July 28, 2019
«ህገመንግስቱ እስካልተቀየረ ድረስ የአዲስ አበባ ለውጥ የሚታሰብ አይደለም፡፡ የትግላችን ዋነኛ ትኩረት በውድም በግድም ህገመንግስቱን ማስቀየር ነው፡፡»

«የትግላችን መዳረሻ ጫፍ አዲስ አበባን ራሷን የቻለች ክልል/ግዛት (State) ማድረግ ነው፡፡»
*****«በህገመንግስቱ ሆን ተብሎ አዲስ አበባ ህገመንግስቱን የመተርጎም እና የመዳኘት መብት ከተሰጠው ከፌዴሪሽን ም/ቤት እንድትወጣ ተደርጓል፡፡»
«ህገመንግስቱ ዘጠኙን ክልሎች እንጂ አዲስ አበባን አያውቃትም፡፡ (የአዲስ አበባን ህዝብ ህልውና ሙሉ በሙሉ እውቅና ይነፍጋል)»
******«በህገመንግስቱ መሰረት የአዲስ አበባ ህዝብ የሀገሩ ባለቤት አይደለም፡፡ በፌዴሬሽን ምክርቤት እንዳይወከል እና አንድም ወንበር እንዳይኖረው ስለተደረገ ህገመንግስቱ ላይ ጥያቄ ቢያነሳ ለአዲስ አበባ ህዝብ የሚወስኑለት ሌሎቹ ክልሎች ናቸው፡፡»
******«በህገመንግስቱ ውስጥ ”ልዩ ጥቅም” የሚል የአፓርታይድ ሥርዓትን መሰል በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የሚጭን አንቀፅ እንዲገባ አድርጓል»
«የብዙ ብሔረሰቦች መኖሪያ የሆነውን ሐረሬን ክልል ለማድረግ የተጠቀመ አመክንዮ አዲስ አበባን ክልል ለማድረግ ምንም አያዳግተውም፡፡ »
«ሲዳማን ከዞንነት ወደ ክልልነት እያሸጋገረ ያለ መንግስት አዲስ አበባን ወደ ክልልነት ለማሸጋገር የሚከብደው ነገር ምንድን ነው?»
«ሐረሬን ክልል ያደረገ አመክንዮ ድሬዳዋን ክልል ማድረግ አይሳነውም፡፡»
«እንደ አዲስ አበባ ሁሉ ድሬዳዋም ተደራጅቶ የሚታገልላት የራሷ ባለአደራ ም/ቤት ያስፈልጋታል፡፡»
«እኔ የአብን (የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ) ደጋፊ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን እስካሁን እስከማውቀው ድረስ ህብረ-ብሔራዊ ነን የሚሉትን ፓርቲዎች ጨምሮ በወሬ ሳይሆን በዶክመንት ”አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ናት” የሚል ግልፅ አቋም የያዘ የፖለቲካ ድርጅት አብን ብቻ ነው፡፡»
«የምርጫ ቀን ቢመጣ እንደ ግለሰብም እንደ ባልደራስም ህዝብ እንዲመርጠው የምንደግፈው አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ መሆንዋን በወሬ ሳይሆን በዶክመንት/ በፓርቲ ፕሮግራማቸው የተቀበሉ ድርጅቶችን ብቻ ነው፡፡ ይህ ግልፅ ሊሆን ይገባል፡፡»
«የዛሬ 22 ዓመት ገደማ ህገመንግስቱ የፈጠረው ”ደቡብ” የሚባል ክልል ውስጥ እንኳን ”እኔ ደቡብ ነኝ” የሚል አዲስ ብሄርተኝነት እንደተፈጠረ ራሱ ደኢህዴን ያስጠናው ጥናት መሥክሯል፡፡ ማንነት ይፈጠራል ፣ ያድጋል፡፡ (አካባቢያዊ ተፅህኖዎች ማንነትን ይፈጥራሉ፡፡) በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የአዲሳበቤ ማንነት/ አዲሳበቤነት consolidate እንደሚያደርግ (ተደላድሎ እንደሚጎለምት) ጥርጥር የለንም፡፡»
«አዲሳበቤነት የህልውና/ የመኖር-ያለመኖር ጉዳይ ነው!»
=================
ባለአደራ ኤርሚያስ ለገሰ የሰጠው ሙሉ ማብራሪያ እንዲሁም በስብሰባው ላይ የተነሱ ጥያቄዎች እና የተሰጡ መልሶችን ሙሉ ፊልም በአባይ ሚዲያ ገፅ ላይ ያገኙታል፡፡