የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የምርጫ ረቀቅ ህጉን አስመልክቶ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚል ርእስ ምርጫ ቦርዱ ካቀረባቸው ውስጥ የሚከተለው ይገኛል::

ጥያቄ 2- የፓለቲካ ፓርቲዎች ለምስረታ ለአገራዊ ፓርቲ 10 ሺህ የድጋፍ ፊርማ እና ለክልል ፓርቲ ምስረታ 4 ሺህ የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባሰቡ በረቂቅ ህጉ ውስጥ ለምን ተካተተ?

መልስ – የፓለቲካ ፓርቲዎች ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው ከመፈለግ አንጻር፣ ከአገሪቷ ህዝብ ቁጥር አንጻር እንዲሁም የሚወክሉት ህዝብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከማጥበቅ አንጻር 10 ሺህ እና 4 ሺ የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ መደንገጉ የተጋነነ ቁጥር አይደለም፡፡ በአንዳንድ ፓርቲዎች የሚነሳው አሁን ካለው የጸጥታ ችግር አንጻር 10 ሺህ ሰው ማስፈረም አንችልም የሚለው ሃሳብ የሚያሳምን ቢመስልም መታወስ ያለበት ግን አንድ ህግ ሲወጣ ለአንድ አመት ብቻ ተብሎ አለመሆኑን ነው፡፡ ህግ የሚወጣው ለረጅም ጊዜ ከመሆኑ አንጻር የህጉን መርሆ በጊዜያዊ ሁኔታ ብቻ ማየት አይገባም፡፡

የ ኔ አመለካከት
ቁጥሩ የተጋነነም ብቻ ሳይሆን አመክኖያዊ መሰረትም የሌለለውና የፖለቲካ ምህዳሩንም የሚያጠብ ነው።

ለምሳሌ በአፍሪካ ትልቁ የህዝብ ቁጥር ያላት እና ዴሞክራሲያዊ ሽግግርንም በማካሄድ ላይ የምትገኘው ናይጀሪያ ከ (170) አንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለሀገራዊ ፓርቲነት ምዝገባ የሚያሰፈልገው 500 (አምስት መቶ) ሰው ብቻ ነው

ከአንድ ቢሊየን ሶስት መቶ ሽህ በላይ የህዝብ ቁጥር ያላትና ዴሞክራሲን አጠናክራ በመምራት ላይ የምትገኘው ህንድ ለሀገራዊ ፓርቲነት የሚያሰፈልገው አንድ መቶ ሰው ብቻ ነው

57 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ደቡብ አፍሪካ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት የሚያሰፈልገው 500 ሰው ብቻ ነው

ባአፍሪካ ድንቅ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ገነባች የምትባለው ቤኒን ለሀገራዊ ፓርቲ ምስረታ የምትጠይቀው 210 ሰው ብቻ ነው።

ስለዚህ የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ አስር ሽህ ሰው አምጡ ሲል ከምን አመክንዩ ተነስቶ እንደሆነ የሚገርም ነው።

ስለዚህ አንድ ጊዜ ከተናገርን ወደኳላ አንመለስም የሚል ለዴሞክራሲ ጸር የሆነ አስተሳሰብ ወደ ጎን ጥሎ የተሰራውን ስህተት ባስቸኳይ ማረም የሰፈልጋል።ስህተትን ማረም ታላቅነት እንጂ ሽንፈት አይደለም።

በዚህ አርቲፊሻል ቁጥር የፖለቲካ መድረኩን ማጥበብና ተወናዋዮቹን የተወሰኑ “ምርጥ” ድርጅቶችን ማድረግ ሊቆም ይገባል። ለዴሞክራሲ ግንባታ አይረዳምና።

በሌሎቹ ነጥቦች ላይ ያለኝን አመለካከት ይዠ እመለሳለሁ

አስከዚያው ሀሳብወን ያካፍሉ፣ እንነጋገርበት የመብታችን መደፈር ወይም መከበር ጉዳይ ነውና ዝምታ በዚህ ጉዳይ ወርቅ አይደለም