July 26, 2019

ኤልቲቪ ላይ ቀርበው ስለ ሰኔ 15ቱ ክስተት ሲጠየቁ አሥራት ሚዲያን የወነጀሉበት ‹‹በሬ ወለደ›› ወሬያቸው እንዲሁ የሚታለፍ አይደለም፡፡ የኦዴፓ ከፍተኛ አመራሩ አቶ ታዬ ደንደአ የሚከተለውን ብለዋል፣

‹‹ከዚያ ሁለት ሦስት ቀን (ከሰኔ 15 ማለታቸው ነው) ቀደም ብሎ ሲደረግ የነበረው ቅስቀሳ በአንዳንድ ሚዲያዎች በአሥራት…በዚያ ሰፈር ያለው ጉዳት መገለል እጅግ በጣም የከፋ ስለሆነ ‹ተደራጅተን መነሳት አለብን፣ መታጠቅ አለብን፣ መዋጋት አለብን› የሚል ቅስቀሳ ሁሉ ሲደረግ ነበር፡፡››

አቶ ታዬ ለዚህ ውንጀላቸው ሌላው ቢቀር ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል፡፡ ለወደፊትም ከእነደዚህ አይነት ‹በሬ ወለደ› ወሬ ለመዳን አሥራትን እንዲመለከቱ የምትቀርቧቸው ምከሯቸው፡፡

አሥራት ከተጠቀሰው ውንጀላ ጋር በምንም መልኩ ሊያገናኘው የሚችለው ስራ እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ሆኖም፣ እንደ ታዬ ደንደአ በሀሰት ዜጎችን እና ተቋማትን የሚወነጅሉትን፣ በዜጎች ላይ ግፍ የሚሰሩትን እያጋለጠ የሕዝብ ልሳን ሆኖ ይቀጥላል፡፡

በላይ ማናዬ