July 4, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/128871

Image

ከሰሞኑ የባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞ በየክልሉ ያሉ የ”ልዩ ኃይሎች” ጉዳይ እያጠያየቀ ነው።መንግስታዊው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ “ክልሎች ከአስር ሺዎች እስከ መቶ ሺዎች የሚቆጠር ልዩ ሃይል እንዳላቸው የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ” ብሏል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ በክልላቸው “ልዩ ኃይል የሚባል መዋቅር አለመኖሩን” ለአዲስ ዘመን ተናግረዋል። በመዋቅሩ ውስጥ ያለው “መደበኛ ፖሊስ እና አድማ በታኝ” ነው ባይ ናቸው።
የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጀይላን አብዲ በክልሎች በልዩ ሃይል ስም የተቋቋመው “ከፖሊስ በላይ ነው” አሉ። “ዙ፣ መትረየስና ሌሎች ከባድ መሣሪያዎችን በመታጠቅ ከመከላከያ ጋር በእኩል ደረጃ ላይ ናቸው” ብለዋል ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ።

“ልዩ ኃይል” የደህንነት ዋስትና ወይስ ፈተና
ክልሎች ከአስር ሺዎች እስከ መቶ ሺዎች የሚቆጠር ልዩ ሃይል እንዳላቸው የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ። የተወሰኑ ምሁራንና የፀጥታ ባለሙያዎች ልዩ ሃይሎቹ”ለአገሪቱ የፀጥታ ችግርና ለአገር መበትን መንስዔ ሊሆኑ ይችላሉ” ሲሉ ይሞግታሉ። ሌሎች ባለሙያዎች ደግሞ የክልል ልዩ ሃይሎች “ለሕገ መንግሥቱና ለአገሪቱ ፀጥታ መጠበቅ ዋስትና ናቸው” ይላሉ።
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የፌዴራሊዝምና ሕገ መንግሥት መምህሩ አቶ ደሳለኝ ጥጋቡ፤ የፌዴራሊዝምን ሥርዓት የተገበሩ አገራት የውስጥ ፀጥታቸውን ለማስጠበቅ በፌደራልና በክልሎች ባልተማከለና ወጥ በሆነ አስተዳደር እንደሚያዋቅሩ ይገልፃሉ።
ምሁሩ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 52 ንዑስ አንቀጽ 2 (ሰ) ክልሎች “የክልላቸውን ፖሊስ ያደራጃሉ ይመራሉ” የሚለውን አንቀጽ በመምዘዝም ኢትዮጵያ የውስጥ ፀጥታዋን ባልተማከለ አስተዳደር እንደምትመራ ያመላክታሉ። ሕገ መንግሥቱ ክልሎች የሚያዋቅሩትን የፀጥታ ሃይል ስያሜውን በትክክል ባይናገርም የፀጥታ ሃይል እንደሚያደራጁ