August 17, 2019

Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል ስልጣን መጋራት የሚያስችላቸውን የመጨረሻ ስምምነት ተፈራሙ፡፡

የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ስነ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል ስልጣን እንደሚጋሩ ነው የሚጠበቅ፡፡
ይህም በሀገሪቱ ለበርካታ ወራቶች የቆየውን የፀጥታች እና ህዝባዊ ተቃውሞ ፍፃሜ ያስገኛል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የልዑላዊ ምክር ቤት የሚቋቋም ሲሆን ምክር ቤቱ ስድስት የሲቪል እና አምስት ወታዳዊ አመራሮችን በአባልነት ያካታል፡፡

የልዑላዊ ምክር ቤቱን ሁለቱ ወገኖች በየሶስት ዓመት እየተፈራረቁ የሚመሩት ሲሆን በዚህ መሰረት ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የነፃነትና የለውጥ ሀይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚሾም ይሆናል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በዚህ የመጨረሻ የስምምነት ስነ ስርዓት ለመሳተፍ በዛሬው ዕለት ሱዳን ካርቱም ገብተዋል።