ሰኔ 28, 2019

ቢልለኔ ስዩም

የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ጄኔራል ዐደም መሃመድን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድረገው ሾመዋል፡፡

አዲስ አበባ — 

ሌተናል ጄኔራል ሞላ ኃይለማርያምን የመድር ኃይል አዛዥ፣ አቶ ደመላሽ ገ/ሚካዔል ደግሞ የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አድርገው ሞሾማቸውን የጠ/ሚኒስቴት ጽ/ቤት ለአሜሪካ ድምፅ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የለውጥ ሂደት ሰሞኑን በባህርዳርና በአዲስ አበባ በተፈፀሙት ዓይነት ድርጊቶች እንደማይደናቀፍ የጠ/ሚ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የጠ/ሚኒስተሩ ቃል አቀባይ ቢል ለኔ ስዩም ዛሬ ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች እንዳሉት መንግሥት ከመጋቢት 2010 ጀምሮ በጀመረው የለውጥ መንገድ ይቀጥላል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ ሹመት ሰጡ

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ ሹመት ሰጡ

by ቪኦኤ Embed share The code has been copied to your clipboard. The URL has been copied to your clipboard