July15/2019

ዶክተር ደረጀ ዘለቀ ከላይ በተጠቀሰ ቀን  ለአንድ አፍታ ሚዲያ አስተናጋጅ  በአቶ ስዩም ተሾመ’ ቃለመጠይቅ ወይም ኢንተርቪዩ የተደረጉበትን የድረገጽ አገናኝ ወይም ሊንክ  ከፌስቡክ ተጋሪዮቼን አንዱ ልኮልኝ ከአንዴም ሁለቴ አእምሮዬን  ሰብስቤ አዳመጠኩት ። ዶክተሩ ለቃለመጠይቆቹ  በሰጥዋቸውን  መልሶች ‘የተሰ    ማኝን ቅሬታ’  ወዲውኑ መልስ መስጠት ብፈልግም የግዜ ሁኔታ አልፈቀደልኝም ። ለሁሉም ነገር ግዜ አለውና  ሊንኩን  ካገኘሁት ከአራት ሳምንታት በኋላ  ከበርካታ የዶክተሩን  ስህተቶች ለቱባ ቱባ ጥቂቶችን  በሚከተለው ሁኔታ ማለት በመነጠብ ለአንባቢያን አሳያለሁ  ወይም አስጨብጣለሁ ።

1) ‘በቀሽብር አምስት መቶ ሺ[500 000] ሰዎች ቢሞቱ ኖሮ ወያኔ የተከለው ችሎት በጥቂት ሺዮች ሞት ክስ ታጥሮ አይቀርም ነበር’ ያሉትን በተመለከተ  ፦ ህወሃት በቀይ ሽብር ለተረፈረፉትን ኢሕአፓዎች ያዘነ ይመስሎታልን? በአካል ሳይሆን በአስተሳሰብ የወያኔዎች ወደል ውሻ[top dog] የነበረው መለስ ዜናዊ የፋሽስቱ መንግሥቱን ዙፋን ላይ ከተቀመጠ በኋላ የሥልጣን ጫጉላውን እስኪያረጋጋ ወያኔ እንኳን መጣልን የሚያሰኙ ፣ የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ተስፋ የሚሰንቁና በጎ የሚመስሉ ነገር ግን መሰሪ የሆኑ ትእይንታዊ[ዲሞንስትሬትቭ ፖለቲካ እንደሰራ በወቅቱ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ግልጽ ነው ።

የአጼ ሃይለሥላሴና የቀይሽብር ሰማዕታትን አጽም አስቆፍሮ ቤተሰብ፣ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ አስለቀሰ ፣ እኡ አስኘ።የአደባባይ ፖለቲካ ፣ [የመጻፍ የመናገር፣የመደራጀት፣ የመሰብሰብ  የሚዲያ]  ወዘተ..ነጻነቶች ፈቀደ፤ እንደልባችሁ ለፍልፉ  ፈንጩ  አለ ። በቀይሽብር ወንጀል ተጠያቂዮችን  የፍርድ ችሎት መሰየም  እላይ ከጠቀስኳቸው የማታሌያ ቴያትሮች አንዱ ነበር ።

   ወያኔና ኢ ሕ አ ፓ እሳትና ጭድ ነበሩ ናቸውም፣ ለምን? ስለምን?

ሀ) ሥውር የወያኔ አባሎች ደርግን ደጋፊ በመምስል  በካድሬነት ተቀጥረው በቀሽብር ግዲያ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል

ለ) ወያኔ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር የሚፈታው በብሄር ተከፋፍሎ በመተዳደር ነው፣ አንድ ሉዓላዊ ኢትዮጵያ የሚባል ነገር የለም ወይም   አንቀበል ሲል – ኢ ሕ አ ፓ የኢትዮጵያ አገራዊ (ኢትዮ-ብሄራዊ) ችግር መፈታት ያለበት የብሄር በሄረሰቦች እኩልነትን በሰፈነበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት -አንድ ኢትዮጳያ አንድ ሕዝብ በሚል መተክል (principle) በመሆኑ/ስለሆነ 

ሐ)  (1) የ60ዎችና የ70ዎቹ የለወጥ ታጋዮች የታገሉላቸውን የለውጥ ራዕ ዮቻቸውን መልስ ሳያገኙ በባሰ አፋኝ ሥርዓት መዳፍ ሥር ማለት በፋሽስቱ መንግሥቱ በተመራው ደርግ በመቀማቱ (2) ከዚያው  ከ60ዎችና ከ70ዎቹ  የለውጥ ታጋዮች  የተወለደው ኢ ሕ አ ፓ – ህጋዊ ኅልውና አግኝቶ  በአገሩ ምድር በሰላማዊ መንገድ እንዳይታገል በመከለከሉ  አባሎቹ ከየትኛውም የአገራችን ከተሞችና ገጠሮች ታድነው ይታሰሩና  ይረሸኑ ወዘተ.. ስለነበረ  ደርግን በጠመንጃ አፈመዝ ተፋልሞ የተነሱበትን ዓላማ እውን ለማድረግ  የኢሕ አ ፓ የትጥቅ ክንፍ ኢ ሕ አ ሠ በትግራይ ክፍለ ሃገር ወደ ሚገኘው ወደ አሲምባ ተራራ ሄደው መመሸግ  በወያኔዎች ስለአልተደገፈ ከትግራይ ምድር ውጡልን በማለት በኢ ሕ አ ሠ ላይ አፈሙዝ መዘዙ ። ኢሕ አ ሠም የአጸፋ አፈሙ በመምዘዙ  የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ገቡ ፣ደም ተቃቡ ።  

መ) ደም መቃባቱን  በዚያ  በአሲምባና በአካባቢዩ አላበቃም ፣ በወልቃይት ምድር፣ በቋራ ወዘተ.. ሁለቱም በደፈጣ ውጌያ ተጠዛጠዙ

ሠ) በ1983 ወያኔ የኢትዮጵያ በትረ-መንግሥት በጨበጠ ማግሥት በጣም ከፍተ       ኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት አሰልፎና በሱዳን መንግሥት ወታደሮች ታግዘው ማለት ወደ ሱዳን እንዳያፈገፍጉ በር በመዝጋት ፤ በቋራ ምድር መሽገው ይዋጉ ከበሩት የኢ ሕ አ ሠ ተጋዳዮች ውስጥ ማርኮ የወሰዷቸውን እስካሁን የት እንዳደረሷችው አይታወቅም    

ረ)  ወያኔዎች  የአገራችንን ሥርወ መንግሥት ከተረከበበት ግዜ ጀምሮ -አገር ቤት የነበሩትን  ኢ ሕ አ ፓዎች እንደ ውሻ እያነፈነፈ ገደሏቸው፣ አሰሯቸው፣ ከሥራ አስወጧቸው ፣  ከአገር ውጭ ያሉትም ወደ አገራቸው እንዳይመለሱ ከለከሏቸው /አገዷቸውወዘተ..

ሰለሆነም ወያኔ በምንም ተዓምር በኢ ሕ አ ፓዎች ላይ የተፈጸመን የገፍና የግፍ ግዲያ ተቆርቁሮና አዝኖ – ሃቀኛ/እውነተኛ የፍርድ ችሎት ሰይሞ አላስቻለም ፤ሊያስ      ችልም አይችልም። ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውና ዘመዶቻቸውን       በተረሸኑባቸው  ቤተሰቦች አቤቱታ በጥቂት የቀይሽበር  ወንጀል ተጠያቅዮች ላይ ለይስሙላ ፍርድ አስፈረዶ ይሆናል ፤ ያዞ እምባ ይሉታል ይህ ነው ። ከላይ የጠቀስኳቸውን ማስረጃዎች ሁሉ እንድጠቅስ  የተገደደኩት  ዶክተር ደረጀ ‘በቀይሽብር አምስት መቶ ሺ[500 000] ሰው ቢሞት ኖሮ ወያኔ የተከለው ችሎት በጥቂት ሺዮች ሞት ክስ ታጥሮ አይቀርም ነበር’ ያሉትን  ተሳስቷል! እነዚህን ማስረጃዎች ይመልከቱ ! ለማለት ነው ።

ፀረ-ሕዝብ ደርጎችና ካድሬዎቻቸው   ‘በያንዳንዱ የደርግ ደጋፊዮች ሞት ሺ[1000] ኢ ሕ አፓ ዎች እንገላለን’ ! ብለው በሬዲዮ፣ በተሌቪዥን፣ በአድስ ዘመን ጋዜጣ፣ በመፈክሮች ወዘተርፈ  አላሳወጁምን?  አላቅራሩምን ? አልፎከሩምን? ሂትለር የአንድ ጀርመናዊ ወይም የአርያን ሞት በመቶ (100) ስዎች ግድያ እንበቀለዋለን ነበር ያለው ፤ የመንግሥቱ ሃ/ማ ጭካኔ ከሂትለር በአስር እጥፍ የከፋ ነበር ማለት ነው።

ከተለያዩ የሰባአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የቀረቡትን ጭብጥ ማስረጃዎች የሚያጣፋ (rebut or disprove) የሚያደርግ ማስረጃ ሳያያቀርቡ በግምት ወይም በሃሳባዊነት  በቀይሽብር [500,000] አልሞተም ብለው ሲሟገቱ  እኚህ ዶ/ር (David John Cawdell Irving) ነው የመሰሉኝ ።

 በ(1941 -1945) በነበረው  ግዜ  ከአምስት እስከ ስድስት ምልዮን የሚደርሱ ነገደ እስራኤሎች በሂትለር መራሹ ናዚዮች  – የዘር ምንጠራ ወይም [Holocaust] እንደ ተፈጸመባቸው ታሪክ ይመሰክራል ። ያ የጅምላ ግዲያ (mass extermination) የተፈጸመው  በዋናነት (Asphyxiant) የሚባል በጣም መርዛማ ጋዝ በማጠን እንደ ነበር ታሪክ ይናገራል ። ድርጊቱ  የተከናወነው (Auschwitz) በሚባል በደቡብ ፖላንድ የኢንዱስትሪ  መንደር ነው ።

ባጭሩ (David Irving) የተባሉ እንግሊዛዊ የታሪክ ተመራማሪ፣ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት (World war two) በተሰኘው  መጻፋቸው ፦                            — ናዚዮች ያንን ያህል ቁጥር ያላቸው እስራኤላውያን አልገደሉም                              – የገፍ/ማስ  ግድያው  በሂትለር ትእዛዝ አይደለም                                    – በ (Auschwitz Concentration Camp) በመርዛማ ጋዝ ታጥኖ ተገደሉ የሚባል ነገር ውሸት ነው  ብለው  በመጻፋቸውና በመሟገታቸው  ‘የሆሎኮስት ከሃዲ’  (Holocaust denial) በመባል ተውገዙ ፣ ፍርድ ቤት ቀረቡ ፣በታሪክ ማህደር ተጻፉ ወዘተርፈ ። ስለሆነም ዶ/ር ደረጀ የቀይሽብር ተመን ከሃዲ ይባሉ/እንበላቸው ወይስ ሌላ ?

2) ‘ዛሬም ‘በስልጣን ላይ ሆኖ የዚያ ትውልድ

ተራፊ ስለሆኑ ገድላቸውን ያወራሉ ያሉትን’ በተመለከተ ፦ዶ/ር ደረጀ ይህ ሃሳብ የሰነዘሩት ስለቀይ ሽብር ከተጠየቁት ጥያቄ ጋር በማያያዝ ነው ። ያ ማለት በወያኔ መራሹ የኢህ አድግ አገጋዝ -ኢሕ አፓዎች የሥልጣን ድርሻ አላቸው ማለታቸው ነው ። ማኅበረሰባችን በተለይም አዳማጮቻቸውን ማሳሳት (mislead) ማድረግ አይ   ሆንምን?

 ለመሆኑ የትኛው የወያኔ  ባለሥልጣን ነው በቀይሽብር ‘ስለተጨፈጨፉትን’ ዜጎች ተቆርቁሮና አዝኖ ሲያወራ ወይም ሲሟገት የሰሙት ? በቅጡ ሳያላምጡ መዋጥ ጉረሮ ወስጥ  እንደሚቸነከል ሁሉ ሳያስተውሉ ወይም ሳያገናዝቡ ማውራትም ስተት ላይ ይጥላል ።ባጭሩ ከላይ በቁጥር አንድ  ከ(ሀ—ሰ) የነጠብኳቸውን  ማስረጃዎች መልሰው እንዲያይዋቸው አሳስባቸዋለሁ ። ይልቅስ ከወያኔ ጋር አማካሪ እስከመሆን  የተሞዳሞዱት የደርግ ባለሥልጣኖች  ናቸው ።

3) ‘ተኩስ ከግራና ከቀኝ ይመጣ ነበር ፣ ከደርግ በተጻራሪ የተሰለፉት [near anglic]ለመላክትነት የተጠጉ  አልነበሩም ፤በአራጅ ወታደሮችና በታራጅ ንጹሃን ወጣቶች መካከል የተደረገ ግብግብ አድርጎ ማውራት፤ከሱማሌና ከሻቢያ ጋር ወደ ተደረገው ጦርነት በግድም በውድ ተልከው ስለሞቱት ሺዎች ወገኖቻችን ለምን አይሰማንም’ ያሉትን አስመልክቶ ፦ ይህ ጅምላ ትርክት በታትኖ  ማስጨበጥ ወይም ማስረዳት  ያስፈልጋል ።

*   የአንድ አፍታ ሬዲዮ አስተናጋጅ ዶ/ር ደረጀን ስለቅይሽብር ሲጠይቋቸው በውድም ሆነ በግድ  ወደ ጦር ግንባር ተልከው ዳር ድንበራችንን ላለማስደፍር  -ከዚያድ ባሬ ወራሪ ጦር ፣ ከአገር አስገንጣዩ የሻቤያ ጦር፣ ለትግራ ሪፐብሊ ይዋጋ ከነበረው ጠባብ ብሄርተኛ ወያኔዎች ወዘተ.. ጋር ሲተናነቁ በጠላት ጥይት የረገፉትን ለብዙ መቶ ሺዎች ወገኖቻችን- አንዘን ፣ አናልቅስ፣ አናስታውሳቸው  ወዘተ.. ከሚል መንፈስ አልመሰለኝም ።

 እንኳንስ የቅርቡን- በተለያዩ ቀደምት ታሪካዊ ወቅቶች ፣ ብቅኝ ያልተገዛ ነጻ አገርና ነጻ ሕዝብ  እንዲኖረን  ከባዕዳን ጦር ጋር ሲትናነቁ የረግፉትን የአባቶቻች  ንን ፣ የአያቶቻችንን ፣የቅድመ አያቶቻችንን  ትውልድ  ጀግኖቻችን ስናስባቸው፣ ስንዘክራቸውና ስንኮራባቸው  ኖረናል ፤ቀጣዩም ትውልድ ሲዘክራቸውና ሲኮራ ባቸ ይኖራል ።የእኔም አባት ከፀረ-ሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ጀግኖች አንዱ ነበር።

የአንድ አፍታ ሬዲዮ አስተናጋጅ መጠየቅ የፈለገው  በፋሽስቱ  መንግሥቱ በተመራው  በደርግ የአገዛዝ ሥርዓት  በፀረ- ሕዝብ ካድሬዎች ማለት በወገን ጥይትና ሰቆቃ ስለተረፈረፉትን ወገኖቻችንን ነበር ።

 የዜጎችን ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ሰባአዊ መብቶች ይከበሩ በማለት መፈክሮችን ይዘው በአደባባይ መንግሥትን ወይም ገዥዮችን የሚለምኑና የሚማጸኑ ሲቪል ዜጎች ከሞያተኛ ሠራዊት ወይም ወታደር ጋር ሲታኮሱ የታየው በየትኛው አገር ዋና ከተማ ነው?

 በዘመናዊ  ትምህርት ዓይናቸውን የከፈቱ፣ ከሰፊውና ካልተማረው ሕዝብ የተሻል ማኅበራዊና በፖለቲካዊ ንቃተ-ኅሊና የነበራቸው የዘመኑ ለውጥ ፈላጊዩ ሃይል በተለይም ወጣቱ- እንደ ‘መንጋ ከብት ወይም እንደሚናገር እንስሳ  አትቁጠሩን! አትግዙን!  እንደሰው  እንደዜጋ ግዙን/ አስተዳድሩን! ግዴታችንን ብቻ አትጠይቁን’!  በማለት በጡጫና በድንጋይ ከሥርዓቱ ነፍስ ገዳዮች ጋር ተፋልሟል፤ተናንቋል። ያንን ድርጊት ወጣቶች  ከወታደሮች ጋር ተታኩሷል የሚያሰኝ ኮሆነ ይህንን ጽሁፍ አንባቢና ታሪክ ይፍረዱ ።

በርግጥ የተለያዩ ዘመናዊ መሳርያዎች  እስከ አንፍጫቸውን የታጠቁ ፀረ-ሕዝብ ካድሬዎች እንደውሻ እያነፈነፉ ኢሕ አፓዎችን መውጫ መግቤያ ሲያሳያጧዋቸውና ሲጨፈጭፏቸው –  ለኅልውና ባልሞትባይ ተጋዳይነት    ጥቂት ጥይቶች ተኩሰው  ጥቂት ፀረ-ሕዝብ ካድሬዎችን ገደሉ፣ ጥቂቶቹን አቆሰሉ ። ከላይ እንደ ጠቀስኩት ደርግ በያንዳንዱን ካድሬዎቻቸውን ሞት በ1000 ኢ ሕ አ ፓዎች ግድያ ተበቀለ ።  ያንን በመሰለ የጅምላና የተናጥል  የበቀል ግዲያ ነው 500 000  ኢ ሕ አ ፓዎች የተመተሩት።          

በዚያ ባላልቅ ባይ ወይም ባትፍጁን ባይ ተጋዳይነት በጥቂት ጠላቶቻቸ ውን ላይ በወሰዱት የግዲያ እርምጃ ምክንያት ያንን  ያህል  ኢሕአ ፓዎች በተለይም ወጣት ኢሕ አፓዎች በመጨፍጨፋቸው ፤ ኢ ሕ አ ፓ እንደ ድርጅት ስህተቱን አምኖ በቃልም በጽሁፍም በተደጋጋሚ ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ  ይቅርታ ጠይቋል።    

  [ገዢና ተገዢ፣ በዝባዥና ተበዝባዥ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ] ወዘተርፈ  ተከስቶ ማኅበረስብ በመደብ ከተክፋፈለበት  ታሪካዊ ወቅት ጀምሮ ከአምባገነን ፀረ-ሕዝብ  ገዢዮች ጋር ተሰልፈው የሰፊውን ሕዝብ ወዳጆችና አጋሮችን እያሳደዱ [የሚጦቆሙ ፣የሚያስጦቆሙ፣የሚገረፉ፣ የሚያስገረፉ፣ የሚገሉ፣ የሚያስያገደሉ] የገዢዮች መሳርያዎች ፤ በየትኛ  ውም  ማኅበረሰብ  አይወደዱም  አዘከሩም።

በተመሳሳይ ከደርግ ጋር ስልጣን ለመጋራት፣ የተሻለ ደሞዝ ለማግኘት፣ውስኪ ለመጠጣት፣ ጮማ ሥጋ ለመብላት፣በውጤታቸው ሳይሆን በፀረ- ሕዝብነታቸው ለከፍተኛ ት/ም  ወደ ሶሻሊስት አገሮች ለመሄድ በአጠቃላይ [ለስልጣንና ለተሻለ ቁሳቁሳዊ ሕይወት] ሲሉ ለሰፊው ሕዝብ መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት ይታገሉ የነበሩትን ለጋ ወጣቶችን፣ጎልማሶችን፣አዛውንቶችን  አሳደው፣የጦቆሙ ፣ ያስጦቆሙ፣  ያሰሩ፣ ያሳሰሩ፣ የገረፉ፣ ያስገረፉ፣ የገደሉ ያስገደሉ  የደርግ መሳርያዎች  የነበሩትን ይታወሱ ፣ ይዘከሩ ከተባለም ከዚያ ከተግባራቸው አንጻር ሳይሆን  በስባአዊነት አይታዘንላቸው  አልልም ።                                                      

ከደርግ ጋር ተሰልፈው ከነበሩት አብዛኞቹ ቱባ ቱባ ካድሬዎች የተመነጠ ሩት በራሱ በደርግ እንጂ በተጻራሪያቸው አይደለም ። ፋሽስቱ መንግሥ  ቱ እንደ እረኞች አርጩሜ ሥልጣኑ እስኪያጠናክር ከተጠቀመባቸው በኋላ -ሥልጣኑን  ይጋፉኛል ብሎ የጠረጠራቸውን  ሁሉ መልሶ በላቸው/ፈጃቸው ። አስቀያሚና እርቃሽ ሞት ማለት ይህ ነው።

   በ17ቱ  የመንግሥቱ ሃ/ማ ፋሽስታዊ አገዛዝ ዓመታት (በቀይሽብር ፣ በተለያዩ                  የጦር ግንባሮችና  አገልግለውት መልሶ በገደላቸው ካድሬዎች ወዘተ..)  ምክንያቶች ሞት ያልገባበት የኢትዮጵያውያን ቤት ነበረ ለማለት እጅግ በጣታም ያስቸግራል ። በያንዳንዱ ቤት ባይሞት እንኳን ፣ አንድ ወይም ሁለት ሰው ያልሞተበት ቤት፣ ቤተሰብና ቤተዘመድ (አጎት፣አክስት፣የአጎት ልጅ፣የአክስት ልጅ፣ የአጎት የልጅ ልጅ፣የአክስት የልጅ ልጅ ወዘተ.. )ያልሞተበት የለም። በቀይሽብር ስድስት ልጆቻቸውን ያጡ ወላጆች ነበሩ።

የሶስት እህትማማቾች ምስል/ፎቶግራፍ መስቀል አደባባይ አካባቢ ባለው የቀይሽብር ሰማዕታት አዳራሽ ግድግዳ ላይ ጎን ለጎን ተለጥፈው ይታያሉ ። መንግሥቱ ወጣቱን ብቻ አይደለም የጨፈ ጨፈው ። የነቁ ዲሞክራት (ሠራተኞችን የሠራተኛ ማኅበራት መሪዮችን፣ መምህራንን፣ የመምህራን ማኅበ ራት መሪዮችን፣ ወታደሮችን፣ ወታደራዊ መኮነኖችን፣ አርሶ አደሮችን ፣ጎልማሶችን ፣አዛውንቶችን ወዘተርፈ) ጨፍጭፏ ። በሠፈራችን ዳቦ ጠፋ፣ ስኳር ጠፋ ወዘተ..ሲሉ በቀበሌ ካድሬዎች የተደመጡን ሁሉ በፀረ-አብዮተኝነት ተረሸኑ ።    ወያኔዎች በኢትዮጵያ የመንግሥት ሥልጣን መጨበጥም ሆነ የኤርትራን መገን   ጠል ተጠያቂ መንግሥቱ ሃ/ማ ነው ፤ ሁለቱም መንግሥቱ ለኢትዮጵ ሕዝብ  ያበረከታቸው ስጦታዎች ናቸው ።  

4) ‘የቀድሞ ተማሪዮች ንቅናቄ – የተመረዘ ፣ሌላኛውን ጽንፍ የረገጠ፣አገር አዋራጅ ፣ (nihilistic) ማለት ደምሳሽ ፣ ሥርዓት አልባ ፣ ቁንጽል ንቃት፣ ግልብ ወዘተ..የፖለቲካ ባህሪ የነበረበት ነው ፣ ከደርግ በተጻራሪነት የተሰለፉት (near angelic) ለመላዕክነት የተቃረቡ ንጹሃን አልነበሩም፣ ደርግን የተቃወሙት ጻድቃን አድርጎ መቁጠር’ ብለዋል ፦ ይህ አባባላቸው በደንብ ስነጣጥቆ መፈተሽ ያስፈልገ።

በእርግጥም የ60ዎችና የ70ዎች ለውጥ ፈላጊ አርበኞች  (አገራችንን፣ ሉዓላዊነታ ችንን ፣ ታሪካችንን፣ ባህላችንን፣ቋንቋችንን ፣ ልማዳችንን፣ሃይማኖታችንን  ወዘተር.. ) ለማጥፋትና ለመደምሰስ የተሰለፉና የተነሳሱ ነበሩን? የኦዲት ጉዲትን፣ የግራኝ መሃመድን፣የሞሶሎኒን  ወዘተ. .ዓይነቶች ተግባር ለመፈጸም የተዘጋጁ ነበሩን?

ለምን ነበር የታገሉት? ለምን ነበር ለዚያ ሁሉ ሰቆቃ የተጋለጡት? ለምን ነበር በእስር የማቀቁት?  ለምን ነበር ለዚያ ሁሉ እልቂት የተዳረጉት? ምን ስለፈለጉ?  የቅንጦት ሕይወት አምሯቸው  ነውን?  ወዘተ..ብሎ መጠይቅ ያስፈልጋል ።

ሕዝባችን- ተርቧል፣ ተጠምቷል ፣ታረዟል ፣በረንዳ አዳሪ በዝቷል ፣ለማኝ በዝቷል ከላይ እንደጠቀስኩት እንደ ሚናገር እንሣ አትግዙን፣ የህግ የበላይነትና ማኅበራዊ ፍትኅ የለም ፣ የመሬት ባርነት ይቁም! መሬት ላራሹ ይታደል! ትምህርት ለሰፊው ሕዝብ ይዳረስ! በአደባባይ የመሰብሰብና የመወያየት ነጻነት ይኑረን! (ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ሰባአዊ መብቶች) ይከበሩ!  የብሄር ብሄረሰቦች ማንበትና ባህሎች   በዕኩልነት ይስተናገዱ!  አገራችንና ሕዝባችንን ያፈሩትን ሃብት-የሚኒስት  ሮች፣ የመኳንንቶች እና የንጉሳውያን ቤተስቦች ብቻ መንደላቀቄያ አሁን!         እናቶቻችንና እህቶቻችን በሥርዓቱና በወንድ ትምክህተኝነት የሚደርስባ   ቸውን ጭቆናና ጥቃት ይቁም! አገራችን ኢትዮጵያ ከጥንታዊ አገሮች አንዱ       ቢሆን አልዘመነም (በኢንዳስትሪ፣በቴክኖሎጂ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በኮምኒኬ ሽን ፣ በሳይንሳዊ ምርምር )ወደ ኋላ ቀርቷል፣ እድገታችን ታቅቧል ወዘ ተርፈ  ፤ ስለሆነም  እነዚህን ችግሮችን ማስተናገድ የሚችል ዲምክራሲያዊ ሕዝባዊ መንግሥት እና በሕዝብ የተመረጠ መሪ ያስፈልገናል በሚል ነበር ትግሉ ።

በመሆኑም -ከላይ ለተጠቀሱትን  እውነታዎች መታገለ ግልበኝነትና ቁንጽልነት ነውን? ለእነዚህ ተጨባጭ ሃቆች መታገል ሥርዓት አልበኝ   ነትን? እነዚህን ችግሮች ይፈቱ ብሎ መጮህ ሌላኛውን ጽንፍ የረገጡ ያስብላለን? እነዚህን የሕዝብ ጠንቆችና የአገር ስልጣኔ ጎታች ሥርዓቶች ይሻሻሉ/ይወገዱ ብሎ መታገል  አገርና ሕዝብ ደምሳሽነት ነውን? እነዚህን ችግሮች መፍትሄ ይፈለግላቸው ብሎ መጮህና መንግሥትን መማጸን  አገር አዋራጅ መሆን ነውን? ከፀረ-ሕዝብ የመንግሥት ሥርዓትና ከፀረ-ሕዝብ ገዢዮች መታገል መርዛማና ወደ ውጭ መመልከት ነውን ?የትኞ       ቹ ጻድቃን ናቸው ለኢትይጵያ ሕዝብ መከራ የሞቱት? የትኞቹ መላዕክት    

ናቸው ያንን እልቂት ይብቃ ብለው መንግሥቱን ያወገዙት?

ተፈጥሮ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱትን ብልሹ የመንግሥት ሥርዓትች የጫነባቸውን ከማኅበረሰባቸውን ጫንቃ ለማውረድ ሲታገሉ  (በእስር የማቀቁትን፣ የተገረፉትን ፣ ሰቆቃ የደረሰባቸውን እና የተሰውትን) እውነተ     ኛና ሃቀኛ የሕዝብ ልጆች ስለሆኑ ክብር ይገባቿል፤ከመላዕክትም መላዕክት ከጻድቃንም ጻድቃን ናቸው ።

 የመጠቀ ብርሃነ ኅሊና (Enlightened consciousness) የነበራቸው፣ ለማኅበረሰባቸውን ፍትህና ነጻነት ሲሉ (የታገሉ፣ የታሰሩ፣የተገረፉ፣ ሰቆቃ የደረሰባቸውና የተሰው ዜጎች ነበሩ/ናቸው እንጂ ዶክተሩ እንዳሉት በግልብነትና በቁንልነት ንቃተ-ኅሊና የተነዱ አልነበሩ።(መታሰር ፣መገረፍ፣ መሰቃየትና  መሞት በክብር! !) ይሉታል ይህ ነው ።     

“The difference between a flower and a weed is a judgement”                          (Susan Hayward) በአበባና በአረም መካከል ያልው ሊዩነት በመዳኘት ላይ ነው- ወይም እንደ እይታችን ነው ማለት ይመስልኛል ። “ለነቃ ኅሊና  ሕይወት አስቸጋሪ ነው”(አና ፍራንክ)

“Great spirits have always encountered violent opposition from mediocre minds” (Albert Ernestine). ትላልቅ አስተሳሰቦች  ሁልግዜ

በጠበኛ ተቃዋሚ – ተራ አስተሳሰቦች ይታወካሉ/ይደናቀፋሉ ወይም ትላልቅ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ሁልግዜ ተራ አስተሳሰብ ባላቸው ጠበኛ ተቃዋሚዮች ይቸገራሉ/ይደናቀፋሉ እንደ ማለት ይመስለኛል ። የአንድ እስረኛን ስሜት ለማወቅ እሱ በታሰረበት ሁኔታ መታሰር ያስፈ  ልጋል ።የአንድ የተራበን ስው ስሜት ለመረዳት እንደ እሱ መራብ ያስፈል ገናል ወዘተርፈ ።

5) ‘ሮማውያን ገዢዮች ባሬዎቻቸውን ከአውሬዮች ጋር ያፋሉሟቸው      ነበር ፣ የያኔ የተማሪዮች ንቅናቄ የነበረውን እውነታ የሚጻረር ነበር፣ በዶክተሩ ቋንቋ   (“the negation of the existing reality”) ነበር ፤ ስለሆነም አገር አዋራጅና ቂም ቋጠር ነበሩ’ አሉ ። ያ ማለት የ60ዎችና የ70ዎች የኢትዮጵያ ገዢዮች ባሬያዎቻቸውን ከአውሬዎች ጋር እያታገሉ አልነበሩም ። በመሆኑም  የያኔ የአገራችን  ታጋዮች ነባራዊ ሁኔታዎችን ግድ ብሏቸው (የመብቶችና የፍትህ እጦትች ኖሮ፣ ጭቆናና ግፍ) ሰፍኖ ሳይሆን አገርና ሕዝብ ለማዋረድና ለመበቀል ነበር የተነሳሱት ባይ ናቸው። በሮም የዚያ ዓይነት ሥርዓት የነበረው መቼ ነበር?  ያ ግፍ ምን አስከተለ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ።

 ከ264 ዓ.ዓ  እስከ የመጀመርያዎቹ 5 ምዕተ ዓመት (264 B.C –early 5 century A.D) በነበረው ግዜ የሮማውያን ገዢዮች ወይም አጼዎች በመጀመርያ ባሮችን ፣ በመቀጠልም  ወንጀለኞችን የውንጀላቸውን መቀጣ ጫ ከአንበስዎችና ከነበሮች ጋር ያታግልዋቸው ነበር። እንደ እስፖርት ይቆጠር ስለነበረ የስፖርቱ ስም ግላዲያተር <gladiator> ሲሆን የስቴዲዮሙ ስም ኮሎሲየም <Colosseum> ይባል ነበር ። የተጀመረው (Decimus Junius Brutus Scaeva) በተባለ አጼ ነው ። የአጼዎች/የገዢ  ዮቹ ፣የቤተሰባቸውና  የማኅበረሰቡ መዝናኛ ነበር። ይሁን እንጂ ያንን ግፍ ዋጋ  አስከፍሏቿል ። በአንድ ምዕተ ዓለም (1st cen B.C) ያንን ግፍ ያንገፈገፋቸው  ባሬያዎች  (Spartacus Thracian) በተባለ ባሬያ መሪነት አምጸው ለሁለት ዓመታት ሮምና ሮማውያንን አሸበሩ ፤ አንቀጠቀጡ ።

ከሁለት ሺ (2000) ዓመታት በኋላ በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን የኢትዮጵያ ገዢዮች ባሮችን ከአንበሳና ከነብር ከማታገል ያነሰ/ሱ ማናቸውም ግፎች ቢሰሩ አሚን ብሎ መቀበል ያስፈልግ ነበር ነው ዶ/ር ደረጀ የሚሉት። ስለሆነም የያኔ ታጋዮች  የታገሉት ቂማቸውን ለመወጣትና አገር ለማረድ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ችግር አልነበረበትም ይላሉ ። ቂም በማን ላይ? ቂም ለምን? ጤናማ አእምሮ ያለው ዜጋ በአገሩና በሕዝቡ ላይ ቂም ይዛልን? ወይስ የያኔ ለውጥ ፈላጊ ታጋዮች በሙሉ ከወያኔ ጋር ያበሩ ነበሩ ለማለት ነው?

6) ‘አሜሪካ በባርያ ጉልበት ነው የቆመው፣ መሪዮቹ የባሬያ ጌታ ነበሩ’ አሉ ። ባሬያዎቹ ነጭ ነበሩ ወይስ ጥቁር? ያ የሆነው መቼ ነበር? ባሬያዎቹ በባርነቱ ተደስተው ወይም አሚን ብለው ተገዝስቷልን? ብሎ መጠየቅ ታሪክ ግድ ይላል። በመጀመርያ ግልጽ መሆን ያለበት በባርነት ይገዙና ይሸጡ የነበሩት ባሬያዎች ነጮች አልነበሩም ።

 (Transatlantic Slave Trade) የአትላንቲክ ውቅያኖስ ተሻግሮ/ባሻገር የባሬያ ንግድ በመባል በሚታወቀው የባሬ ንግድ ክንውን አማካኝነት ከ15ኛው ም/ዓመት ጀምሮ መቼና እንዴት አፍሪካውያንን በባርነት ወደ (ካርቢያን፣ ደቡብ አሜሪ አሁግርና ሰሜን አሜሪካ -ዩናይትድ እስቴትስ) ይደረሱ እንደነበረ የሚያወሳውን ታሪክ መምዘዙን ትቼ  ዶ/ር ደረጀ ላሉት  የባርነት ኩነት ባጭሩ አብራራለሁ። በበርቲስሽ ፍጹም ዘውደኛ አገዛዝ (Absolute monarchy)ሥር አንገዛም በማለት ከዘመኑ  የእንግሊዝ ወታደር በጠመንጃ አፈሙዝ ተፋልመው ካሸነፉ በኋላ  እ.አ.አ በ1776 ዓ.ም የአሜሪካ ነጻነት (Indepenance of American Declaration) ካወጁና ከዚያም በኋላ አሜሪካን ከመሩት ውስጥ በርካታዎቹ የባሬ ጌታ እንደ ነበሩ ታሪክ ይመሰክራል። ለምሳሌ- ቶማስ ጀፈርሰን፣ ሳሙኤል          ቼዝ፣ ጄምስ ማዲሰን፣ (ቤንጃሚን ፍራንክሊን፣ ጆን ጄይ፣አሌክሳንደር) ሃምሊተን ወዘተ.. ባሬያ ነበርዋቸው። ይሁን እንጂ ከመካከላቸው ለባርያ ነጻነት የሚታገሉ ነበሩ  ለምሳሌ ከላይ በቅንፍ ያሰቀመጠኳቸው ትላልቅ ፖለቲከኞች  ፀረ-ባርነት ማኅበረሰብ (anti-slavery society) የተሰኘ ድርጅት መስርተው የባርነት ሥርዓት መቅረት አለበት ብለው አስተምረዋ ል/ተሟግቷል ። ታዲያ ይህ የሆነው በ18ኛው ክ/ዘመን እንጂ በ20ኛው ክ/ዘመን ነውን ?

ዛሬ በአሜሪካ ኅብረ/ፌደራላዊ መንግሥት -ለፕሬዝዴንትነት ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ለሕዝብ ምክር ቤት/ሴነትነት ፣ለጠቅላይ ፍርድ ቤትና ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኝነት፣ በፊልም፣ በሙዚቃ፣ በትወና ወዘተ..   ኢንዱስትሪ ትልቁን ድርሻ ለመያዝ የበቁት የያኔ ባሬያዎች የልጅ ልጆ አይደለሙን? አባቶቻቸውን፣አያቶቻቸውን፣ ቅድመ አያቶቻቸውን በከፈሉት የሕይወት መስዋዕትነት ፣ ባልተቋረጠ ፖለቲካዊና ሰብአዊ  መብቶች፣የእኩልነት እና የፍትህ ጥያቄዎች ትግል ነው አሁን የደረሱበ     ትን ማኅበራዊ ደረጃ የደረሱት ፤ ዶክተርና  ፕሮፌሰር ስለሆኑ ብቻ አይደለም ። ዶ/ር ደረጀ ያለትግል ዲሞክራሲያዊና ፍትኅአዊ የመንግሥት ሥርዓት ያሰፈነ አንድ አገር ሊጠሩልን ይችላሉን?

መዝጊያ፦ አንባቢያን በዚህ ጽሁፍ እንዳነበባችሁት ዶ/ር ደረጀ ለዚያ ቃለመጠይቅ የሰጥዋቸውን መልሶች አንዳቸውም – ውሃ የቋጠሩ ወይም መሬት የረገጡ አይደሉም ። ከተጨባጭ ታሪካዊ እውነታ የራቁ፣ ታሪክን ያዛቡ፣ ፈየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ዓይነት ወይም ውሃና ዘይት እንደመቀላቀል ዓይነት ናቸው ። አዳማጭን የሚስቡ ያልታኘኩና የተወጣጠሩ ባዶ ሃረጎችና ቃላቶች በመጠቀም ብቻ ታሪካዊ ሃቅ ማስተማር አይቻልም ( by using  undigested catch phrases and pompous words alone) we can not teach historical realities).  ዶ/ር ደረጀ እንኳንስ የሩቁን፣ የቅርቡን የዓለማችንና የአገራችንን ፖለቲካዊና ታሪካዊ ኩነቶችን በቅጡ የሚያውቁ አይመስለኝም ። ዶ/ር መሆን ብቻውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ንቃተ-ኅሊና አያስታጥቅም። አንዳንድ ተራ አርሶ አደሮችና ተራ ላብ አደሮች ከአንዳንድ ዶከተሮች የተሻለ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ንቃተ-ኅሊና አላቸው ።

ነገር ግን ስለወያኔዎች እና ስለመሪያቸው መለስ ዜናዊ ባልዋቸውን እስማማለሁ ፤ ለ28 ዓምታት ስንላቸውና ስንጽፍባቸው የነበሩትን ነው ያሉት ። መለስ ዜናዊ (ፀረ-ማኅበረሰብ፣ ፀረ-አገር፣ ፀረ-ታሪክ፣ ፀረ-አንድነት፣ፀረ-የአማርኛ ቋንቋ ማለት ሁሉም ነገር የመጻረርና እኔ ያልኩ     ትን ብቻ የሚል ባህሪዮች ስለነበረው የከፋ የአምሮ በሽታ ሳይኖርበት (ሳይኮፓት) ሳሆን አይቀርም በሚል ዙርያ ዶክተሩ በጠቀስዋቸው ምሁር ብቻ ሳይሆን በርካታዎቻችን ጽፈንበታል፤ ተወያይተንበታል ። በቀውጢ ወቅቶች ለአንድ ቀን እንኳን  ከሕዝብ ጎን ያልተሰለፉ አንዳንድ በድኸረ ህድሳት የከፍተኛ ትምህርት ባህል ያለፉትን ኢ-ጥልቅ ወይም ፖፕሊስት ምሁራን አሁን በተገኝው ነጻ ሚዲያና መድረኮች በመጠቀም፣  የአሁን የአገራችንን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ኢ-ፍትሃዊ ፣ የጠባብ ብሄርተኝነት  ወዘተርፈ (በአጠቃላይ የኢ-ዲምክራሲያዊ የአገዛዝ ሥርዓት) ችግሮች ሁሉ ያንን ለለውጥ የታጋለውን ትውልድ ሲኮንኑና ሲወቅሱ ይደመጣሉ ። የ60ዎችና የ70ዎቹን የለውጥ ሃይሎች ከታገሉባቸ     ው ከላይ ከተጠቀሱትን አበይት የማኅበረሰባችንን ችግሮች፤ ከዚያ በኋላ የመጣውን ትውልድ ታግሎ ያመጣው ለውጥ ምንድ ነው ??  ትግሉ የቀጠለው ያንን ትውልድ በጣለ

በቀውጢ ወቅቶች ለአንድ ቀን እንኳን  ከሕዝብ ጎን ያልተሰለፉ አንዳንድ በድኸረ ህድሳት የከፍተኛ ትምህርት ባህል ያለፉትን ኢ-ጥልቅ ወይም ፖፕሊስት ምሁራን አሁን በተገኝው ነጻ ሚዲያና መድረኮች በመጠቀም፣  የአሁን የአገራችንን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ኢ-ፍትሃዊ ፣ የጠባብ ብሄርተኝነት  ወዘተርፈ (በአጠቃላይ የኢ-ዲምክራሲያዊ የአገዛዝ ሥርዓት) ችግሮች ሁሉ ያንን ለለውጥ የታጋለውን ትውልድ ሲኮንኑና ሲወቅሱ ይደመጣሉ ። የ60ዎችና የ70ዎቹን የለውጥ ሃይሎች ከታገሉባቸ     ው ከላይ ከተጠቀሱትን አበይት የማኅበረሰባችንን ችግሮች፤ ከዚያ በኋላ የመጣውን ትውልድ ታግሎ ያመጣው ለውጥ ምንድ ነው ??  ትግሉ የቀጠለው ያንን ትውልድ በጣለው መሠረት አይደለምን? ያንን ትውል   ድና ትግሉን የምታንቋሽሹና የምትነቅፉ – በተነጠፈበት ጨፋሪዮች ! ተመጻዳቂዮች (ሂፖክሪትስ)! እላችሁአለሁ ። የበኩላቸውን ድርሻ መውጣት ሲያቅታቸው ያንን አገሩና ሕዝቡን ፍጹም ወዳድ ትውልድ ሲወቅሱ ይደመጣሉ። ያንን ጀግና ትውልድ  ከ(ህወሃት፣ከኦነግና ሻቢያ ሃይሎች) ጋር የምታገናኙ ካላችሁ ፍጹም ተሳስታችኋል ። መወቀስና መተቸት ያለባቸው ገዢዮቻችን ናቸው። የአሁኑ የአገራችንን ሁለገብ ቀውሶች ገዢዮቻችን አጭቀውና አፍነው ያቆዩልንን ነቀርሳዎች ናቸው፤  በተለይም መንግሥቱና ወያኔዎች ።

ማሳሰቢያ በሕይወት ላላችሁ ለዚያ ትውልድ የትግል አጋር ለነበራችሁ ሁሉ በያላችሁበት ፦ መንግሥቶቻችንን/ገዢዮቻችንን ያሰፈኑብንን የአስከፊና የጨቋኝ ሥርዓቶች ሁለገብ ችግሮች ግድ ብሎን ያደረግ     -ናቸው ትግሎቻችንን እንደ ወንጀልና ጽንፍ ተቆጥሮ ወይም ተወስዶ ስንወገዝ እየተደመጠና እየተሰማ ነው። ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይነጠቃል እንደሚባለው የኛ ዝም ማለት ገድሎቻችን ጥላሸት የሚቀቡ ሃይሎች እያበረታታ መጥቷል ። በአገራቸውና በሕዝባቸውን ፍቅር የመሰጡ ብዙ ሺዮች ታጋዮች የሕይወት ዋጋ የከፈሉበትን የትግል እሴቶቻችንን ዋጋ ሲያሳጡትና ሲዘልፉት አሚን በለን መቀበል ያለብን አይመስለኝም። መቆርቆር፣መቆጨት፣መሟገት፣መልስ መስጠት ወዘተርፈ የሚያስፈልገን ይመስለኛል ።

https://www.fanotube.net/video/watch.php?vid=6e5b9c64b

እንበርታ! አንስነፍ! በንቀት ለሚተቹን አጸፋ እንስጥ!

የኢትዮጵያ ጠላቶች ይወድማሉ!

ኢትዮጵያ አንድነቷ ጠብቃ ለዘላለም ትኖራለች!