July 21, 2019
Source: https://welkait.com/?p=19785
★ ሃይ ባይ ከልካይ መንግሥት የለም። ሁሉም የእልሁ መወጫ ተዋሕዶና የተዋሕዶ ልጆች ናቸው። በሀገሪቱ ወሳኝ የአመራር ስፍራ ላይ ኦርቶዶክሳውያን ስለሌሉ ድርጊቱን ለማስቆም የሚከራከር ሰው እንኳ የለም።
★ በጅጅጋ፣ ቀጥሎ በከሚሴና በአጣዬ፣ አሁን ደግሞ በደቡብ ቤተ ክርስቲያን ኤጄቶና ቄሮ በተባሉ አልሸባቦች እየወደሙ ነው።
★ የአክሱም ጽዮን ልጆች ደግሞ ከሩቅ ቆመው ይስቃሉ።
#ETHIOPIA | ~ ሲኖዶሱ ግን በህይወት አለን? እስቲ ጠይቃችሁ አጣርታችሁ ንገሩን።
እስከ በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀገረ ሰላም ወረዳ ቤተ ክህነት ውስጥ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል፦
1፦ ጭሮኒ አማኑኤል
2፦ ገተማ ገብረ ክርስቶስ
3፦ ዶያ ቅዱስ ሚካኤል
4፦ ሄጋ ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናትን ትናንት ሐምሌ ፲፪ ከሰዓት በኋላ አቃጥለዋቸዋል።
5፦ ቀጨኖ ልደታ እና
6፦ ቀራሮ ኢየሱስ አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋክ። በአብያተ ክርስቲያናቱ ዙሪያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ቤታቸው ወድማል። ግማሾቹ ተገድለዋል። የተረፋት በየጫካው ተደብቀው ይገኛሉ። ክርስቲያኖች እየተገደሉ ናቸው። የሚደርስላቸው የለም።
★ መንግሥት መረጃ እንዳይወጣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ዘግቷል ተብሏል።
★★★ ባህርዳር ዐማራ ክልል አሳምነው ጽጌን ለመግደል የማንም ፈቃድ ሳያስፈልገው ከወር በፊት ሰተት ብሎ ወደ ክልሉ የገባው የፌደራሉ የመከላከያ ጦር፤ እነ አሰማኸኝና እነ ላቀ ሳይሰሙ በባህርዳር መፈንቅለ መንግሥት እየተካሄደ ነው ያለው ኢቲቪ እስከአሁን ስለ ጉዳዩ ምንም ትንፍሽ እያለ አይደለም።
•••
በሌላም ዜናም ከዚያው ከደቡብ ክልል ሳንወጣ ሰሞኑን በጎፋ መሎ ለሃ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንና በምእመናን ላይ በወረዳው የተደራጁ የመናፍቃን አመራሮች ከክልሉ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር በመሆን በካህናት እና ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመፈፀም ላይ ያሉ መሆናቸውን ለሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ኤልያስም በደብዳቤ ገልጸዋል።
• እስከ አሁን ድረስም ከ57 በላይ ምዕመናን በላሃ ፖሊስ ጣብያ ታስረዋል።
• 1ድ ካህን እና 3 ወጣቶች በጥይት ተመተው በሕክምና ላይ ናቸው።
• አሁንም በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ለማሠር አደን ላይ ናቸው
• በጥምቀት እና መስቀል በዓል ማክበርያ ቦታ ያለው መስቀል እና የመጠመቅያ ገንዳ አፍርሰው ወስደውታል።
• በላሃ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግብ ውስጥ የተጠለሉ ምዕመናንን ለማሥወጣት ከ15 በላይ የጪስ ቦንብ በመወርወር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ ብያደርጉም ምዕመናኑ ባደረገው ተጋድሎ ተርፈዋል።
• ስለለውጡና ስለ አቢቹ ለመደስኮር እንቅልፍ የሚያጡት ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና የኔታ እሸቱ አለማየሁስ ወዴት ጠፉ? ብሔራዊ ቲአቴር መድረክ ላይ ለመደስኮር እንደምትጣደፉት ምነው ይሄ ሲሆን ልሳናችሁ ተዘጋሳ?
• ማኅበረ ቅዱሳን፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረ መለኮት ምሩቃን ሰባክያነ ወንጌል ወንድሞች ምን እያሰባችሁ ነው?
• መምህር ዶር ዘበነ ለማ፣ መምህር ምህረተአብ አሰፋ፣ እነ መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ፣ እነ ዶክተር ዘሪሁን ሙላት፣ ፀረ ተሃድሶ፣ ፀረ ተባዮች ምንጥስዬ ቅብጥርስዬዎች ምን እያሰባችሁ ነው?
• ይሄ አሁን መግቢያ መውጫ አጥቶ በየጫካው እየታረደ ያለው ምዕመን ካሴታችሁን፣ መጻሕፍቶቻችሁን እየገዛ የቤት ኪራይ እየከፈለ ቀፈት ሆዳችሁን እየሞላ ክፉ ዘመን ያሳለፈላችሁ ደግ ህዝብ እኮ ነው። የሲዳሞን ህዝብ በዚህ ወቅት ምነው ዝም አላችሁት?
• በአሜሪካና በአውሮጳ፣ በካናዳና በአውስትራሊያ፣ በዓረቡ ዓለም የምትገኙ የካህናት ኅብረት ለዐቢይ አህመድ ያሽቃበጣችሁትን ያህል ቤተ ክርስቲያን እንደ ጧፍ ስትነድ ምንድነው ዝምታው? ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ለመውሰድ ማን አዚም አደረገባችሁ?
• ” እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
“ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው ፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ።” አሜን. !
“ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ ”
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
ሐምሌ 13/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ

ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ
ደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ