰን ለማለፍ የምንሞክር ከሆነ ነገ ከነገወድያ የምንከፈለው መሰዋትነት እጅግ የከፋ እንደሚሆን መገመት ነብይ አያሰኘንም።