July 15, 2019

“ለ150 ዓመታት ያክል ተቋርጦ የቆየው የፊንፊኔ/አዲስ አበባ የእሬቻ በዓል አከባበር በመጪው ዓመት በጨፌ እሬቻ መስቀል አደባባይ መከበር ይጀምራል። ”

የኦሮሚያ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ስለ ኢሬቻ በአል ብዙ የማውቀው ነገር የለም። ልጅ እያለው ቢሾፉቱ አንድ ዛፍ አለ፣ እዚያ ቂቤ ሲቀቡ እንደነበረ ትዝ ይለኛል። አሁንም ይቀባ አይቀባ ብዙ የማውቀው ነገር የለም። ኢሬቻ ኦሮሞዎች ብዙዎቹ ክርስቲያንና ሙስሊም ሳይሆኑ በፊት ፣ በገዳ ዘመን፣ ያመልኩት የነበረ አምልኮ እንደሆነ አንዳንዶች ይናገራሉ።00:11/01:03

አንዳንዶች ደግሞ ኢሬቻ የምስጋና ቀን ነው። ሙስሊሙም ለአላህ፣ ክርስቲያኑም ለእግዚአብሄር ፣ሙስሊምም ክርስቲያንን ያልሆነው ኦሮሞ ደግሞ እርሱ ፈጣሪ ለሚለው ምስጋና የሚያቀርብበት ቀን ነው የሚሉም አሉ።

አገር የጋራ ሃይማኖት የግል ነውና ፣ አምልኮም ይሁን አይሁን፣ የኢሬቻ ሆነ ማንኛውም ባእሎችን፣ የሌሎችን መብትና ነጻነት እስካልተጋፋ ድረስ፣ በማንኛውም የአገሪቷ ክፍል የማክበር ነጻነት የተከበረ መሆን አለበት። በመሆኑም ኣዲስ አበባ ኢሬቻን ለማክበር መፈለጋቸው በምንም መስፈርት ችግር ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም።

እንደውም በዚህ አጋጣሚ ብዙ ኦሮሞዎች አዲስ አበባ ይሄን በዓል ለማክበር ስለሚመጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፣ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች ጥሩ ቢዝነስ ሊሰሩ ይችላሉ። ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ከተማችን ሲመጣ ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም አለው።

በነገራችን ላይ ኢሬቻን በአዲስ አበባ ማክበር ልዩ ጥቅም አይደለም። እኩል ተጠቃሚነት ነው። ክርስቲያኑም በመስቀል አደባባይ መስቀልን ያከብራሉ። ሙስሊሞችን እንደዚሁ በዚሁ አደባባይ በአል አክብረዋል። ወንጌላዉያን በስታዲየም ኮንፍራንሶች አድርገው ያውቃሉ። ኢሬቻንም በአዲስ አበባ ማክበር ከሌላው እኩል መሆን ነው። እኩል ተጠቃሚነት ነው።

እኛ እኩል ተጠቃሚ እንሁን ሲሉ የምንደግፈው ነው። ችግራችን ልዩ ተጠቃሚ እንሁን ሲሉ ነው።