August 14, 2019
*** የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአመራሮቹና በአባላቱ ላይ እየተፈፀመ ያለው እስርና ወከባ የፓርቲዎች የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ መርህን የጣሰ መሆኑን በመጥቀስ፣ በቀጣይ ራሱን ከስምምነቱ ሊያገል እንደሚችል ያስታወቀ ሲሆን የታሰሩትን አባላቱን ለማስፈታት የተለያዩ የትግል ስልቶች መንደፉን የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡ ንቅናቄው በአባላቱ፣ በአማራ የመብት ጥያቄ አራማጆችና አንቂዎች ላይ መጠነ ሰፊ እስራት መፈፀሙን ጠቁሞ የታሰሩትን ለማስፈታት በቅድሚያ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የተደራጀ አቤቱታ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ለሚመለከታቸው የመንግስትና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ …