July 15, 2019

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አቶ ተመስገን ጥሩነህን ዕጩ ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ ሲመርጥ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለውን የፓርቲው ምክትል ሊቀ-መንበር አድርጎ ሾሟል፡፡
ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደርነት በእጩነት የቀረቡት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከዚህ በፊት የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን፥በቅርቡም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል