August 20, 2019

Source: https://amharic.voanews.com/a/is-ethiopia-8-20-2019/5050122.html
https://gdb.voanews.com/C179CA73-D5FD-46F9-BF49-AD8C18927B9C_cx0_cy6_cw0_w800_h450.jpg

ነሐሴ 21, 2019

ሶማሊያ የሚገኘው የእሥላማዊ መንግሥት ክንፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ጀሌዎችን ለመመልመል የሚያስችሉትን በአማርኛ በድምፅና በቪድዮ የተቀረፁ ጂሃዳዊ የቅስቀሳ ውጤቶችና ፅሁፎችን ሊያወጣና ሊያሠራጭ እንደሆነ ተገልጿል። ዋሺንግተን ዲሲ — 

እሥላማዊ መንግሥት ቡድን ለአዲሱ ዘመቻው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የጎሣና የፖለቲካ አለመረጋጋት አመቺ ሁኔታ እንደፈጠረለት ኬንያ ውስጥ የሚገኘው የሳሃን ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ማት ብራይደን ከአሜሪካ ድምፅ የሶማሊኛ አገልግሎት ባልደረባ ሃሩን ማሩፍ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አይሲስ በኢትዮጵያ?

by ቪኦኤ

16x9 Image

ትዝታ በላቸው

tbelach@voanews.com

ሶማልያ ያለው “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገለፀ

VOA : ሶማልያ ያለው “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገልጿል። ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ምልመላ የማካሄድ ዓላማ እንዳለው ያመለክታል ተብሏል።

ይህ ማስታወቅያ ባለፈው ወር በሦስት ደቂቃ ቪድዮ መልክ የተለቀቀው በፅንፈኛው ቡድን ደጋፊ ድረ-ገፆች ላይ ሲሆን ኦፊሴላዊው እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ሚድያ ደግፎታል። ቪድዮው የአማርኛ ቃላትን ተጠቅሟል፣ ተጨማሪ ጽሑፎችን በአማርኛ እንደሚያወጣም ተናግሯል ተብሏል።

ማት በረየደን የተባሉ ኬንያ ባለው የሳሃን ጥናትና ምርምር ተቋም የሚሰሩ ተንታኝ እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ያለመረጋጋት ሁኔታን ተጠቅሞ ሙስሊም ማኅበረሰብን የመስበክ ዓላማ አለው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም ተንታኙ ጽንፈኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድል እንዳለው ይታየዋል የሚል አመለካከት እንዳላቸው ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ብዙም ባይሳካለትም አፍሪካ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘትና እንቅስቃሴውን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ይላሉ ብራይደን።