August 17, 2019

ከ60 በላይ ህይወት በተጨፈጨፈበትና 17 አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ ከሶስት መቶ በላይ ቤቶች ውድመት ተጠርጥረው የታሰሩት ኤጄቶዎች ዛሬ ተፈቱ። በእነ ታሪኩ ለማ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ዘጠኝ ኤጄቶች ዛሬ ነሀሴ 10 ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በ50 ሺህ ብር የዋስ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር ተለቀዋል።
የዋስ መብታቸው የተጠበቀላቸውና ከእስር የወጡት፦
1 ታሪኩ ለማ
2 ጌታነህ ደጉዬ
3 በላይ በልጉዳ
4 ፋሲካ ለገሰ
5 ለገሰ ሀንካርሶ
6 ገናለ ጋርሞ
7 መለሰ አጋሮ
8 ግርማ ቃረ
9 አስናቀ አሰፋThe Battle Of Adwa: When Ethiopia Crushed Italy!x
ሲሆኑ ሌሎቹ በእነ ረ/ፕ/ር ተሰማ ኤልያስ መዝገብ ላይ ያሉት እስረኞች ገና ውሳኔ አልተሰጣቸውም፡፡
በሲዳማ ለብዙ ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑት የኢጂቶ አመራሮች በዚህ መልኩ ከ እስር ቤት ሲፈቱ፣ በአንዲትም ህይወትና ንብረት መጥፋት እማይጠየቁት ከሺህ በላይ የአማራ ተወላጆች ግን በእስር ይማቅቃሉ
እነዚህ ከስድሳ በላይ ንፁሃን ህይወት በግፍ ተጨፍጭፎ መገደልና 17አቢያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ ከሶስት መቶ በላይ አቢያተ ክርስቲያናት መቃጠል ተጠያቂ ናቸው ተብለው የታሰሩ ሰዎች በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ሲፈቱ ማየት በእጅጉ ያማል ብሎም ያንገሸግሻል:
የሚያመው የሰዎቹ መፈታት ሳይሆን በአንዲትም የሰው ልጅ ህይወት መጥፋት እና በንብረት መውደም እማይጠየቁትን ከሺህ በላይ የአማራ ልጆችን ዋስትና ነፍጎ በእስር እያሰቃዩ የመሆናቸው ጉዳይ በአንዲት ሀገር ውስጥ ያሉ ዜጎች በዘር ማንነታቸው እየተለዩ ለስቃይ የመዳረጋቸው ሁኔታ ነው እሚያሳምመው:::
ይህ ምንም ድብብቆሽ የለለው እልም ያለ አፓርቲያዳዊ የዘረኝነት አገዛዝ ውጤት እንደሆነ ድርጊቱ በራሱ አፍ አውጥቶ እየተናገረ ያለበት ሁኔታ ላይ እነገኛለን::
ምንም አይነት ፖለቲካዊ ሚና የሌላትን ነፍስ ጡር ሴት እነሱ ጉድጏድ ቆፍረው ያጠፉት ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ባለቤትና አማራ በመሆና ብቻ በግፍ አስረው በሚያሰቃዩበት ሀገር በከፍተኛ እልቂት ተጠያቂ ሆነው የታሰሩትን ነፍሰ በላዎችን ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የዋስትና መብታቸውን ጠብቀው እንዲፈቱ ማድረግ የግፎች ሁሉ ግፍ ነው::
እንግዲህ ይህ ነው የአቢይ መራሹ የኦዴፓ መንግስት ፀረ አማራዊ አይኑን ያፈጠጠና ያገጠጠ ዘረኝነትን ተግባር ሲፈፅም እያየን ያለነው:::