July 18, 2019 – Konjit Sitotaw
ጠ/ሚ አብይ አሕመድ ኤርትራ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ኤርትራ መግባታቸው ተሰማ። አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የ ኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት ተካሄደብኝ ካለው መፈንቅለ መንግስት እና ሕወሓትና አዴፓ ከተፋጩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አስመራ ሲጓዙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ ኤርትራ ቆይታቸው ሁለቱ ሃገራትን በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ሲሉ የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሕወሓትና በሻእቢያ መካከል ድርድር መጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን የምሁራንም ቡድን ድርድሩን ለማጠናከር የውይይት መድረክ መጀመራቸው ይታወሳል። እንዲሁም ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡ ድንበሮችን መዝጋቷ ሲታወስ ስለመከፈት አለመከፈቱ ኤርትራ ምንም አይነት መረጃም ሆነ መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኗ ይታወቃል።