August 17, 2019
Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣ 2011(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የዓለም የቱሪዝም ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሀገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የ2019 የዓለም የቱሪዝም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ሽልማቱንም የፊታችን ህዳር ወር ላይ በለንደን ከተማ በሚካሄደው የዓለም የቱሪዝም ሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የሚቀበሉ ይሆናል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሀምሌ ወር መጨረሻ ላይ ከአለም የቱሪዝም ፎረም ፕሬዚዳንት ቡሉት ማግቺ ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።
በውይይታቸውም ተቋማቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የሚካሄደውን የአለም የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳለው በሉት ማግቺ መናገራቸው ይታወሳል።