በላፈው ዓመት በ2018 እንደ አውሮፓ አቆጣጠር የአውሮፓ የባህልን ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ ዝግጅት የነበረው በሽቱትጋርት ከተማ፣ በጀርመን አገር ነበር።የዚህን ዝግጅት ሃላፊነት ወስዶ የነበረው የሽቱትጋርት ቡድን ነበር። ይህም ማለት የሽቱቱጋርት ቡድን ይህን የ2018 ዓ.ም. ዝግጅት በአዘጋጅነት ወስዷል ማለት ነው።
አንድ ነገር ጥሩ ነበር ሊባል የሚችለው የእግር ኳስ ሜዳዎቹ ናቸው።የዝግጅቱ ቦታ ለእንዲህ ዓይነት ዝግጅት ከከተማ ወጣ ብሎ መደረጉ መልካም ነው።
የአዘጋጁ የሽቱትጋርት ቡድን የእግር ኳስ አጨዋች ዳኞችን በበቂ አላዘጋጀም። በዚህ ምክንያት ያለ መስመር ዳኞች የተካሄዱ ጨዋታዎችም ነበሩ።
የቢራ ትኬት ልክ ፍራንክፈርት ከዚህ በፊት እንደተደረገው፣ ዛሬ የተሸጠው ትኬት ለነገ እንዳይሰራ በማድረግና ይህም ለህዝቡ በግልጽ ሳይነገር በማታለል፣ ገንዝብ ለማግኘት የትላንቱን ትኬት ለዛሬ ተቀባይነት እንዳይኖረውና ይህም ሕዝብን የዛሬው ትኬት ለነገ አለመስራቱ ሳይነገረውና ምስጢር በማድረግ ነበር።
የሰው ጉልበት እጥረት በግልጽ ይታይ እንደነበረና ሁለት ወይም ከሶስት ያለበለጡ የሹቱትጋርት ሃላፊዎች ብቻቸውን ሲሯሯጡ ይታዩ ነበር። ይህም በቂ የሰው ሃይል ሳያዘጋጁ ሳንቲም ለመሰብሰብ የተደረገ ካልሆነ፣ ለምን በቂ የሰው ሃይል እንዳላሰማሩ የሽቱትጋርት ሃላፊ ነን ባዮቹ ሊያብራሩት ይገባል።
በፌዴሬሽን ሕግ ደንብ ለእያንዳንዱ ቡድን የውሃ አቅርቦት መዘጋጀት ነበረበት።ይህ በሽቱትጋርቱ አዘጋጆች በኩል ጭራሽ አልተዘጋጀም ነበር። በኋላም ፌዴሬሽኑ የውሃውን ወጪ ለተጨዋቾች ለሶስት ቀን እንደሸፈነ ነው።
በሜዳው አካባቢ የሚጣሉትን ቆሻሻዎች ለመልቀም ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ያልበለጡ ነበሩ። እሱም በጣም ብዙ ግዜ መፍጀቱ ነው። በዚህ የፍራንክፈርቱ ዝግጅት ቆሻሻውን ወዲያ በመለቃቃም በቂ የሰው ሃይል በማዝጋጀትና በመኪና በመውስደ ሃላፊነታቸውን በበቂ ተውጥተዋል።የሹቱትጋርቱ አዘጋጆች መደበቅ የሚገባቸው ሰዎች ናቸው።
የአዘጋጁ ቡድን የኢትዮ–ሽቱትጋርት የአጨዋች ዳኞችን የየቀኑን ክፍያ ለመክፈል ሳይፈልጉ ቀርተው፣ ፌዴሬሽኑን ክፍያውን እንዳጠናቀቀ ነው።
ሁለት ቡድኖች ኢትዮ–ትሮንድሃይምና ኢትዮ–ስዊዲን የእግር ኳስ ሜዳውን አንለቅም በማለታቸው ችግሮች ፈጥረው ነበር። በተለይ ኢትዮ–ትሮንድሃይም ፖሊሶች እንዲመጡ ተደርጎ፣ በውድድሩ ሂደት ላይ አላስፈላጊ ውጥረቶች ተከስተው ነበር።እንደዚህ ዓይነት ቡድኖች ከነተጨዋቾቻቸው በፖሊስ ከሜዳው ማስወገድ እንጂ መለመን፣ መለማመጥ ፈጽሞ ተገቢ አልነበረም። በዚህ የቴክኒክ ኮሚቴው ሃላፊም ያሳየው ለቀቅተኝነት ጥሩ አልነበረም።እንደዚህ ዓይነት ቡድኖች ጭራሽ ለህብረተስቡ መጥፎ አዝማሚያ በማሳየት ወደማይፈለግ የእርስ በርሽ ግጭት ውስጥ እንዲፈጠር የሚፈልጉ ነበሩ። ይህ ደግሞ ማንንም አይጠቅምም። ያለነው አውሮፓ ውስጥ ስለሆነ ወንጀል ስርቶ መደበቅ አይቻልም።እነዚህ ቡድኖች ግን በሕጉ መሰረት ሊቀጡ ይገባል።ያለበለዚያ መቀለጃ መሆኑ ይቀጥላል።
የአምቡላንስ መኪና ጥያቄም አንድ ሰው ተጎድቶ ብዙ ክቆየ ብኋላ ብቅ ማለቱ ነበር። አምፑላንሱ ውድድር እስከሚያልቅ ግዜ ድረስ እዚያው ሆኖ አግልግሎት እንዲሰጥ ውል መፈራርሙ የኢትዮ–ሹቱትጋርት ቡድን እንደ አዘጋጅ ሃላፊነት ነበረበት።ይህንንም በተገቢው መንገድ ግዴታውን መወጣት አልቻልም።ገንዘብ ከመቆጠብ አንጻር ከሆነ፣ እጅግ በጣም ያሳዝናል።
ብዙ ግዜ ምግብና መጠጥ የሚገኙባቸው ቦታዎች ተራርቀው መደረጋቸው ለነጋዴውም ለተጠቃሚውም ትልቅ ርቀት ስለሆነ ችግር መፈጠሩ ግድ ነው። ስለዚህ ይህ የሚሻሻልበትን ሁኔታ መፍጠር የቀጣዩ አዘጋጅ አገር ነው። ሽቱቱጋርትማ ረፈደበት።
በኋላ እንደሰማነው የሙዚቃውም ዝግጅት ለሽቱትጋርት አዘጋጆች የተሳካላቸው አልነበረም።
ሌላው የኢትዮ–ሽቱቱጋርት ከፌዴሬሽኑ ጋር በጽሁፍ ውል በመፈራረም መቶ በመቶ ለማሟላት የተስማማቸውን ሁሉንም ማለት ይቻላል ከሜዳው በስተቀር ያሟላቸው ነገሮች በጣም ኢምንት የሚባሉ ናቸው።ታዲያ ለምንስ መዋሽት አስፈለገ? ውሉን ፈርሞ አለመፈጸም መዋሽት ነው። ሌላ ምንም ሊባል አይችልም።
በደህንነት በኩልም በጣም በቁጥር አነስተኛ የሆኑ እንደነበሩና እነርሱም ብዙም የሰሩት መግቢያ በር ላይ ሲሆን፣ ብዛታቸውም በጣም አነስተኛ ነበር።
ሲጠቃለል የኢትዮ–ሽቱትጋርት ቡድን እንደ አዘጋጅ ሆኖ መመረጡ በጣም የሚገርም ነው።ምክንያቱም ለማዘጋጀት ከሌሎች ጋር ተሻምቶ ለምን ግዴታውን መወጣት እንዳቃተው ግልጽ አይደለም። ሁለተኛ ግን ወደሽቱትጋርት ዝግጅቱ ይምጣ ማለት ህብረተሰቡ ብቅ እንዳይል ማድረግ ስለሆነ፣ ፌዴሬሽኑ በጣም ሊያስብበት ይገባል።
ሌላው ፌዴሬሽኑን የሚመልከት ሲሆን፣ ቢያንስ ሊነጋገርባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ።
አንደኛ በፊፋ ሕግ መሰረት ውድድሩ የሚካሄድ ከሆነ፣ ሁሉንም ሙሉ በሙሉ መቀበል ወይም በውድድሩ መመሪያ ላይ ከፊፋ ሕግ ውጭ አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን ማድረግ የሚያስችል ነጥብ መቀመጥ ይኖርበታል።ይህ የውድድር መመሪያ ደንብ ቁጥር 4ን ይመለከታል።
„የእግር ኳስ ውድድር አካሄድ የፊፋን የእግር ኳስ ሕጎችን በመከተል ተግባራዊ ያደርጋል።\” የሚል አለ። ከዚህ በተጨማሪ \”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማሻሻያ ተደርጎበት መጠቀም ፌዴሬሽኑ ይችላል።\” የሚል ቢጨመርበት መልካም ነው።
ሁለተኛ፣ በውድድር መመሪያ ደንቡ ውስጥ አንድ ጨዋታ ስንት ደቂቃ እንደሆነ ቢገባበት መልካም ነው።
ሶስተኛ፣ በውድድር መመሪያ ደንቡ ውስጥ ከየግሩፑ አንደኛና ሁለተኛ ወጥተው የሚያልፉት ቡድኖች የውድድር አካሄድ አልገባም።በሕጉ መሰረት ግን መግባት አለበት።አራት ግሩፖች ካሉ አራት ቡድኖች በአንድ ወገን ሊሎቹን አራት ቡድኖች በሌላ ወገን ለማድረግ ሶስት አማራጮች አሉ።
አንደኛው አማራጭ
ኤ1ቢ2 ቢ1 ኤ2 ሲ1 ዲ2 ዲ1ሲ2
ሁለተኛው አማራጭ
ኤ 1ዲ2ዲ1ኤ2ቢ1ሲ2ቢ2ሲ1
ሶስተኛው አማራጭ
ኤ1ሲ2ሲ1ኤ2ቢ1ዲ2ዲ1ቢ2
ከሶስቱ አማራጮች አንዱን መርጦ የውድድር መመሪያ ደንብ ውስጥ ማካተቱ አስፈላጊ ነው።ከብዙም አተካራ ያድናል።እያንዳንዱ ቡድን ገና ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ሊያውቅ ይገባል።
ባለፈው ግዜ ብዙ ነገር ዝምብሎ ሽልማቶች የተሰጡበት ሁኔታ ተከስቷል።ማን ጎበዝ ተጨዋች ሊሆን እንደሚችል፣ ማን ጎበዝ በረኛ ሊሆን እንደሚችል በቴክኒክ ኮሚቴው በኩል የተሰራ ነገር አልነበረም። ከዬት መጥቶ ያ ሽልማት ሊስጥ እንደቻለ ግልጽ አይደለም።
ፌዴሬሽኑ ምንም ዓይነት መረጃ ወደውጪ እንዳይወጣና መወጣት ሲገባው ግን ሁሉም ይዘቱን በደንብ ከተረዱና አንድ ዓይነት ይዘት ሊኖራቸው ከተደረጉ በኋላ ብሆን የተሻለ ነው።ይህንን አስመልክቶ በሽቱትጋርቱ ዝግጅት ላይ ችግር ተፈጥሮ ነበር።
አንዳንድ ቡድኖች ሁሉንም ነገር እነርሱ ብቻ አዋቂ ሆነው ለመቅረብ ሲሞክሩ ታይቷል። ይህ ግን እውሸት ነው። ሁሉን ነገር ማንም ሊያውቅ አይችልም። ሰለዚህ ፌዴሬሽኑም ላይ ድከመት ካለ ከራስ ቡድን ጥቅም ውጪ ሆኖ ትክክለኛውን ሃሳብ ማቅረብ ተገቢም ጠቃሚም ነው።
የኢትዮ–ሽቱትጋርት ቡድን ለምን ይህን ዝግጅት ለማዘጋጀት እንደፈለገ ለብዙዎቻችን ግልጽ አይደለም። ምክንያቱም ከወሬ በሻገር ሰርተው ውጤታማ ለመሆን አቅሙም ዝግጅቱም አልነበራቸውም።
ሌላው ችግር ለመወዳደር ፈቃደኝነታቸውን ገልጸው፣ በውድድሩ ላይ ያልተገኙ ቡድኖችና፣ በውድድሩ ላይ ተገኝተው በፍርፌ በመሽነፍ ችግር የፈጠሩ ቡድኖች ነበሩ።አነርሱም ለችግሩ አስተዋጽኦ ስለነበራቸው፣ ፌዴሬሽኑ ጠንከር ያለ እርምጃ ሊወስድ ይገበዋል። በሽቱትጋርቱ ውድድሩ ይሄ በደንብ ተከስቷል።
በተለይም በሁለተኛ ዲቪዚዮን በዋናነት ታይቷል።
በሽቱትጋርቱ የልጆቹና ወጣቶቹ ዝግጅት ምንም እንኳ ለእነርሱም ዳኞች ሊመደብላቸው ሲገባ፣ ይህ ሳይደረግ የቀረበት ምክንያት በዳኖች እጥረት ከሆነም፣ ቢያንስ የመጨረሻውን ጨዋታ በአጨዋች ዳኛ ሊመራ በተገባው ነበር።በተረፈ ጥሩ ሙከራ ነበር።
ለልጆች ጨዋታ ዳኞች ጭራሽ እንዲያጫውቱ አልተሞከረም። ለምን? እነዚህ ወጣቶች ደንበኛ አጨዋች ዳኛ እንዲኖራቸው እንደሚፈልጉ ግልጽ ነው። ይህ ተግባራዊ አልተደረገም።ለወደፊቱ ቢታሰብበት መልካም ነው።
የዘንድሮው አዘጋጅ ኢትዮ ዙሪክ ከሽቱትጋርቱም ሆነ ከዚህ በፊት ከተዝጋጁት ዝግጅቶች ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን በደንብ አጥንቶ የተሻለ ዝግጅት አዘጋጅቶ ይጠብቀናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
ከተንሳይት በቃና
20.07.2019
