August 21, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/139912

ሰኔ 15 በተገደሉት አቶ ምግባሩ ምትክ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሾመ አቶ ገረመው ገብረፃዲቅ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነው ተሾሙ።አቶ ገረመው ገብረፃዲቅ ከትናንት ጀምሮ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆነው እንደተሾሙ ታውቋል።ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ ከሐምሌ ወር 2005 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸውን ከአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አቶ ገረመው ገብረፃዲቅ የተሾሙት ሰኔ 15 በተገደሉት አቶ ምግባሩ ከበደ ምትክ ነው። አቶ ምግባሩ ከበደ ከክልሉ ርእሰ መስተዳደር ዶክተ አምባቸውና ረዳታቸው ከነበሩት ጋር መገደላቸው ይታወሳል።