July 25, 20
~”ዶ/ር ዐቢይ የመፅሐፍ ቅዱስ የሚመስል ጥቅስ ቢነግራችሁ እንኳን ፖለቲከኛ መሆኑን አትርሱ።”
~”በጣም ትልቁ ችግራችን መሪ እንከተላለን እንጅ መርህ አንከተልም!”

የትነበርሽ ንጉሴ
“ዶ/ር ዐቢይ የመፅሐፍ ቅዱስ የሚመስል ጥቅስ ቢነግራችሁ እንኳን ፖለቲከኛ መሆኑን አትርሱ። ከቤታቸው ብቻ የተፈናቀሉ አይደሉም፣ እነሱ የቆጠሩት ከቤታቸው የተፈናቀሉትን ነው። እኔ ደግሞ የሚያሳስበኝ ከሙያቸው የተፈናቀሉ ብዙ ተፈናቃዮች አሉ። በጣም ትልቁ ችግራችን መሪ እንከተላለን እንጅ መርህ አንከተልም። መሪ ደግሞ ይሄዳል። ይመጣል። ነግሬያችኋለሁ፣ እናንተም አይታችሁታል። መሪው ሀጥያት ሲሰራ ሀጥያት ሰራህ አንልም። ምክንያቱን መሪ ነዋ! ስለ መርህ አንጨነቅም።
……………በፊት ከዚህ ሀገር ታስረው ለነበሩት ጋዜጠኞች ነፃ ሆኖ የመጠበቅ መብታቸው እንዲከበር ስንከራከር የነበርን ሰዎች ዛሬ ደግሞ ለተጠረጠሩ ሰዎች ያ መብት ተጠብቆላቸዋል ወይ ብለን አንከራከርም። እኛ መሪውን እንጅ መርሁን አናነሳውም።”