mission accomplished! አለ ፈረንጅ፡፡ አብኖች ተልእኳቸውን ጨርሰዋል መሰለኝ በእርስበርስ መናቆር ሰበብ አብንን ሊያፈርሱት ነው፡፡
በአብን አመራሮች የእርስበርስ መናቆር አዲስ ነገር የሰማን አይመስለኝም፡፡ አብን በብአዴን ባለሥልጣናት መመሥረቱን እንደሁ ከመጀመሪያውም ስነግራቹህ መቆየቴን የምታስታውሱ ይመስለኛል፡፡
ምናልባት በዚህ ሽኩቻ ሰበብ አብን የሚፈርስ ከሆነ ይህ የማፍረሻ ምክንያት አስቀድሞ የታቀደ እንጅ በድንገት የተፈጠረ አለመሆኑን ልብ በሉ፡፡
የአማራ ሕዝብ ጥያቄ፣ ጥቅም፣ መብት፣ ፍላጎት፣ ደኅንነት፣ ህልውና በሰላማዊ ትግል እንዲመለስ ወያኔ/ኢሕአዴግ በቁሙ እስካለ ጊዜ ድረስ ፈጽሞ መቸም ቢሆን በምንም ተአምር የማይፈቅድና ይሄንንም ከመጀመሪያው ጀምሮ ከእነ ፕሮፌሰር ዐሥራት ወ/ኢየሱስ እስከ ትናንትና በእነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ድረስ በወሰደው ግፍ የተሞላበት አንባገነናዊ ፀረ አማራ እርምጃ በመውሰድ አረጋግጦ እያለ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ፣ ጥቅም፣ መብት፣ ፍላጎት፣ ደኅንነት፣ ህልውና በሰላማዊ ትግል የሚመለስ አስመስሎ የአማራን ሕዝብ በማታለል በማጃጃል እጅግ ውስን ገንዘቡን፣ ውስን ጉልበቱንና የሰው ኃይሉን፣ በተለይም ደግሞ አማራ ካለበት እጅግ አሳሳቢ የህልውና አደጋ አኳያ አንዲቷን ሰከንድ እንኳ ብትሆን ፈጽሞ በከንቱ ሊያባክናት የማይገባውንና ካባከናትም ህልውናውን ይበልጥ ለአደጋ እንዲዳረግ የሚያደረገውን የማይተካ እጅግ ወርቃማ ጊዜውን በከንቱ እንዲያባክን፣ እንዲያጠፋ፣ እንዲያቃጥል ማድረግ እንደነበረ ብአዴኖች አብንን የመሠረቱበት አንዱ ዓላማ በተደጋጋሚ ስነግራቹህ ቆይቻለሁ!!!
“አብን ከተመሠረተ አንድ ዓመት አይደለም ወይ በዚህም አንድ ዓመት ብቻ ይሄንን ተልእኮ ፈጽሞ ለመፍረስ ተዘጋጀ ማለት ያስኬዳል ወይ?” የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፡፡ ጊዜው አጭር ቢሆንም አብን በዚህች አጭር ጊዜ ለአገዛዙ ያስመዘገበው ድል ግን ከፍተኛ ነው፡፡ አብን በዚህች አጭር ጊዜ ለአገዛዙ ከሠራው ትልቅ ሥራ ወይም ድል እራሱን ለአማራ ሕዝብ ጥሩ አማራጭ አስመስሎ በማቅረብ አማራ አገዛዙ “ለውጥ!” ብሎ ያወጀውን ሐሰተኛ የሽግግር ጊዜ ክፍተት፣ አጋጣሚ ወይም ዕድል በመጠቀም ብአዴንን ከልቶ ሊያሥተዳድረው፣ ታግሎ ሊያታግለው የሚችል የራሱን ትክክለኛ ድርጅት ማቋቋም ወይም መመሥረት እንዳይችል አብንን ለመመሥረት ከመታዘዛቸው ወይም ከመመልመላቸው በፊት ስለ አማራ ሕዝብ አንዲትም ነገር ተንፍሰው የማያውቁ ይልቁንም የብአዴን ካድሬ ሆነው አማራን ለትግሬ/ወያኔ ሲሉ ሲያስበሉና ወያኔን ሲያገለግሉ የነበሩ የብአዴን ካድሬዎችንና ከእነሱ ውጭ ከሆኑት ደግሞ “አማራ የሚባል ብሔረሰብ የለም!” የሚል አቋም ያራምዱ የነበሩትን ሰብስቦ ብአዴን የመሠረተውን ይሄንን አብንን ተስፋ አድርጎ ትክክለኛ የአማራ ድርጅቱን በትክክለኛ፣ ተማኝ፣ ሐቀኛና ቆራጥ ልጆቹ ከመመሥረት እንዲገታ አድርጎ አጃጅሎ አማራ ወያኔ ለማስመሰል ብሎ ያወጀውን የለውጥ ጊዜ ወይም አጋጣሚ ሳይጠቀምበት እንዲያልፍ ማድረጉ ነው አብን ለወያኔ/ኢሕአዴግ ያስመዘገበው ትልቁ ድል!!!
ከዚህ በኋላ ያለው ጊዜ ደግሞ እንኳንና አዲስ የፖለቲካ ድርጅት ሊመሠረት ይቅርና አዲስ በጸደቀው አፋኝ፣ የማያሳትፍ፣ ገዳቢ፣ ገፍታሪ፣ ነቃይ የምርጫ ሕግ የቆዩትም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚዘጉበት፣ ከፖለቲካው መድረክ የሚሰናበቱበት፣ እንዲጠፉ የሚደረጉበት በመሆኑ አማራ “አብን አልሆነኝም አዲስ ድርጅት ልመሥርት!” ብሎ ቢያስብ እንኳ ሐሳቡን እውን ሊያደርግ የሚችልበት ዕድል ስለሌለ የአብን መፍረስ ለአገዛዙ ከሚሰጠው አገለግሎትና ጥቅም አኳያ ለአገዛዙ የሚያጎልበት ነገር አይኖርም!!! አሁን ገባቹህ አይደል አብን በአንድ ዓመት ከምናምን ጊዜው ምን ያህል ከፍተኛ ድል ለአገዛዙ እንዳስመዘገበና አገዛዙን እንደጠቀመ???
የማንም ሆዳም ቅጥረኛ መጫወቻ የሆነው ወገኔ ብቻ ነው የሚያሳዝነኝ!!!
በተለይ ደግሞ አብን ትክክለኛ የአማራ ድርጅት መስሏቸው አባል ሆነው ሕይዎታቸውን እስከመስጠት ድረስ ቆርጠው የተሰለፉ ንጹሕ፣ ተቆርቋሪ፣ ቆራጥ ወገኖች እና አሁንም አብን የአማራ ድርጅት መስሏቸው “የኔ ይቅርብኝ!” እያሉ የቻሉትን ያህል ሲረዱ የነበሩ ንጹሐን፣ ለወገን ተቆርቋሪና ቆራጥ ወገኖቻችን በጣም በጣም ያሳዝኑኛል!!!
ለእነኝህ ወገኖቻችን አጥብቄ ማሳሰብ የምፈልገው ነገር ቢኖር የአማራ ትግል እንዲህ የዋዛ አለመሆኑን ጠንቅቀው እንዲረዱ ነው!!! ጠላቶቻችን የያዙት ነገር በሆዳም ቅጥረኞቻቸው፣ በባንዶቻቸው፣ በባሮቻቸው በሚፈጽሙብን ክህደት የተሞላ ተደጋጋሚ ተስፋ አስቆራጭ ሴራ፣ ሸፍጥ፣ አሻጥር “በቃ ታግለን እራሳችንን ነጻ ማውጣት፣ ህልውናችንን፣ ጥቅማችንን፣ መብታችንን ማረጋገጥ አንችልም፣ ትግሉ ከአቅማችን በላይ ነው!” ብለን ፈጽሞ ተስፋ ቆርጠን ተሸንፈን በመቀመጥ የእነሱ የዘለዓለም ባሪያ ለማድረግ ነው የያዙት ጥረት!!!
አማራ በዚህች ዓለም የትኛውም ሕዝብ ተጋፍጦት የማያውቀውን የተወሳሰበ ፈተና ተጋፍጦ ያለ ሕዝብ መሆኑን ተረዱ!!! በመሆኑም ምንም ዓይነት ፈተና ፈጽሞ ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባም!!! ይልቁንም በማንነታችን ሳንፈልገውና ሳንጠራው በተጋፈጥነው የተወሳሰበ ፈተና ልክ እራሳችንን ጠንካራ፣ ጽኑ፣ ረቂቅ፣ ትጉ፣ ደፋር፣ ቁርጠኛ፣ ጨካኝ ማድረግ እንደሚኖርብን ተረድተን በመታገል ግዴታ የሆነብንን ትግል እንድንታገል ነው አጥብቄ የማሳስበው!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com