June 28, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/127410

BBC Amharic : የኢትዮጵያ ኤምባሲ በታንዛኒያ በሚገኙ ስምንት ክልሎች በሚገኙ እስር ቤቶች ባደረገው አሰሳ 743 ኢትዮጵያውያን እስረኞች መገኘታቸውን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚኒስትር ካውንስለር አቶ ቴዎድሮስ ግርማ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በታንዛኒያ ወደ 21 ክልሎች አሉ ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ከማክሰኞ ጀምሮ በቀሪዎቹ 13 ክልሎች አሰሳ እንደሚያካሂዱ ተናግረው የእስረኞቹ ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ያላቸውን ግምት ገልጸዋል።
በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከፍቶ በይፋ ሥራ ከጀመረ አምስት ወር ገደማ እንደሚሞላው ያስታወሱት አቶ ቴዎድሮስ እስካሁን ድረስ 1ሺህ 50 ሰዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ተናግረዋል።
ኤምባሲው በታንዛኒያ የተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር በትክክል ለማወቅ ባደረጉት አሰሳም እስካሁን ድረስ 743 ገደማ እስረኞችን በስምንት እስር ቤቶች ማግኘታቸውን ጨምረው አስረድተዋል።
ከእስረኞቹ መካከል አንድ ሴት ብቻ እንደምትገኝ የገለፁት አቶ ቴዎድሮስ ዕድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ አዳጊዎች፣ ወጣቶች እና የሰባት ልጆች አባት እንደሚገኙበት ገልፀዋል።
አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት የእነዚህ እስረኞች ቤተሰቦች ልጆቻቸው የት እንዳሉ፣ እንዲሁም በሕይወት ስለመኖራቸውም ስለማያውቁ ስም ዝርዝራቸውን በኤምባሲው የፌስቡክ ገጽ ላይ በየወቅቱ እንደሚለጥፉ ተናግረዋል።
ከዚህ በታች ባለው የኢምባሲው የፌስ ቡክ አድራሻ በመግባት የእስረኞቹን ስም ዝርዝር ማግኘት ይቻላል ብለዋል።
እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሦስት ዓመት እና ከዚያ በታች በእስር ላይ የቆዩ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ቴዎድሮስ አንዳንዶቹ እስራቸውን ጨርሰው ከማረሚያ ቤቶች ያልወጡ እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
የታንዛኒያ መንግሥት እስረኞቹ የእስር ጊዜያቸውን እንደጨረሱ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ቢፈልግም ከሚገኙበት እስር ቤት ወደ ዳሬሰላም ወይንም ኪሊማንጀሮ አየር ማረፊያ ለማምጣትና የአየር ትኬት