August 1, 2019

1. የዚችን ሃገር ፖለቲካ ሁኔታ በበለጠ ለመረዳት ማንበብ አስፈላጊ ነዉ በሚል ሰሞኑን ትቂት መጽሀፎች ይዠ ጠፋ ብየ ነበር፡፡ ካነበብኳቸዉ መጽኃፎች ዉስጥ ስለ መኢሶኑ አመራር ሃይሌ ፊዳ ይገኝበታል፡፡ ሃይሌ ፊዳ በፈረንሳይ አገር ሲታተም ለነበረ አንድ መጽሄት ጥቅምት 1967 ዓ.ም ባሰፈረዉ ጹሁፍ ላይ መንግስቱ ሃይለማሪያምን ገና ስልጣኑን ከመጀመሩ አካሄዱ አልጣመዉም እና እንዲህ ሲል እንዳሰፈረ አማረ ተግባሩ (ዶ/ር) ;ሃይሌ ፊዳ እና የግሌ ትዝታ በሚለዉ መጽሃፉ እንደሚከተለዉ ገልጾል “ተቀዳሚ ሊቀመንበር ሻለቃ መንግስቱ ሃየለማሪያም ባገር ፍቅር መንፈስ የተቃጠለ መኮነን ለመሆኑ ጥርጥር የለዉም፡፡ ይህ ያገር ፍቅር መንፈስ ግን በዲሞክራሲ ካልታረቀ ሻለቃዉ ዉሎ አድሮ አረመኔ እና ፋሽስታዊ መሆኑ የማይቀር ነዉ፡፡” እንግዲህ መንግስቱ ሃይለማሪያም ሁላችንም እንደምናዉቀዉ ኢትዮጵያ ወይም ሞት እያለ ከአለም ትቂት እጅግ አምባገንን መሪዎች እንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይህ የሃይሌ ፊዳ አባባል ኢትዮጵያ ከምትፈርስ እኛ ብንሞት ይሻላል ለሚለዉ ለ ዶ/ር አብይ ትምህርት ሊሆነዉ ይገባል፡፡ ዶ/ር አብይ ስለሃይሌ ፊዳ በተደጋጋሚ ሲናገር ሰምቸዋለዉ፡፡ ሃይሌ ፊዳ በ60ዎቹ ከነበሩት የኦሮሞ ኢሊቶች ፕሮግረሲቭ የሚባለዉ ነዉ፡፡

2. ብዙ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ አትፈርስም ወይም ደግሞ ልትፈርስ ስለሆነ እኛ እናድናታለን ወይም እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች በማለት አንድም ተወዳጅነት ያተርፉበታል ወይም ደግሞ ፍርሃትን በማስረጽ ተገዠነትን ያጠናክሩበታል፡፡ ኢትዮጵያ አትፈረስም እያሉ በየመድረኩ መለፈፍ self-serving role እንጅ ሌላ አላማ የለዉም፡፡ በነገራችን ላይ የሀገር መሪ ወይም ማንኛዉም ህዝብን በመምራት ደረጃ ላይ ያለ ሰዉ ስለ ሀገር መፍረስ ደጋግሞ ማዉራት አይኖርበትም፡፡ ስለ አብሮነት፤ አንድነት እና መከባበር ነዉ የሚወራዉ፡፡በነገራችን ላይ እንደሚሰበከዉ ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ የለባትም፡፡ በሀገሪቱ ዉስጥ ያሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸዉ ቡደኖች መካከል power struggle ሁሌም ይቀጥላል፡፡ ይህ power struggle በዋነኛነት የፖለተካ እና ኢኮኖሚ ተቋማትን ለመቆጣጠር እና የቡድን ፍላጎቶችን በእነዚህ ተቋማት አማካኝነት የማስፈጸም አላማ ነዉ የሚኖረዉ፡፡ ሀገር ማፍረስ ቢቻል ኖሮ 40 አመት የታገለዉ ትህነግ (በአዴፓ አጠራር) ወይም ህወሃት እንዲሁም በዚሁ ተመሳሳይ እድሜ የታገለዉ ኦነግ ባደረጉት ነበር፡፡ ነገር ግን በባህል፤ በአኗኗር፤ በቋንቋ፤ በሃየማኖት፤ በስነልቦና፤ በኢኮኖሚ፤ በጋብቻ፤ ባጠቃላይ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፉ የተሳሰረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በትቂት ኢሊቶች ትርክት መለያየት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ የሸነጠዉ ሁሉ እየተነሳ እንባ እያነባ ኢትዮጵያ ልትፈረስ ነዉ ቢልህ አትስማዉ፡፡ የሚፈረስ ነገር የለም ይልቅ እንደዚህ በማለት ተወዳጅነትን እና ተቀባይነትን ማግኘት ዋናዉ አላማዉ ነዉ፡፡ ሀገሪቱ እንዳትፈረስ አድርጎ አጼ ምኒልክ ገንብቷታል፡፡

3. ችግን ተከላዉ ጥሩ ነዉ፡፡ የሰዉ ልጅ በመሰረታዊነት ህይወቱ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነዉ፡፡ በጠቃሚነቱ ላይም ማንም ጥያቄ አያነሳም:: ነገር ግን አሁን ያለዉ ተጨባጭ የሀገሪቱ ሁኔታ ወላ በችግኝ ተካለ፤ ወላ በማዋከብ፤ ወይም በማሰር፤ አጠቃላይ በፕሮፖጋንዳ የሚፈታ አይደለም፡፡ የሀገሪቱን መሰረታዊ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ችግር ለመፍታት መሬት የነካ የተቋማዊ፤ የፖሊሲ እና ስትራቴጅ ለዉጥ ያስፈልጋል፡፡ ያገጠጡ ህዝቡ በፍጥነት እንዲፈታለት የሚፈልጉ ችግሮች ተባብሰዉ ቀጥለዋል፡፡

-መፈናቀል፤ መታሰር፤ እርሀብ መቆም ይጠበቅበታል
-የኑሮ ዉድነቱ ከመቸዉም በላይ ጠሪያ ነክቷል
-የሀገሪቱ የንግድ ጉድለለት ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ ዘንድሮ ሰፍቷል
-የሀገሪቱ የበጀት ጉድለት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል (የዘንድሮዉ በጀት ክፍተት 100 ቢሊየን ደርሷል)፡፡ ይህ ማለት የሀገሪቱ 5 በመቶ አካባቢ GDP በባለፈዉ አመት 3 ፐርሰንት አካባቢ ነበር፡፡
-ወደ ሃገር የመጡ የዉጭ ኢንቨስትመንት ከአምናዉ በ10 ፕረሰንት ቀንሷል
-የሀገሪ የዶላር እጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነዉ ጥቁር የዶላር ገቢያዉም 40 ብር ደርሷል ;ከኖርማል ገቢያዉ በ 12 ብር እና ከዚያ በላይ ልዩነት
-የዋጋ ንረቱ 15 ፐርሰንት አካባቢ እየተንከባለለ ነዉ፡፡
– አብዛኛዉ የኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ተመራቂ የስራ እድል የለዉም
– ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰዉ ስራ ፈላጊ ቀድሞም ደካማ በሆነዉ የከተማ ሰርቪሶች ላይ ከፍተኛ ጫና አምጥቷል፡፡

ከዚህ ሁሉ በላይ ትልልቅ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚፈልጉ የማንነት እና ወሰን፤ የሀገመንግስት ስረአት፤ በምርጫ የመወከል ወዘተርፈ ከፊት ለፊት ተቀምጠዋል