July 17, 2019

እኔ የኦሮሞ ፖለቲካን ጉዳይ ከጅምሩም አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ ይሁንና እንደለማ የመሳሰሉ ሰዎች አንስተውት የነበረውን ብዝሐነት የመሰለኝ ነገር እኔንም እንደ ብዙሀኑ ኢትዮጵያውያን ሸውዶኛል፡፡ በእርግጥም እኔ ከለማ ውጭ ያለውን የኦሮሞ ባለስልጣን ሰው መግደል ሽንፈት ነው ሲል የነበረውን፣ አንድም ጋዜጠኛ የታሰረ የለንም እያለ ሲያወራ የነበረውን፣ በአጠቃላይ ዛሬ ላይ ከቃሎቹ በተቃራነው የምናየውን ሰውዬ ጨምሮ የምከታተላቸው በከፍተኛ ጥርጣሬ ነበር፡፡ አሁን ላይ ሁሉንም ማን እንደሆኑ እያየን ነው፡፡ ሰሞኑን በቅርብ በኦሮሚያ በፕሬዘዳንትነት የተሾመው ሰሞኑን ኢሬቻ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እናከብራለን አለ ተብሎ ወሬው ፌስቡኩን ሞልቶት አየሁ፡፡ እኔ ግን ማለት አለማለቱን አልሰማሁም፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ብሎ ከሆነም ብዙም የሚገርም አደለም፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ዓላማውን አሳምሩ አውቀዋለሁ፡፡
ኢሬቻ ምንድነው? ኢሬቻ የክርስትናውም የእስልምናውም የአይሁድም እምነት የሚቀበለው የእምነት ሥርዓት አደለም፡፡ ኢሬቻ መሠረቱ ምንም ይሁን ምን አሁን ያለበት ደረጃ ከክርስትናውም ከእስልምናውም እምነት የወጣ ራሱን የቻለ አምልኮ ነው፡፡ እንግዲህ በኦሮሞነት ብቻ ሳይሆን ሰዎች በእምነታቸው እውነትና እምነታቸውን ሊረዱ ይገባል፡፡ አሁን አሁን ኢሬቻን ከምስጋና ቀን ለማመሳሰል እየተሞከረች ያለችው ቁማር የሌሎች እምነት ተከታዮችን ለማታለልና ምን አለበት ብለው እነሱም በአላወቁት ጉዳይ የማይመስላቸውን እምነት እንዲተገብሩ የማድረግ ስልት ነው፡፡ ኢሬቻ ሐይማኖታዊ እንጂ ባሕላዊም አደለም፡፡ እምነቱ ደግሞ የእስልምናውም የክርስትናውም እምነት ከሚፈቅደው ውጭ በሆነ ሁኔታ የአምልኮት ስርዓት የሚከወንበት ነው፡፡ ስለዚህ የክርስትናም ሆነ የእስልምና እምነት አለኝ የሚል የዚህ አምነት ሥርዓት ተካፋይ የሚሆን ራሱን ባይሸውድ ጥሩ ነው፡፡
ማንም ሰው የወደደውን ሊያምን ይችላል፡፡ ሆኖም በሌሎች ላይ ግን የራሱን እምነት ሊጭን አይፈቀድለትም፡፡ ነውርና ይሉኝታ የሌላቸው የኦሮሞ ፖለቲከኞች በተደጋጋሚ በሌሎች አማኞች ላይ በዚህ መልኩ ሊጫኑ ሲሞክሩ ታይተዋል፡፡ ከዚህ በፊት ኢሬቻን በጥንታዊው ዝቋላ ገዳም እናከብራለን ብለው መግለጫ ማውጣታቸውን አስታውሳለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ከ150 ዓመት በላይ የተቋረጠብንን ኢሬቻ በመስቀል አደባባይ እናከብራለን የሚል ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ነውር የለሽ በበታችነት፣ በዘረኝነትና ጥላቻ እድሜ ልካቸውን ኖረው ዛሬ እድል ያገኙ ሁሉንም በኦሮሞነት ሊለውጡ ነው ምኞታቸው፡፡ መስቅል አደባባይ የክርስቲያኞች ሁሉ እምነት መገለጫ የሆነው የመስቀልን መገኘት ለማክበር የተዘጋጀ ቦታ ነው፡፡ ይሄ ቦታ ለማህበራዊ ግልጋሎት እንጂ ለሌሎች እምነቶችም አይውልም፡፡ መስቀል አደባባይን ለኢሬቻ የታሰበበት ዋና ዓላማው ለዘመናት ሲታገሏት የነበረቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነትን ትውፊት ለማጥፋት ነው፡፡ በዝቋላም ኢሬቻን እናከብራለን ብለው የነበረው ዓላማው ይሄው ነበር፡፡ እንግዲህ አስቡት ሲጀምር ኦሮሞ ስልጣን ይዟል ተብሎ መረን የወጣ የኦሮሞ ወረራ እየተካሄደ ነው፡፡ አብይ ኦሮሞ ስለሆነ ቤተመንግስት ኦሮሞን ጋበዘ፡፡ ይችን ያህል እንኳን አስቦ ቤመንግስቱ የሕዝብ እንጂ የኦሮሞ አለመሆኑን እንዳያስተውል አይቻለውም፡፡ የመንግስት መዋቅሮችን ያለነውር በኦሮሞ አጭቆ የምናየውን እውነት ውሸት ነው በሚል እየማለ ይክደናል፡፡ እምነት ለሌላው ቃልና መሐላ ቀላል ነው፡፡ አሁን ደግሞ ኢሬቻን ሕዝብ ላይ ለመጫን ዘመቻ ጀምሮብናል፡፡ የሌሎችን መኖሪያ ቤት ሳይቀር እያፈረሰ የእሱን እምነትና ባሕል ሊጭን ያስባል፡፡ ይሄ ነው የኦሮሞ ባለስልጣን አስተሳሰብ፡፡ ጉዳዩን ዛሬ በኦሮሞነት የሚያናፍሱት ክርስቲያንም ሆኑ ሙስሊም ለራሳቸው ሲሉ ቢያስቡበት መልካም በሆነ፡፡ የኢሬቻ አከባበር በባሕል ሽፋን እየተሰጠው ብዙዎች እምነት እያዘናጋ ያለ ነው በማያያውቁትና ለመኖር በሚል በግድ የኢሬቻ ተሳታፊ እየተደረጉ ነው፡፡ እስከዛሬ የተጭበረበረበት ይበቃል፡፡ የሕዝብን አሴቶችና እምነቶችን እየተጋፉ በሌላው ላይ የማይፈልገውን እምነት እየጫኑ ዝም ሊባሉ አይገባም፡፡ መስቀል አደባባይ ከእምነት ውጭ የሆኑ የሕዝብ አገልግሎቶች እንጂ ቦታው የመስቀል መከበሪያ ቦታ ነው፡፡ ኢሬቻን ከሆራ ወደ መስቀል አደባባይ ለማምጣት የታሰበበት ሴራ ምን እንደሆነ ዛሬ ካልገባህ ወደፊት ራስህንና እምነትህን ስታጣ አትረዳውም፡፡ ነገ ዝቋላም ላይ እነዳሉት የጥቅምቱን ገብረመንፈስቅዱስ ሳይሆን የመስከረም 22ቱን ኢሬቻ ልታከብር ትጓዛለህ፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ በአልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላል፡፡
ኢሬቻ መሠረቱ ምንም ይሁን ምን ዛሬ የሚደረገው አምልኮት ለክርትናውም ለእስልምናውም የማይሆን እንደሆነ አይንህ ያያል፣ ልብህ ይመሰክራል ግን በዘር አዘቅት ስለገባህ እምነትህን ሳይቀር ለመካድ ፍቃደኛ ትሆናለህ፡፡ ከዛ ባዶ ትሆናለህ፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ በአልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው እንዲሁ በአንተ ይተረጎማል፡፡ እውነትን (እግዚአብሔርን) ለማወቅ በአልወደድከው መጠን ለማይረባ አእምሮ ተላልፈህ ትሰጣለህ፡፡ አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተሰጠህ ደግሞ በምን ልታስብ ትችላለህ? እስከዛሬም ብዙ ያጣናቸው መሠረታዊ እሴቶች አሉን፡፡ በዛው ልክ የማንም ወሮበላ አስተሳሰብ ተገዥዎች ሆነናል፡፡ ዛሬ በእምነት ሥም ካራቴ የሚማቱን አእምሮህ እምነት ነው ብሎ እንዲቀበል ተገዷል፡፡ ዛሬ በዘረኝነት አይንህ የሚያየውን እውነት ክደሀል እምነትህንም ለውጠሀል፡፡ በኦሮሞነት ፍጹም ሌላ እምነትን የማይቀበለው ክርስቲያ በሉት ሙስሊም ዛሬ የኢሬቻ አምልኮት ፈጻሚ ሆኗል፡፡ ኢሬቻ እምነት እንጂ ባሕል አደለም፡፡ አተገባበሩንም እይ፡፡ ኢሬቻ በታንከስ ጊቪንግ ሽፋን የሚደረግለትም ስህተት ነው፡፡ በፈረንጆቹ የምስጋና ቀን ተብሎ የሚከበረው ሲጀምር ከመሠረቱ የክርስትና አማኞች አዝመራ አምርተው ምርታቸውን ሲሰበስቡ የሚያደርጉት ነው፡፡ እርግጥ ነው ዛሬ ዛሬ የመጀመሪያው አላማ እየተዘነጋ በደፈናው የምስጋና ቀን ተብሎ ይባላል፡፡ ቆይቶ እሱም ሌላ አምልኮ ላለመሆኑ ምንም ዋስትና የለውም፡፡ እንደሚገባኝ ኢሬቻም በዚህ ሂደት አልፎ ዛሬ ፍጹም ከአብራህም ልጆች እምነት እንደወጣ ነው፡፡ መሠረቱ ኦሮሞ ነን የሚሉት እንደሚያወሩት አደለም፡፡ የኦሮሞ ነን ባዮች አንዱ ችግር ደግሞ የታሪክ ጫፍን እንጂ መሠረትን በፍጹም እንዲታወቅ ሁሉ አይፈልጉም፡፡ ሌላው ቀርቶ በይፋ ተመዝግቦ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ከመሠረቱ ሳይሆነ ከሚኒሊክ ነው ሊጀምሩልን የሚፈልጉት፡፡ እንዲህ ያለ እውነትን የማይቀበል አእምሮ ነው እንግዲህ ዛሬ ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ታሪክና የሕዝብን እምነት፣ ባሕህልና እሴቶቹን ለማውደም እየሰራ ያለው፡፡
ስለዚህ ኢሬቻን ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ሌላ አምልኮ እንደሆነ ተገንዝቦ ከተሳተፈም በዚህ ግንዛቤ ሊሆን ይገባል፡፡ የእመነት አባቶች ስለዚህ ጉዳይ በይፋ ልትናገሩና ተከታዮቻችሁን ልታስገነዝቡ ይገባል፡፡ ይሄ የእምነት ነጻነታችን ነው፡፡ የፈለገ ኢሬቻ ማምለክ ይችላል፡፡ ባለማወቅ ግን እምነታቸውን እየተቀሙ ያሉትን የማደን ኃላፊነት የየእምነቱ መሪዎች ነው፡፡ የኦሮሞ መንግስት ፈጽሞ የሌላውን መብት ሊያከበር አይችልም፡፡ ነውር የማያውቅ 50 ዓመት በበታችነት ትርክት ሲያላዝን የኖረ በዘረኝነትና ጥላቻ የተበከለ ነው፡፡ ለዛም ነው ታሪክን ከመሠረቱ ሳይሆን ሁሉንም ሚኒሊክ ላይ የሚጀምረው፡፡ ሚኒሊክ ባይነግሱ ዛሬ ኦሮሞ የሚባል ነገር ራሱ ሊኖር ባልቻልም ነበር፡፡ እንኳን ኤሬቻ፡፡ የኦሮሞ ገዳን እንዴት ሚኒሊክ እንዳቆዩት ከዚህ በፊት ገልጬ ነበር፡፡ እውነቱ ይሄ ነው፡፡ የኦሮሞ ገዳ ዛሬ በኬኒያ በሚኖሩ ኦሮሞዎች አይተገበርም፡፡ በሙስሊም እምነት ተከታይ ኦሮሞዎችም አይተገበርም፣ ይተገበር የነበረው በሚኒሊክ ወዳጆች በነበሩት ቦረናና በተወሰነ በሸዋዎች ነው፡፡ የሚከተለውን ሊንክ ያድምጡ ከታሪክ ምሁራን https://streamable.com/bpkxt
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሁሉ ማንም የመረጠውን ሊያመልክ ይችላል፡፡ እኔ በአለሁበት የክርስትና እምነት ማንንም በግድ ክርስቲያን ማድረግ አይፈቀድም፡፡ ክርስትና አስተምረህ ማሳመንና ሲገባው እንዲከተለው እንጂ በግድ አይጫንም፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እያደረጉ ያሉትን በይፋ ልናወግዝ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱን አቋም ሊያሳውቅ ይገባል፡፡ ከዚህ በፊት በዝቋላ ኢሬቻ እናከብራልን ተብሎ የተሴረውን ሴራ ቀጥሎሞ በገዳሙ ላይ ጉዳት እንዲደርስ የተደረገበትን ሴራ አስታውሱ፡፡ የበታችነት ስሜት የወለደው ነውር የለሽነታቸው ዝቋላንም ኢሬቻ ይከብርበት ነበር ብለዋል፡፡ ዝቋላ ከጥንት ጀምሮ የቅዱሳን አባቶች ገዳም እንደሆነ ታሪኩን አጥተውት ሳይሆን ጥላቻቸው እውነትን እንዳይቀበሉ አድርጓቸዋል፡፡ እነዚህ ዝም እያሉ ማለፍ ብዙ ጥፋት መጋበዝ ነው፡፡ ከእንግዲህ ሁሉም በቃ ሊላቸው ይገባል፡፡ እነዚህ አምነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሊገባቸው አይችልም፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከሴረኞች ይጠብቅ! አሜን!