የአማራ ሕዝብ ለውጥ!” የተባለውን የወያኔ/ኢሕአዴግን ድራማ ተከትሎ የብሔራዊ ባንክ በኦነጋውያን መወረርና በእጅጉ የተዛቡ አሠራሮች እንዲሁም ዝርፊያዎች ምክንያት አሁን ካለው ዘር ተኮር የፖለቲካ ኢኮኖሚ ሽሚያና አሻጥር አኳያ የማንም መጠቀሚያ ላለመሆን፣ ጥቅሙንም ለማንም አሳልፎ ላለመስጠትና ከሀገሪቱ የቢዝነስ እንቅስቃሴ የድርሻውን ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ የአማራ ባንክ የመመሥረት ፍላጎትና መነሣሣት ከመቸውም ጊዜ በላይ አይሎ መቀስቀሱ የሚታወስ ነው፡፡

አማራ በሀገሪቱ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፈጽሞ ተጠቃሚ እንዳይሆን በርትቶ ሲሠራ የቆየው አገዛዙ ታዲያ አማራ ባለሀብቶቹንና የቢዝነስ ሰዎቹን አቀናጅቶና አደራጅቶ የራሱን ባንክ (ቤተ ንዋይ) ከመመሥረቱና ከሀገሪቱ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ተጠቀሚ ከመሆኑ በፊት ተሽቀዳድሞ አህዮቹን የብአዴን ጭፍሮች በማሠማራት የአማራ ባንክ!” ብለው እንዲወጡ አደረገ፡፡

አገዛዙ ይሄንን ሲያደርግ የአማራ ሕዝብ እነኝህ በባንኩ አደረጃጀት በግልጽ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የብአዴን ሰዎች እያየ ብአዴንን አምኖ የባንኩን አክስዮን በመግዛት ባንኩን ይመሠርታል!” ከሚል እምነት አይደለም፡፡ መንገድ እንዲዘጉ ለማድረግ ነው እንጅ!!!

ጥቂት ቆይታቹህ የምታዩት ይሆናል ይሄ ባንክ አይመሠረትም፡፡ ዓላማው መንገድ በመዝጋት የአማራን ሕልም ማጨናገፍ እንጅ ባንክ መመሥረት አይደለምና፡፡ እርግጥ ነው ባንኩ የአማራን ሕዝብ አመኔታ አግኝቶ መመሥረት ቢችል አገዛዙ ደስታውን አይችለውም ነበር፡፡ ምክንያቱም ከዳያስፖራው (ከግዩራኑ) አማራ ሊገኝ የሚችለው ዶላር ወይም የውጭ ምንዛሬ በእጅጉ አማላይ ነውና!!!

ይሁንና ግን አማራ ብአዴን ቀንደኛ ጠላቱ መሆኑን ስለሚያውቅ ይሄንን ብአዴን የመሠረተውን ባንክ ተቀብሎ አክሲዮን ሊገዛ ስለማይችል ይሄ ሕልማቸው እውን ሊሆን እንደማይችል ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ስለሆነም አገዛዙ ባልበላም ላፍሰው!” በሚል የምቀኛ አስተሳሰቡ ቀድሞ መንገድ በመያዝ ወይም በመዝጋት አማራን ለማደናቀፍ ተነሣ አደናቀፈም!!!

ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ሕዝቡ አንደኛ ነገር የአማራ ባንክ!” የሚለው ሥያሜ ተወስዶበታልና በዚህ ሥያሜ ባንክ ማቋቋም አይችልም፡፡ ሥያሜ ባልቸገረ አማራን የሚገልጥ የሚወክል በርካታ ድንቅ ሥያሜ ማምጣት ይቻላልና፡፡ አስቸጋሪው ፈተና ግን ብአዴን ባንኩ እንዳይመሠረት ስለሚያደናቅፍ፣ ባለሀብቶችን ስለሚያስፈራራ ወንድ ሆኖ ይሄንን ትክክለኛ የአማራ ሕዝብ ባንክ ለመመሥረት የሚንቀሳቀስ ባለሀብትና የቢዝነስ ሰው አለመኖሩ ነው ችግሩ!!!

በባንኩ ምሥረታ ቀን በወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ በአደራጅነት ስማቸው ሲዘረዘር የሰማቹሃቸው ከሀገሪቱ የዞን ከተሞች እስከ ወረዳዎች አገዛዙ በማደራጀቱ እንቅስቃሴ በግልጽ የሚታወቁ ብአዴኖችን በፊትለፊት አሰልፎ ያሠማራውም ለዚህ ነው፡፡ ባለሀብቱንና የቢዝነስ ሰዎችን ነጻ የአማራ ባንክ እንመሠርታልን!” ብለው ብአዴንን እንዳይቀናቀኑ ለማስጠንቀቅና ለማስፈራራት!!!

ከላይ እንዳልኳቹህ አገዛዙ በዚህች ሀገር አማራን በፖለቲካው በኢኮኖሚው…. ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ነጻ ማንኛውም የአማራ ድርጅትና ተቋም እንዲኖር ፈጽሞ አይፈቅድምና ነው፡፡ በፖለቲካው ያልበሰለና አማራ ላለፉት 28 ዓመታት ምን ሲፈጸምበት እንደቆየ የማያውቅ የማይረዳም ሰው ይሄ ሊገባው አይችልም!!!

የብአዴኑ ባለሥልጣን አቶ መላኩ ፈንታ እስከአሁን ድረስ በሀገራችን የባንክ ምሥረታ ታሪክ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች በተገኙበት በባንኩ የምሥረታ ቀንና ቦታ ላይ ይህ የመሠረቱት ባንክ እስከአሁን ያለበትን ደረጃ፣ ባንኩን ለመመሥረት መነሻ የሆናቸውን ምክንያት፣ ፈቃድ ለማግኘት ያከናወኑትን ተግባራትና መሰል ጉዳዮችን ለማብራራት ባደረጉት ንግግር እነኝህን ሥራዎች ለማከናወን በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በባንኩ አደራጆች ምክንያት ባንኩ የፖለቲካ ተጽዕኖ ያረፈበት ለማስመሰል ይደረግ የነበረው ጥረት ትልቁና ከፍተኛው ችግራችን ነው፡፡ ይሄም የባንኩን ምሥረታ ለማደናቀፍ የሚደረግ ዕኩይ ጥረት እንደሆነ ሕዝቡ እንዲገነዘብ እንፈልጋለን!” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ሙሉ ንግግሩን ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው መመልከት ይችላሉ፡፡

https://youtu.be/_s1oXxMfovw

እንግዲህ ብአዴን ሊለን የፈለገው ባንኩን እያደራጀሁና እየመሠረትኩት ያለሁት እኔ ብሆንም ባንኩ ግን የአማራ ሕዝብ ባንክ ነውና የብአዴን ነው አትበሉ!” ነው፡፡ ይሄም ዓይናቹህን ጨፍኑ ላሞኛቹህ ዓይነት ንግግር መሆኑ ነው፡፡ ለስም ለስምማ እራሱ ብአዴንስ የአማራ ሕዝብ ድርጅት ነው!” ይባል የለ እንዴ??? ነገር ግን ነው ወይ?” ነው ጥያቄው!!!

ለማንኛውም በዚህ መልኩ አማራ የራሱን ነጻ ባንክ የማግኘት ፍላጎቱ በዚህ የወያኔ ባሪያ ድርጅት በነቀርሳው ብአዴን ተጨናግፏል፡፡ የብአዴን ጠላትነት እዚህ ድረስ ነው፡፡ ብአዴን ማለት ለአማራ ሕዝብ ጉሮሮ ላይ የተሰነቀረ አጥንት ማለት ነው፡፡ የማያስበላ፣ የማያስጠጣ፣ ጤናም የማይሰጥ ክፉ የክፉም ክፉ ጠላት!!!

በዚህ አጋጣሚ ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያው ጥቂትም እንኳ ሳያፍሩና ምን ይሉኝ?” ሳይሉ ዓይናቸውን በጨው አጥበው በመውጣት ይሄንን ባንክ ነጻ የአማራ ሕዝብ ባንክ አስመስለው እያወሩ አማራ አክሲዮን እንዲገዛ ወገባቸውን አስረው ሲወተውቱ የነበሩት የአማራ አክቲቪስት የአማራ ብሔርተኛ ነኝ!” ባዮች በሙሉ የቀንደኛ ጠላታችን የነቀርሳው ብአዴን ተከፋይ ቅጥረኞች መሆናቸውን ዕወቁ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com