July 15, 2019
Posted by: ዘ-ሐበሻ
ከቅርብ አመታት ወዲህ የቡና ባህል በአፍሪካ እያደገ ነው፡፡ ምንም እንኳ አፍሪካ ለአለም ከሚቀርበው 13 በመቶ ብታበረክትም እና የቡና መገኛ አኅጉር ብትሆንም ከሌላው ዓለም ጋር ሲወዳደር የአፍሪካውያን ቡና የመጠጣት ባህል አሁንም የተፈለገውን ያህል አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ በስተቀር፡፡ በአፍሪካ ከሚመረተው ምርት አብዛኛው ለአለም ገበያ የሚቀርብ ሲሆን ከፍጆታ አንጻር ግን በጣም ትንሽ ነበር፡፡ አሁን ግን በመጠኑም ቢሆን ሁኔታዎች እየተለወጡ ነው፡፡
የአፍሪካ መንግስታት የሀገር ውስጥ የቡና ፍጆታን እያበረታቱ ነው፡፡ ለምሳሌ ካሜሩን «የቡና ፌስቲቫል» የሚል ሁነት በማዘጋጀት በሁሉም የመንግስት መ/ቤቶች ቡና መጠጣትን እያስተዋወቀች ነው፡፡
በደቡብ አፍሪካም ከፋስት ፉዱ እና ወደ ቤት ተወስደው ከሚጠቀሙበት መጠጦች ውስጥ በየአመቱ በአማካይ 2.8 የቡና ሱቆች ይሸፍናሉ፡፡ የቡና ኢንዱስትሪውም በአመት በአማካይ በ7.1 በመቶ እያደገ ነው፡፡ የቡና መጠጣት አብዮት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡
በናይጄሪያም ውስጥ የመካከለኛው ህብረተሰብ ክፍል እያደገ በመምጣቱ እ.ኤ.አ በ2010 እና 2015 በናይጄሪያ ቡና መጠጣት 20 በመቶ አድጓል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ በ2020 ናይጄሪያውያን 1000 ቶን ቡና ይጠጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንን ፍጆታ ደግሞ የናይጄሪያ የቡና ምርት አይሸፍንም፡፡ ይህንን እድል ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት ትችላለች፡፡ የአሜሪካ የግብርና ምርት መምሪያ እንደገመተው ኢትዮጵያ በ2019/20 በኢትዮጵያ 441ሺህ ሜትሪክ ቡና በማምረት ሪከርድ የሆነ ምርት በማምረት ኤክስፖርቱም ሪከርድ እንደሚሆን ተንብይዋል፡፡ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ማህበር መመስረቱም አስተዋጽዖ አለው፡፡
ከአፍሪካ አብዛኛው ቡና አምራች አገራት አንዷ የሆነችው ዩጋንዳም የአገር ውስጥ ፍጆታዋን በ20 በመቶ በአማካይ በማሳደግ ኢኮኖሚዋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ትችላለች፡፡ ዩጋንዳም የቡና ባለስልጣን የሀገር ውስጥ ፍጆታን ለማበረታታት ንቅናቄ ጀምሯል፡፡ ይህም በሳምንት ውስጥ 20ሺህ ስኒ በነጻ ማቅረብ ያካትታል፡፡
በጎረቤታችን ኬንያም መካከለኛው ህብረተሰብ እያደገ በመምጣቱ የኬንያውያን ቡና የመጠጣት ባህል ለማሳደግ እና ከሻይ ይልቅ ቡናን እንዲጠጡ ለማበረታታት የቡና ሱቆች በማስፋፋትና በማበረታታት የሸማቹን እምነት ለማሳደግ እየጣረች ነው፡፡
ይሁንና እነዚህ ጥረቶች ሁሉ በቂ ሆነው አልተገኙም፡፡ ከዚህ በመነሳት ከዳበረው የኢትዮጵያ ቡና የመጠጣት ባህል ልምድ ለመውሰድ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ የቡና ባህል ልምድ በመቅሰም እና ወደ ራሳቸው ለመውሰድ በሰኔ ወር በአዲስ አበባ መክረዋል፡፡
ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የቡና መገና አገር ብቻ ሳትሆን ለዘመናት የዳበረ የቡና ባህል ያላት አገር በመሆኗ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ በአማካይ ከምታመርተው የቡና ምርት ከግማሽ በላይ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ታውለዋለች፡፡ ይህ ልምድ የኢትዮጵያን ቡና ቀጣይነት ከማረጋገጥ አኳያ መልካም እድል ነው፡፡
በአፍሪካ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ ቡና የመጠጣት ባህል በመጠኑ እየጨመረ ነው፡፡ በከተሞች የቡና ሱቆች እየተስፋፉ ነው፡፡ የመካከለኛው ህብረተሰብ ክፍልም እያደገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና ኤክስፖርት ማደግ ከፍተኛ እድል ነው፡፡ የአለም የቡና ገበያ ዋጋ ወሻኞች ባደጉ አገሮች ትንሽ ቡና ቆዪዎች እና ድንበር ተሻጋሪ ኮርፖሬሽን ናቸው፡፡ ዋጋውን የሚወስኑት እነሱ በመሆናቸው የአለም አነስተና ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች ገቢ የምርት ወጪውን እንኳን የሚሸፍን አይደለም፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያን ቡና ይህንን ስጋት የመቋቋም እድሎች አሉት፡፡ እነሱም፤
- ኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው ልዩ ቡና / Speciality Coffeee ባለቤት በመሆኗ 2/3ኛውን ኢትዮጵያ ቡና ልዩ ቡና ተብሎ የመመደብ ብቃት አለው፡፡ ሸማቾች ደግሞ ለልዩ ቡና የተሸለ ክፍያ የመክፈል ልምድ እያዳበሩ ነው፡፡
- የኢትዮጵያ ቡና ከ90 በመቶ በላይ ኦርጋኒክ ተብሎ የሚፈረጅ መሆኑ ከሸማቾች ጤንነት ጋር ተያይዞ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱ እና የተሸለ ክፍያ እያደገ መምጣቱ፤
- « ፍትሀዊ ንግድ » የቡና ቀጣይነት በአለም በተዛባው የንግድ ስርዓት ምክንያት አነስተኛ ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች እየተጎዱ በመሆኑ ፍትሀዊ ንግድ ንቅናቄ አቀንቃኞች አነስተኛ አምራች አ/አደሮች የምርት ወጪያቸውን ለመሸፈን የሚያስችል እና ኑሯቸውን ለመግፋት የሚያስችል ሲስተም እንዲኖር አየጣሩ ነው፡፡ በሸማቹም ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፤ ቡና ጠጪዎች ቡናው የት እንደተመረተ፣ እንዴት እንደተዘጋጀ እና እንደታሸገ በማወቅ የተሻለ ዋጋ ለመክፈል ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡
ከቡና ምርት ጀርባ ያለው አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና የአካባቢ ጉዳዮችን ቡና ጠጪዎች በማወቅ የተሻለ ክፍያ ለመክፈል ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፤ በድርጊትም እየገለጹ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ይህንን ስለምታሟላ ለአ/አደሮቻቸው ምርጥ እድል ነው፡፡ ለዚህም ነው የሚቀጥለው አመት የቡና ጣዕም ውድድር ሀገራችን የምታስተናግደው፡፤
- የአፍሪካ ኢኮኖሚ ማደግ በአለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት አገሮች አብዛኛዎቹ ከአፍሪካ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ፡፡ በአፍሪካ ወጣቱ እና መካከለኛው የህብረተሰብ ክፍል በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ቡና መጠጣት በአሁኑ ሰዓት የሞደርናይዜሽንና ስልጣኔ ምልክት እየሆነ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቀን ከሁለት ስኒ ቡና በላይ መጠጣት የእድሜ ጣሪያን በ15 አመታት እንደሚጨምር ተረጋግጧል፡፡ እድሜ ጣሪያ ደግሞ ከፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል (HDI) አንዱ ነው፡፡ እያደገ የሚመጣውን የአፍሪካ ቡና ፍጆታ ደግሞ ሊሸፍን የሚችለው የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው የኢትዮጵያ ቡና ምርት ነው፡፤ ስለዚህ ፊታችንን ወደ አፍሪካ ማዞር አለብን፡፡
- የኢትዮጵያ ቡና መገና አገር በመሆኗ ጥሩ ገጽታ እና መልካም ስም አዳብሯል፡፡ ሸማቾች ደግሞ ከምርቱ በላይ ዋጋ የሚከፍሉት ለመልካም ስም ነው