August 19, 2019
አይፈተሹም የተባሉ የመከላከያ ሰራዊት መኪናዎች በሕዝብ ተቃውሞ እንዲቆሙ ተደርጓል።

መተማ ላይ አምስት የመከላከያ መኪናዎች ወደ ሱዳን ለማለፍ ሲሞክሩ “አንፈተሽም” በማለታቸው ከሕዝቡ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ በሕዝብ ተቃውሞ እንዲቆሙ ከተደረገ በሆላ ተፈትሽው በመሳሪያ የሞሉ እንደነበር ተገለጸ።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት “ወደ ዳርፉር እየሄድን ነው” ቢሉም ማለፊያም ሆነ ወደ ዳርፉር የሚሄዱበትን ማስረጃ ማቅረብ አለመቻላቸው ተገልጿል።

የመኪናዎቹ ታርጋዎች እንዳይለዩ በግሪስ የተቀቡ መሆናቸው በሕዝብ ጥርጣሬ መፍጠሩን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት መኪናዎቹ እንዲፈተሹ ባለመፍቀዳቸው ሕዝቡ ኬላ ዘግቶ አስቁሞ ከክልሉ ልዩ ሃይሎች ጋር ባደረገው ፍተሻ ብዙ መሳሪያዎች ተገኝተዋል

እስካሁን ባለው ሁኔታ የዐማራ ክልል ልዩ_ኃይል እና ሕዝቡ ያቀረበው ጥያቄ ትክክል መሆኑን መግለፁ ተነግሯል።
Source -EthiopiaDJ