2019-08-10
ፖሊስ የኢትዮጲስ ጋዜጠኞችን አስሮ በፀረ-ሽብር ህጉ ከሶ የ 28ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠየቀባቸው!!! የኢትዮጲስ ጋዜጠኛ ምሥጋን ጌታቸው እና አዳም ውግጅራ ፤ ትላንት ነሃሴ 3/2011 የችሎት ውሎ ለመዘገብ በተገኙበት ፍርድ ቤት ፖሊስ ይዞ ያስራቸዋል። እነኚህ ጋዜጠኞች በችሎት ለመታደመ እና ለመዘገብ ከተገኙበት ቦታ የያዛቸው ፖሊስ ፤ አንድ ቀን አስሮ አሳድሮ በማግስቱ ፤ በፀረ-ሽብር ህጉ በመወንጀል ፍርድ ቤት አቅርቦ የ 28ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል። እርግጥ ነው ፤ እንዲህ ያለው ነገር የሚያመላክተው አስቀድሞ በግፍ የታሰሩት የህሊና እስረኞች ፤ የቀረበባቸው የሽብር ክስ ምን ያህል የሐሰት እንደሆነ የሚያሳብቅ ነው። Filed in:Amharic