ታጠቅ ዙርጓ

: August 16/2019

የነገድና የጎሳ (tribe and ethnic) ማንነት መገለጫ ፦ ቋንቋ፣ ማኅበራዊ ባህል ፣ልማዳዊ አኗኗር፣ ማኅበራዊ ሥነልቦና (language,social culture, customary habits and psycho-social dynamic) ከሆኑ አማራ እነዚን ማንነቶች የሉትም ማለት ነውን?

የኦሮሞችን፣ የትግሬዎችን፣የአፋሮችን ፣ የሱማሌዎችን፣ የጉራጌዎችን፣ የወላይታዎችን ወዘተ..

ማንነት የሚገለጸውና የሚለየው ከላይ በተጠቀሱትን እሴቶች ከሆነ አማራ እነዚህን እሴቶች ለምን አይኖሩትም?

ከየትኛው ጭብጣዊ ወይም ሳይንሳዊ ጥናት ተነስተው ነው አማራ የሚባል ብሄር የለም፣አማርኛ የአማራ ቋንቋ አይደልም የሚሉት? የቋንቋ፣ የማኅበራዊ ባህል፣የልማዳዊ አኗኗር እና የሥነልቦናዊ ሊሂቃን ማለት የሥነስብዕ ሊሂቃን (Anthropologists) ናቸው በዚህ ጉዳይ አስተማማኝ መልስ መስጠት የሚችሉት ።

ከላይ የጠቀስኳቸው ሶስቱም ሰዎች በእነዚህን የትምህርት መስኮች ደንቆሮች ናቸው ፤ በማያቁት ነገር ገብትው ይዘባርቃሉ።

የዘመኑ የአገራችን የሚዲያ ሰዎች በአንዳንድ ምክንያት አደባባይ የወጡትን ወይም መጽሃፍ በመጻፋቸው ብቻ ለአገራችንም ሆነ ለሕዝባችን ምንም ፋይዳ ያለው ነገር ሳይሰሩ ፤ በባዶ በማዳነቅ ‘ወደሰማይ ስለሚያወጡ ዋቸው’ የፈለጉትን ቢጽፉም ሆነ ቢናገሩ ሕዝቡ ይቀበለናል የሚል እምነት አላቸው።

አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ከተፈታበት ግዜ አንስቶ፣ዶክተር ብርሃኑ ነጋ አገር ቤት ከገባበት ግዜ ጀምሮ ለቃለመጠየቅ ለሚዲያ ሰዎች በመቅረብ የአንበሳን ድርሻ የወሰዱ ፖለቲከኞች ናቸው ። ያስተናገዷቸው የሚዲያ ሰዎች እነሱ ያሉትን ተቀብለው ከማስተጋባት ባሻገር፤ እንዴት? መቼ?የት? ለምን? ማስረጃህ ምንድነው? የተሰኙ ጥያቄዎች ሲያቀርቡላቸውና እውነቱ ን ለማግኘት ሲያፋጥጧቸው አይደመጡም/አይሰማም ። የሚዲያ አውታ ራቸው የውሬ እጦት ስላለባቸው ተመልሰው አይመጡልንም ከሚል ፍርሃ ት ይመስለኛል ጠንከር ጠንከር ያሉትን ጥያቄዎች የማያቅርቡላቸው።

ከላይ የጠቀስኳችው ሁለቱም የኢትዮጵያዊነት ጭንብል/ማስክ ለብሰው አምታተውና አተራምስው ሥልጣን ባቋራጭ በሚል መርህ የተጓዙ ናቸው። መጠየቅ ከሚያስፈልጋቸው በርካታ ጥያቄዎች ጥቂቶቹን ላስጨብጥ ፦

1)ከአገር ውጭ በነበረው ትግል ግንቦት7 በዲሞክራሲያዊ መርህ አንድ አገር አንድ ሕዝብ ብለው ከሚታገሉትን ከኢትዮብሄርተኛ ድርቶች ጋር አብሮ ከመታገል ፤ ለምን ከፀረ አንድነትቾ እና ተገንጣዮች ጋር አብሮ መስራትን መረጠ? ለምሳሌ ከሲዳማ ነጻ አውጪ ግንባር፣ የያኔ ከኦጋዴ ነጻ አውጪ ግንባር ፣ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር ወዘተርፈ ተብዮች ጋር

2)የግንቦት7 ንብረት የሆነው ኢሳት እነጃዋርን፣ሻቢያን፣ድምህትን እና ከላይ የጠቀስኳቸውን ድርጅት መሪዮች የሚፈልጉትን ለመናገር ደጋግሞ የአየር ግዜ ሲሰጧቸውና ሲያስተናግዷቸው ፤ በዲሞክራሲያዊ መርህ አንድ አገር አንድ ሕዝብ በማለት ሲታገሉና ሲጮሁ ለነበሩትን ያንን እድል አልሰጣቸውም ፤ ለምን?

3) ኢሳትን ማቋቋሜያ ገንዘብ ለመሰብሰብ በሚዲያና በተለያዩ የስብሰባ መድረኮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወያኔ ከስድስት ወር ግፋ ቢል ከአንድ ዓመት በላይ አይቆይም፣ ወያኔን የመጣል ትግል ከአንድ ዓመት ከበለጠ ትግሉን አቆማለሁ እያለ ቀሰቀስ፣ ፎከረ። እውነት የመሰላቸው እውህ እውህ ኢትዮጵያውያን እያንዳንዳቸው $500 ዶላር አዋጡ። በዚያ የውሸት ፉከራው ምክንያት የራሱን አባትና ጅነራል አሳምኖ ጽጌን ጭምር በርካታ ኢትዮጵያውያን ለወያኔ እሥር ቤት ተዳረጉ። ይህንን አስመልክቶ ለምን ዋሸህ? ገንዘብ ሰብስቦ ኢሳትን ለማቋቋም ያንን ያህል ሰው ለእስር መዳረግ ነበረበትን? ብሎ ከጠየቀው ከአንድም ጋዜጠኛ አላዳመጥኩም/ አልሰማሁም ።

4) ንቦት7 በአስመራ የመሸገው በርግጥም ወያኔ በጠመንጃ አፈሙዝ ተፋልሞ ኢትዮጵያን ከወያኔ ነጻ ለማድረግ ነበር ወይስ ‘ፊሽካው ተነፋ’! በሚል መፈክር የኢሳትን መዋጮ ለማቀጠል (sustain) ለማድረግ ነበር?

5) የግንቦት7 ዓላማ ከወያኔ ጋር በጠመንጃ አፈሙዝ ለመፋለም ከነበረ የጎንደርና የባህርዳርን ወጣትች በወያኔ ጥይት እንደቅጠል ሲረግፉ ለምን አልደረሰላቸውም?

6)ከግንቦት7 በፊት ከአሥር ያለነሱ ኢትዮጵያዊ የፖለቲክ ድርጅቶች በአሥመራ ‘ቤርሙዳ ትሪአንግል ትውጠው መቅረታቸውን’ እየታወቀ የግንቦት7 ወደ አሥመራ ማምራት እላይ ከጠቀስው የኢሳትን መዋጮ ከማጠናከር ሌላ ምን ፋይዳ አስገኘ?

7)የግንቦት7 ወደ አሥመራ ማምራት (1) የኢሳትን ሕይወት ለማቆየት ከኢትዮያዊያን ድጎማ ለማግኘት (2) ከኢሳያስ በዓመት $500,000 ዶላር ከማግኘት ጥቅም ባሻገር ትልቁ ፋይዳ ያበረከትው ለኢሳያስ አፈወርቂ ነበር።ይኽወም ኢሳያስ ዲሞክራት መሪ ነው ፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለሚታገሉ ሃይሎች የሚረዳና የሚያስጠጋ መሪ ነው ፣ኤርትራውያን ስብእና ያለው መሪ አላቸው፣የሚሰደዱት የውጩን ዓለም ስለሚያምራቸ ው ነው የሚል ዓይነት መልዕክት ወይም ገጽታ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማስጨበጥ ሚና ተጫውቷል ወይም ለማስጨበጥ አስተዋጾ አድርጓል ። ስለሆንም ይህ ትልቅ ደባ አይደለምን? ለምን አይጠየቁም?

እነዚህንና ሌሎችም ግንቦት7 የፈጸማቸውን ደባዎች ወደ ጎን ተትው አንዳርጋችው የዘመናችን ‘ብቸኛ ታጋይ፣የአጼ የተድሮስ አቻ ፣የበላይ ዘለቀ አቻ ፣የአርበኛ ሸዋረገድ አቻ፣የአቡነ ጴጥሮስ አቻ ተባለለት’ (በዳቁን ዳንኤል ክብረት ጦቢያ መድረክ) ላይ። ሰዎች የሌላቸውን ክህሎት በመካብ ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳሳት አይሆንምን?

አንድ ኢትዮጵያ አንድ ሕዝብ በሚል መርህ እንደችካል ተተክለው ምንም ዓይነት የፖለቲካ ሽርሙጥና ሳይጫወቱ ከ40-55 ዓመታት የታገሉትን ሃቀኛ ኢትዮጵያውያንን እየፈለጋችሁ ለሕዝባችን ለምን አታስተዋውቁም ።