July 3, 2019

Posted by: ዘ-ሐበሻ

አሁን ተሰራ የሚባለው ወንጀል የተቀነባበረ ሴራ እንጂ መፈንቅለ መንግስትም ሆነ የሽብር ስራ አይደለም። ወንጀሉን አቀነባበሩ የተባሉ ግለሰቦችም የሴራው ተጠቂ እንጂ የድርጊቱ ፈፃሚዎች አይደሉም። ይህ ሴራ ሆን ተብሎ የተቀነባበረው አብይ በሚመራው ፓርቲ በኢህአዴግ ነው።
አከተመ!
~~
አላማው፦
1. የአማራ ህዝብ አማራ ነኝ ብሎ በመደራጀቱ እየተጠናከረ መሆኑ ስላስፈራው ትግሉን ለማኮላሸትና ህዝቡ ዳግመኛ አይደለም መታገል አማራ ነኝ ብሎ መናገር እንኳ እስኪፈራ ድረስ ተሸማቆ እንዲቀር በፀረ አማራ አቋም የታሸ ሴራ ነው።
2. የአማራ ህዝብ ከሚደርስበት ተደጋጋሚ ብሄር ተኮር ጥቃት ራሱን መከላከል እንዳይችል ሲባል ለራሱ ደህንነት ሲል የሚያሰለጥነውንና ያሰለጠነውን ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይልና አድማ በታኝ በሽብርተኝነት ከስሶ ለማሰር፣ አመራሮቹን ለማሰር (አንዳንዶቹንም ለመግደል)፣ የክልሉን ህዝብ ትጥቅ በማስፈታት ወረራን ፈፅሞ መመከት እንዳይችልና ያለምንም ስጋት ወራሪው ወረራውን እንዲፈፅም ለማስቻል ነው።
3. በትግራይና በአማራ ክልል መካከል ያለውን አለመግባባት ለማባባስና ሁለቱ ህዝቦች እርስ በርስ የበለጠ እንዲካረሩ፤ እንዲሁም የአማራን ህዝብ ለመውረር በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ ከትግራይ ጋር የሚፈጠረው መካረር እንዲያግዝ፤ ብሎም የክልሉ ሃይልም ሆነ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እንዲከፈትበትና እንዲበታተን በማድረግ የወረራ አላማውን ለማሳካት ነው።
ለዚህም ሲባል ነው ኦሮሞ ያልሆኑ ጀነራሎችን ወይም ትግሬ የሆኑ ጀነራሎችን (ጀ/ል ሰዓረንና ጀ/ል ገዛኢን) በመምረጥ በራሱ በመንግስት ሴራ በመግደል ገዳይ ተብዬው ለመረጃ እንዳይተርፍ በመግደልና ‘ራሱን አጠፋ’ በሚል ክህደት በመፈፀም የትግራይ ህዝብ በአማራ ህዝብ ላይ ቁጣን ለመቀስቀስ የተሞከረው።
የትግራይ ህዝብም ይህን እንዳይጠረጥር የሴረኛው መንግስት መሪ ባለፈው ወደ አክሱም በመሄድ ከህወሃቶች ጋር እርቅ አውርዶና ሴራን ሸርቦ መመለሱን እናስታውሳለን። በእኔ እምነት የጀነራሎቹን ሰለባነት የህወሀት መሪዎችም ያውቃሉ። ከህወሃት ተለይተው ከአብይ ጋር በመወገናቸው በህወሀት እንደ ጠላት የሚታዩ መሆናቸውን እናውቃለን፤ ግድያው ለሰዓረ እንጂ ለገዛኢ እንዳልነበረም የምናውቀው ጉዳይ ነው።
4. ሌላው በክልሉ አመራሮች ላይ የተደረገው ግድያ በማንም ሊሳበብ እንዳይችል ተደርጎ የክልሉ አመራርና ህዝብ እንዲከፋፈል፤ እንዲሁም እርስ በራሱ እየተጋጨ እንዲዳከም ለማድረግ ነው።
5. የአዲስ አበባን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሚከታተለው የአማራ ህዝብ ስለሆነ፤ እንዲሁም ከእስክንድር ነጋ ጎን በመቆሙና እስክንድርም የመጀመሪያ ስብሰባውን እንዲያደርግ ከባህር ዳር በመጋበዙ፤ አዲስ አበባን የማወረሙ ስራ ያለምንም እንቅፋት እንዲሳካ፤ ባልዴራስ በአጭሩ እንዲቀጭና ምናልባትም እስክንድር ነጋን በተቀነባበረ ክስ ከተፈበረከው የመፈንቅለ መንግስት ዜና ጋር በማያያዝ ለማሰር ወይም ለመግደል ታቅዶ ነው።
~~
ማስረጃ፦
1ኛ. የሴረኛው መንግስት መሪ በግልፅ ከእስክንድር ነጋ ጋር የማያቋርጥ መገዳደል ውስጥ እንገባለን ብሎ ዝቶ የነበረ መሆኑ፤
2ኛ. የኦፒዲኦ ህዝብ ግንኙነት የሆነው አዲሱ አረጋ “ባላደራ እና ባለተራ የሚለውን ሃይል በቅርቡ ስርዓት የማስያዝ ስራ እንሰራለን” ብሎ አዳማ በነበራቸው ስብሰባ ላይ ከተናገረ ገና ሳምንት እንኳን ያልሞላው መሆኑ፤
3ኛ. ከሳምንታት በፊት የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረው ጀነራል አሳምነው ፅጌ “የፌደራል መንግስት የአማራ ሃይሎችን አፍኖ ለመውሰድ ባህር ዳር ገብቶ ነበር” ሲል በክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተናገረ መሆኑ፤
4ኛ. የሴረኛው መንግስት መሪ ደሴ ባደረገው ንግግር “ለክልሉ የምንበጅተውን በጀት ሚሊሻ ለማሰልጠን ከዋለ ልማት ከየት ይመጣል?” የሚል ነገር ካነሳ ገና አንድ ሳምንት ያስቆጠረ በመሆኑ፤
5ኛ. ችግሩ እንደተፈጠረ ከመቅፅበት፣ ያለምንም ማጣራትና ምርመራ፣ መፈንቅለ መንግስት እንደተደረገ እና አቀነባባሪውም ጀነራል አሳምነው ፅጌ ነው የሚል መግለጫ መውጣቱ፤
6ኛ. መፅሃፍ “አህዛብ በልፍለፋቸው ብዛት የሚሰሙ ይመስላቸዋል” እንዳለ ወዲያውኑ የሴረኛው ኢህአዴግ ሴሎች እየተቀባበሉ ያስተጋቡት መሆኑና ምንም አይነት የማጣሪያ ስራ ሳይሰራ ቀጥታ ወደ እርምጃ መገባቱ፤
7ኛ. ህዝብ ሳይረጋጋና ካለበት የመደናገጥ ስሜት ሳይወጣ የታቀዱ ፀረ አማራ እርምጃዎች ባናት ባናት እየተወሰዱ መሆኑ፤ (ለምሳሌ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ሃላፊ ተገድሏል፣ የአማራ ልዩ ሃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ መታሰሩ፣ የክልሉ ፀጥታ ሃላፊ ጀነራል አበረ አዳሙ መታሰሩ፣ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እየተመታ መሆኑ፣ ….)።
8ኛ. የአማራ ህዝብ በማንኛውም ህዝብ እንዲጠላና በጥርጣሬ እንዲታይ በተቀናጀና በተባበረ መልኩ በመንግስት መዋቅርም ሆነ በብዙሃን መገናኛ ሚዲያዎች ሰፊ ዘመቻ እየተደረገ መሆኑ፤
9ኛ. ምንም አይነት የመፈንቅለ መንግስት መልክ የሌለውን ድርጊት ቀድሞ ለታቀደው ሴራ ግብዓት እንዲሆን ታስቦ በማንኛውም መስፈርት ለማይገናኝ ድርጊት የማይገናኝ ስም መሰጠቱ፤
10ኛ. ከላይ በተዘረዘሩ ምክንያቶች ሁሉም የኢህአዴግ መዋቅሮች በአማራ ህዝብ ላይ የተጀመረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ተቀብለው ማራገባቸውም ብቻ ሳይሆን የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ በሚል የሚወሰደውን የዘር ፍጅት መደገፋቸው፤
11ኛ. ምንም ትስስር የሌለውን የነ ሰዓረን ሞት አሳማኝ ባልሆነ ሁኔታ ባ/ዳር ከተደረገው ሴራ ጋር ለማገናኘት መሞከሩ፤
12ኛ. በርካታ የባላደራው ምክር ቤት አባላቶች መንግስት ነኝ በሚለው አካል ተጠራርገው መታሰራቸው፤ … ወዘተ።
~~
መደምደሚያ!
~~
እየሆነ ያለው ፀረ አማራዎቹ እንዲሆን እንደፈለጉት ነው። ስለዚህ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አዴፓ አቅም እንዳያንሰውና ሙሉ በሙሉ በኦነግ መራሹ ኢህአዴግ እንዳይዋጥ በአማራነት አለት ላይ በፅናት እንዲቆም ልናግዘው ይገባል። ሆነም ቀረም በአዴፓ ይሁንታ ብዙ ውሳኔዎችና እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ። በዚህ ፈታኝ ወቅት የአዴፓ አማራዊ አቋም እጅግ ወሳኝ ነው። በተለይ ድርጅቱ የእነ አብይ ሴራና ተንኮል እስኪገባው ድረስ ሊነገረው ይገባል።
~~
ከዚህም በተጨማሪ ሁሉም የአማራ ወጣት የአብይን የውሸት ቅሌትና በአማራ አመራሮች እንድሁም በመላው የአማራ ህዝብ ላይ ላሳየው ድፍረት አንድ ሆኖ መነሳት አለበት። የአብይ የሴራ ፖለቲካ መጋለጥና የአማራ ህዝብ አንድ ሆኖ የአብይን ፀረ አማራ እንቅስቃሴ መመከት እንዲችል መስራት አለበት።
አለቀ ።
አቤል ዋበላ Sponsored by Revcontent