ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ወ/ሮ አዳነች ገዳ ዋቅኬኔ ማን ናቸው??.

Image may contain: 1 person
Image may contain: 1 person, smiling, sitting and closeup

በ መኮንን ሃሰን እንደተነገረው፤…

” ለልጃቸው ለጓደኛዬ ዮሃንስ ታከለ፤ ወንድምና እህቶቹ እንዲሁም ለመላው ቤተሰብ መፅናናትን እመኛለሁ ብሎ ታሪኩን ይጀምራል፤….”

“ወ/ሮ አዳነች ገዳ ዋቅኬኛ በአካባቢው ህዝብ በተለይ በወጣቱ “አድዬ” በመባል ይታወቁ ነበር። የስምንት ልጆች እናት በመሆን ቤተሰባቸውን ያስተዳድሩ የነበሩት ወ/ሮ አዳነች በአዲስ አበባ ውስጥ በተክለሃይማኖት አካባቢ በቀበሌ 44 ወጣቶች በጣም የተወደዱና የተከበሩ እናት ነበሩ። ያካባቢውን ወጣቶች እንደ እራሳቸው ልጆች በማየት፤ ለልጆቻቸው በናትነት የሚሰጡትን ፍቅር ላካባቢው ወጣትም በእኩልነት አካፍለዋል። ዘር ሃይማኖት ሳይለዩ፤ በደስታም ጊዜ ሆነ በዛ በመከራም ወቅት በተግባር ከወጣቱ ጎን በመቆም ኢትዮጵያዊ እናትነታቸውን አስመስክረዋል።

ወ/ሮ አዳነች ገዳ ላካባቢው ወጣት ካላቸው የእናትነት ፍቅር የተነሳ የዛ ትውልድ ወጣት ከፋሺስቱ ደርግ ጋር ከሚያደርገው ትግል ጎን ተሰልፈው “በእናቶች ብዙሃን መሃበር” በህቡዕ በመደራጀት ታግለዋል። በደርግ ወንጀለኞች ክትትል ሊያዙ ያሉ ወጣቶችን በመደበቅና በማስመለጥ ነፍስ አድነዋል። በተወሰነም ደረጃ የኢሕአፓ የፕሮፖጋንዳና የሚበተኑ ወረቀቶን በቋጠሮአቸው ይዘው ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ ከቦታ ወደ ቦታ አሸጋግረዋል። የታሰሩ ወጣቶችን ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት በመሄድ ጠይቀዋል፤ ይፈቱ ብለውም ተሰልፈዋል።

ብዙ ጀግና እናቶች ከልጆቻቸው ጎን ቆመው የደርግን አምባገነንነት ሲታገሉ ለእስር ተዳርገዋል፤ አስከፊ ግብረ-ስዬል ተካሂዶባቸዋል፤ ከአንድም ሁለት ልጆቻቸውን፤ ዘመድ አዝማድ ወይም የልጆቻቸውን ጓደኞች በደርግ ወንጀለኞች ተነጥቀዋል፤ በግፍ ተረሽነዋል። ወ/ሮ አዳነች ገዳም ከነኝህ ጀግና ኢትዮጵያዊ እናቶች አንዷ ነበሩ።

በዚህ አጋጣሚ ሳላስታውስ የማላልፈው ከ 41 አመት በፊት በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞተ የተለዩት ባለቤታቸው አቶ ታከለ ውቤ፤ በአካባቢያቸው በጣም የተከበሩ፤ ወጣቱም በሚያደርገው የኢሕአፓ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸው አባት ነበሩ። በአካባቢያቸው የእድር ዳኛ ሆነው ህብረተሰቡን ከማገልገላቸውም ባሻገር በተለያዩ ወቅቶች ከወጣቱ ጋር በማመፅ እስረኞችን በማስፈታትም ተባብረዋል።”

ወ/ሮ አዳነች ገዳ በደረሰባቸው ህመም ምክንያት MONDAY, JUNE 24/ 2019 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ወ/ሮ አዳነች ገዳ በአሁኑ ሰአት ከልጆቻቸው ጎን ቆመው ለሚታገሉ እናቶች አርአያና ምሳሌ ናቸው። በጣም እንኮራባቸዋለን!!!!!

ነፍስ ይማር!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!