July 10, 2019

ብዙ የአማራ ወጣቶች፤ የአማራ “አክቲቪስቶች” እና ብዙዎቹ ደደብ የአማራ ምሁራን እና ነፈዝ ጋዜጠኞች የሚያወሩት ወሬ “አማራ አንድነቱን እንዳይፈረካከስ “ጥንቃቄ” እናድርግ የሚሉትን የነፈዘ ክርክራቸው ሳደምጥ እጅግ ይገርመኛል። እንዲህ የሚመክሩዋቸው ደግሞ የዘለፋ ግምባር ቀደም ሰንዘሪዎች የሆኑት “የኢትዮጵያዊነቱን ዘንግ ይዞ የተሰዋው፤ በቃሉ የጸናው የአማራው አርበኛ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን” ከሃዲ እና ጡት ነካሽ፤ ያውም አጼ ቴዎድሮስ ሲዘለፉበት የነበሩባቸው ቃላቶች እየተጠቀሙ ሕሊናው የዞረበት ዕብድ” እያሉ አንድነትን የሚያፈርሱ ቃላት የሚጠቀሙት እነ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ እና እነ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ወፈፌው መቶ አለቃ አበረ አዳሙ የመሳሰሉ ባንዳዎች ናቸው። ማሕበረሰቡን የሚያለያይበት ብትር እያቀበሉ፤የሚያራርቅ ዘለፋ “እየዘለፉ” ስለ አንድነት ስያወሩ ይገርመኛል።
እራሳቸው እነዚህ ሰዎች “ለ28 አመት ያደፈ ገበና ማሕደር ተሸክመው የአማራን ህይወትና የሰባ/ለም/ መሬት በጠላት እጅ ወድቆ እንዲጠቃ ሲያድርጉ የነበሩት የፋሺስቶቹ ወያኔ “አገልጋዮች” የነበሩ ዛሬ ደግሞ የኦሆዴድ/ኦነግ አሽከሮች የሆኑት እነ ደመቀ መኮንን፤ እና የባሕር ዳር ፖሊስ ኮሚሽነር ሆኖ የተሾሞው ስዊድን አገር “መነግሥታዊ ዌልፌር/ዕርጥባን” እየተረጠበለት ሲተዳዳር የነበረው ወደ ኤርትራ ከመሄዱ በፊት በወያኔ ሥርዓት “አዲስ አበባ” ውስጥ የአንድ ወረዳ “ምርመራ ክፍል ሹም” ሆኖ በብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች ፋሺሰታዊ ሕገደምብ’ ማሓላ ፈጽሞ ፡ ‘ጸረ ወያኔ’ ዜጎቻችንን “ሲያሳድድ” የነበረው የወያኔ አገልጋይ እና “በጸረ አማራነት የታወቀው የግንቦት 7 ድርጅት” የአመራር አባል የነበረው “ልክፈተኛ ወፈፌው “የመቶ አለቃ አበረ አዳሙን” ልሳን ተማምነው “የአማራን ደህንነት እያስጠበቁ “አማራውን ከፋሺስቱ ሥርዓት” ነፃ ያወጡታል የሚሉ ነፈዞች እጅግ እጅግ መወገዝ አለባቸው።
እነዚህ ሆዳም አማራዎች ከአግልጋይ ባሕሪያቸው እና ለወያኔ አድረው ለ28 አመት የሠሩት ወንጀል እና ተልካሻ አድርባይ ባሕሪያቸው ተላቅቀው “የፋሺስት ሥርዓት” ይቃወማሉ ብሎ ማለት አንድም ለ28 አመት የተጓዙበት ባሕሪያቸው እና እስካሁን ድረስ ያልተናዘዙበት ወንጀላቸው ካለመረዳት የመነጨ ነው፤ወይንም በአፓርታይዱ ስርዓት መሪ ሚና እየተጫወቱ ካሉት ሰዎች ጋር ያላቸው የ28 አመት “ጓዳዊ” ግንኙነት መርምሮ ያለመረዳት የመነጨ ካልሆነ በስተቀር እነዚህን ምርጥ የአማራ ተወካዮች እና ልምድ ያላቸው ናቸው ብሎ ተስፋ ማድረግ ዛሬም ‘ውሃ መውቀጥ’ ነው።
ሌላ ቀርቶ “ የስራ ተሞክሮ ያላቸው ናቸው” እያሉ የፋሺሰቶች ባሕሪያዊ ተሞክሮ እንደ ቁም ነገር አድርገው በማየት የሚሰብኩ ሰባኪዎች ይገርሙኛል። ከልምዳቸው መማር ባልቻሉት በነ ደመቀ መኮንን፤ንጉሡ ጥላሁን እና የመሳሰሉ የወያኔ እና የኦነግ/ኦሆዴድ ፉርጎ/ተጎታቾች ላይ ተስፋ የሚጥሉ የዋሆች የጭንቅላታቸው ብስለት ደካማ ነው።
ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት እኔ እነዚህ ሰዎች ለ28 አመት ታዝቤአቸዋለሁ። ለ28 አመት ብቻየን (ከጥቂት በጣም በጣት ከሚቆጠሩ ጛዶቼ ጋር ሆኜ) ለበርካታ አመታት አማራ እየተጠቃ ነው እና እባካችሁ “ተነሱ” ካልሆነም “እባካችሁ የወያኔ እና የተገንጣይ ኦሮሞዎች እና ከአክራሪ እስላም ፖለቲከኞች እያንቆለጳጰሳችሁ ከእነሱ ጋር በእየ አዳራሹ እየተሞዳሞዳችሁ የአማራን ጥቃት እንዳይደመጥ ከማድረግ ተቆጠቡ” ስል እንደነበር በጻፍኳቸው በርካታ መጻሕፍቶቼም ሆነ በየድረገጾቹ ከምለጥፋቸው እና ካደረግኳቸው ቃለ መጠይቆች ስትከታተሉኝ የነበራችሁ ወዳጆቼ የምታውቁት ሃቅ ነው።
ይባስ ብለው እኔን ሲቃወሙ የነበሩት ከወያኔ እና ከኦነግ ብሶባቸው ሲቃወሙኝ እና ሲዘልፉኝ የነበሩት በሚገርም ሁኔታ “አማራዎቹ” ናቸው። “አፍክን ዝጋ” ሲሉኝ የነበሩት “አማራዎቹ ናቸው”። የአማራ ወጣቶችን ወደ ጠባብ ብሔረተኛነት እንዲገቡ እየገፋሃቸው ነው እያሉ ሲከራከሩኝ ነበር። ከዚያም አልፎ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኔን ረስተው “አንተ ትግሬ ነህ አማራ ጋር ምን አገባህ እያሉ ወገኖቻቸው ሲታረዱ፤ እርጉዞች በቢላዋ ሲተለተሉ፤ እህቶቻችን ሲደፈሩ ፤ ነብሰጡሮች ወደ ገድል ሲወረወሩ፤ ዓይነ ስውራን ብላታቸው በቢላዋ ሲሰለቡ፤ እያዩ ፤እየሰሙ ያንን ከማስቆም ይልቅ፤ እኔን በትግሬነቴ ብቻ ፡”ትግሬ ትግሬ ነው” እያሉ “የመንግሥት ያለህ የሕዝብ ያለህ ድረሱልን” እያሉ ሲጮሁ የነሱን ጩኸት ዘግተው የኔንም ብዕር ዝም ለማሰኘት ያልጣሩት ነገር አልነበረም።
አሁን ቤፌስቡኩና በየ ቴሌቪዥኑ ‘አማራ አማራ’ እያለ “ምላሱን የሚያሞረሞረ” የምታደምጡት “አማራ ነኝ ባይ” ከጥቂት አመት በፊት ‘ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ’ መስሎ ሌሎችን ሲያደራጅ እና ሲያሞካሽ የነበረ ነው’። አረ አንዳንዱ ምሁር እማ እኛ አማራዎች “ኦሮሞውን ይቅርታ እንጠይቅ ሲል የነበረ ነው” (እኔ ከነስማቸው የማውቃቸው ዘሐበሻ ድረገጽ ላይ የተጻፈ ማስረጃ አለኝ)።
የሚያስተዛዝቡ ንግግሮች ‘በድምፅ የተቀረጹ’ ንግግሮቻቸው እስካሁን ድረስ እኔ ጋር አሉ። አንድ ቀን አቀርበላችሗለሁ። “ትግሬ ብሎ ስለ አማራ ተቆርቋሪ” እያሉ እኔን ‘አያገባህም’ እያሉኝ የነበሩት ዛሬ ‘አማራ ፤አማራ’ እያሉ ሳደምጣቸው ጥሩ እርምጃ ቢሆንም ወደ ሗላ ተመልሼ ሳየው “የሰው ባሕሪ ምን እንደሆነ ግን ይደንቀኛል”።
አማራዎች በጉሙዝ “ሰው በሊታዎች” ተገድለው ‘ስጋቸው’ ተቀቅሎ ‘ሲበላ’ ፤ በዚህ አስደንጋጭ ዜና ተነስቼ “አማራ ምሁራንና ሌሎች ዜጎች ተነሱ ፤ ሕዝባችን ከመጠቃት አልፎ እየተገደለ ስጋው እየተበላ ነው” ብየ ስለ አስተጋባሁ እኔን በመዝለፍ “ውሸት ነው” “ጉሙዞችን ለመዝለፍ እና ኢትዮጵያን ለማዋረድ እንጂ ዜጎች ዜጎችን አይበሉም” እያሉ “አማራዎች ነን የሚሉ የኢሕአፓ አባሎች” እኔን እያዋረዱ “የአማራን ጥቃት ሊደብቁት ያልሞከሩት ነገር አልነበረም”። በዚህ ብዙ ዘለፋ ደርሶብኛል። ስለሆነም ዛሬም ሆነ ትናንት አማራው ሌላውን ከመውቀስ እራሱ መጠየቅ አለበት የምለው ለዚህ ነው!
ለ28 አመት ሲያንቀላፋ ብቻ ሳይሆን የአማራ እናቶችና አረጋውያን የድረሱልን “ድምጽ” እንዳይደምጥ እራሱ ምሁሩና ፖቲከኛው ሲያፍነው ነበር! ያውም “ድብቁ ኦነግ መረራ ጉዲና” ፤ “ኢንተርሃሙዌው በቀለ ገርባ” እና ‘ኦነጐችን’ እና ”ሓጂ ጃዋርን” እያንቆለጳጰሱ የአማራን ድምጽ ሲያዳፍኑ ነበር፡ ራሳቸው አማራዎች!! …… (Read more