July 26, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/133183


የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት (ኢዴህ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ፓርቲ (ኦነንፓ)፣ የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ (አሕነፓ) እና የአፋር ሕዝብ ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አሕፍዴፓ) በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ በመግለጫቸው  በሕወሃት ጊዜ ይታይ የነበረው የሰብአዎ መብት ረገጣ እየቆጠቆጠ መምጣቱና በፊት ወደነበረው ሁኔተ የመመለስ ዝንባሌ እንዳለ በመገልጽ መንግስት በአስቸኳይ ማሻሻያዎችን በማድረግ ለዜጎች መብት እንዲቆም ጠይቀዋል።
በመግለጫው ሰባት ነጥቦች የተቀመጡ ሲሆን፣ ድርጅቶቹ በተለየም በጋዜጠኛና ሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንደር ነጋ የሚመራውን የባላደራውን ምክር ቤትን በስም በመጥቀስ ፣ ንቅናቄው በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚያራምደውን እንቅስቃሴ ያለምንም ችግር ማድረግ እንዳለበት በማስቀመጥ፣ ለባላደራው አጋርነታቸው ገልጸዋል።
የባላደራው ምክር ቤት፣ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን “ጦርነት ውስጥ ነው የምንገባው” ንግግር ተከትሎ በርካታ የኦህዴድ ባለስልጣናት ባላደራው ላይ ተመሳሳይ ዛቻ ማድረጋቸው፣ ባላደራው ስብሰባዎች እንዳያደረግ፣ ጋዜጣዊ መገጫዎችን እንዳይሰጥ መከልከሉና አባላቱም እየታሰሩበት መሆኑ ይታወቃል።
ድርጅቶቹ በመገጫቸው ያስቀመጧቸው  አሁን እየተወሰደ ያለው ዘርን መሰረት ያደረገ እስራት፣ ጅምላ ፍርጃ በአስቸኳይ ቆሞ ህግን መሰረት ያደረገ አሰራር እንዲዘረጋ፣ በመላ አገሪቱ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን በአፋጣኝና ተገቢ በሆነ መልኩ ምላሽ መስጠት፣ በሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ህይወታቸው ባለፈው ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ጉዳይ በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ፣የሰኔ 15ቱን ግድያ ተከትሎ ያለበቂ ማስረጃ በጅምላ በየቦታው የታሰሩ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ የፓርቲ አመራሮች አባላት እና ንፁሀን ዜጎች በአስቸኳይ