ባጠቃላይ ለኦሮሞ ሕዝብ የቆምን ነን!” የሚሉ ኦነጋውያን ስለ ፍትሕ ወይም ፍትሐዊነት፣ ስለ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ ስለ እኩልነት ነጋ ጠባ ሲለፍፉ ይሰማሉ፡፡ የሚገርመው ነገር ግን እነኝህ መሠረታዊ የመብት እሴቶች ወይም ጥያቄዎች ከእነሱም በኩል እንደሚጠበቁ ለቅጽበት እንኳ አስበውትና አክብረውት የማያውቁ፣ ጨርሶ ሊያከብሩትም የማይፈልጉ መሆናቸው ነው፡፡

ይሄንንም ነፍጠኛ!” እያሉ በንጹሐን የአማራ ተወላጆች ላይ በየስፍራው ሲፈጽሙት በቆዩትና እየፈጸሙትም ባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰትና አረመኔያዊ ጥቃት ወይም ግፍ እንዲሁም ከቋንቋ ጀምሮ የአማራ እሴት ነው!” በሚሉት ነገር ሁሉ ላይ በሚፈጽሙት ጥፋት ማረጋገጥ ትችላላቹህ!!!

ለምሳሌ ያህል አንድ ሰሞንኛ ጉዳይ እናንሣ፦ እነኝህ የኦሮሞ ድርጅት ነን!” የሚሉት ኦነጋውያኑ በአማርኛ ትምህርት በሚሰጡ ኦሮሚያ በሚሉት የሀገራችን ክፍል ባሉ ትምህርት ቤቶች እርምጃ እንደሚወስዱ ርዕሰ መሥተዳድራቸው መዛቱን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ት/ቤቶቹን የመዝጋት ፍጹም ተቀባይነት የሌለውና አንባገነናዊ የግፍ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

ትምህርት ማኅበራዊ አገልግሎት ነው፡፡ ትምህርት የዕውቀት ገበያ ነው፡፡ በአንድ ገበያ ውስጥ ነጋዴው የሚሸጠውን ሕጋዊ ሸቀጥ አትሸጥም!” ብሎ መከልከል አይቻልም፡፡ አንድ የግል ወይም የኮሚዩኒቲ (የማኅበረሰብ) ትምህርት ቤት ተማሪዎችን እስካገኘ ጊዜ ድረስ አይደለም በአማርኛ በዓረብኛ ወይም በእስፓኒሽ ላስተምር ቢል መብቱ ነው፡፡ እንደምታውቁት ኦሮሚያ በሚባለው የሀገራችን ትምህርትም ሆነ በተቀረው የሀገራችን ክፍል የእስልምና እምነት ተቋማትን ተተግኖ ትምህርት በዓረብኛ ይሰጣል፡፡ ድሮም ሆነ አሁን የሀገሪቱ የትምህርት ፖሊሲ “….ከእነኚህ የሀገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች ሌላ በየትኛውም የሀገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች ትምህርት መስጠት የተከለከለ ነው!” የሚል ድንጋጌ የለውም!!!

ገበያው ወይም ፍላጎቱ እስካለ ጊዜ ድረስና የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም እስካልጎዳ ጊዜ ድረስ ትምህርት ቤቶች ማስተማር፣ ዜጎችም የፈለጉትን ትምህርት በፈለጉት ቋንቋ መማር ሰብአዊ መብታቸው ነው፡፡ ለዚህም ነው በየትኛውም ሀገር የተለያዩ የባዕዳን የኮሚዩኒቲ (የማኅበረሰብ) እና የግል ትምህርት ቤቶችም የሚገኙት፡፡

እዚህ ከእኛ ሀገር ውስጥ በዛ ያለ ቁጥር ያላቸው የውጭ ዜጋ ማኅበረሰቦች ልጆቻቸውን በቋንቋቸው እንደሚያስተምሩ ሁሉ የእኛ ማኅበረሰብም ከአሜሪካ እስከ ዓረብ ሀገራት ድረስ በርከት ብለው በሚገኙባቸው ቦታዎች የራሳቸውን ት/ቤት ከፍተው በራሳችን ቋንቋ ልጆቻቸው እንዲማሩ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ዓለም አቀፍ አሠራር ነውና የትኛውም ሀገር ይሄንን የማኅበረሰብ (የኮሚዩኒቲ) እና የግል ትምህርት ቤት አገልግሎት አሰጣጥን ሲከለክል ተሰምቶ አይታወቅም!!!

የእኛ ጨቋኝ፣ አንባገነንና ደናቁርት ኦነጋውያን ግን ስለ ፍትሕ፣ ስለ ሰብአዊ መብት፣ ስለ ዲሞክራሲ፣ ስለ ዕኩልነት እያወሩ በደብረ ዘይት፣ በናዝሬት፣ በጅማና በሌሎች ከተሞች አማራንና በአማርኛ መማር የሚፈልገውን ማኅበረሰብ በገዛ ሀገራቸውና በገዛ ቋንቋቸው በአማርኛ ቋንቋ አትማሩም አንፈቅድም!” በማለት የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በመግፈፍ ሕገወጥና አንባገነናዊ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ!!!

እነሱ የፈጠራ ወሬ ፈልስፈው ለቋንቋቸው ክብር ሰጥቶ መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋቸው ያስተረጎመላቸውን፣ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚሠራጭ ራዲዮ ጣቢያን የከፈተላቸውን ዘውዳዊ ሥርዓት በሐሰት በመወንጀል በዐፄዎቹ ሥርዓት በቋንቋችን እንዳንጠቀም እንዳንናገር፣ እንዳንማር፣ ቋንቋችንን እንዳናሳድግ እንከለከል፣ እንጨቆን ነበር!” የሚሉትን የፈጠራ እርምጃ አሁን እነሱ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዜጎች ላይ በተግባር እየፈጸሙት ይገኛሉ!!!

የሚገርመው ይሄንን ሲያደርጉም የሰው ልጆችን ብሎም የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን እየጣሱ፣ እየገፈፉ፣ ፍትሕ እየነፈጉ እንደሆነ አለማሰባቸውና ማሰብም አለመፈለጋቸው ነው፡፡ የዚህን ያህል የተደፈኑና ማመዛዘን፣ ማገናዘብ የማይችሉ፣ ፈጽሞ ዘመኑን የማይመጥኑ፣ የጫካ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ደናቁርት ናቸው!!! እነኝህ ደናቁርት በምን ሞራላቸው (ቅስማቸው) ስለ ፍትሕ ስለ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ ስለ ዕኩልነት ለማውራት እንደሚደፍሩ ነው ግርም የሚለኝ ነገር!!!

እነኝህ ደናቁርት ይሄንን ጭቆና ወይም ኢፍትሐዊና አንባገነናዊ እርምጃ በየስፍራው ሲወስዱም የለውጥ መንግሥት ነኝ!” የሚለው አገዛዝም እንደቀድሞው ዘመኑ ይሄንን ሕገወጥና አንባገነናዊ እርምጃ ሲደግፍና ሲያባብስ እንጅ የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ከማስከበርና ፍትሕን ከማስፈን አኳያ አንዳችም የማስተካከያ ወይም የእርምት እርምጃ ሲወስድ አይታይም!!!

እጅግ የሚገርመው ጉዳይ ደግሞ ይሄንን ግፍ የሚፈጽሙት እነኝህ አካላት ግፉን የሚፈጽሙበት ቦታ የግራኝ አሕመድ ወረራ የፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ወደ ሀገሪቱ በመግባት ወረው የያዙት እንጅ የራሳቸው አለመሆኑ ነው፡፡ አሁን ሰፍረው ያሉበት የሀገራችንን ክፍል ወረው ሲይዙትም ነባሩን ማኅበረሰብ አረመኔያዊ በሆነ መንገድ በመጨፍጨፍ፣ የተረፈውን ደግሞ ሞጋሳ በሚሉት በኃይል ማንነትን የማስጣያና የማስቀየሪያ ሥርዓት በግዳጅ ወደ ኦሮሞነት ለውጠው ኦሮሞ በማድረግና ገርባ (ባሪያ) የማድረጊያ ሥርዓት ማንነትን የማጥፋት (identity assassination) ግፍ ፈጽመው መሆኑ ነው አስገራሚው ነገር!!!

ይሄንን ነውረኛና አረመኔያዊ (barbaric) ተግባር ምሁራን ነን!” የሚሉ የኦሮሞ ታጋይ ነን!” ባዮች ሳይቀሩ ያለ አንዳች መሸማቀቅና እፍረት እንደ መልካም ተግባር በተለያየ መድረክ በኩራት ሲናገሩት በተደጋጋሚ ሰምታቹሃቸዋል፡፡ ያኔ አያት ቅድመ አያቶቻቸው የፈጸሙትን አረመኔያዊና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውን ኋላ ቀር ተግባር ወይም ግፍ ዛሬ በሠለጠነው በ21ኛው መቶ ክ/ዘ በእኛ በባለርስቶቹ ላይ በኃይል ለመፈጸም መፈለጋቸው ነው ሌላው እጅግ አስገራሚው ነገር፡፡ ለእነኝህ ሰዎች ማንን? በማንስ መሬት ላይ? ነው እንዲህ ዓይነቱን እርምጃ ልትወስዱበት የሚያምራቹህ? ትንሽ ሕሊና የሚባል ነገር የላቹህም ወይ???” ብሎ የሞራልና የፍትሕ ጥያቄ ለእነሱ ማንሣት ከድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ከንቱ ድካም ነው የሚሆነው፡፡ የሞራልና የፍትሕ ጥያቄ ፈጽሞ የሚገባቸውና የሚረዱት ነገር አይደለምና!!!

ታዲያ ይሄንን ያህል ጠቦና ደድቦ ዜጎችን በራሳቸው ፍላጎትና ወጭ የሚያንቀሳቅሱትን የኮሚዩኒቲ (የማኅበረሰብ) እና የግል ትምህርት ቤት እንዳይኖር ለማድረግ እየሠራ እየተንቀሳቀሰ ያለ ኦሕዴድ የተባለ የኦነጋውያን የጥፋት ቡድን እንዴት ብሎ ነው ጎሳየ ወይም ብሔረሰቤ ነው!” ለሚለው አባላቱ የሀገሪቱን የሥራ ቋንቋ አማርኛን ሊያስተምር የሚችለው???

የጎሳ አባላቴ!” ለሚሏቸው ማስተማሩ ቀርቶ በአማርኛ መማር ለሚፈልገው ኦሮሚያ በሚሉት የሀገራችን ክፍል ከተሞች ላለው ሰፊው ኅብረተሰብ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቱን አክብሮ በመንግሥት ት/ቤቶች በፍላጎታቸውና በምርጫቸው እንዲማሩ ቢያደርግ ራሱ ትልቅ እርምጃ ነው!!!

እንደ ደንቡማ ቢሆን ኖሮ እንደሌሎች የሬዴሬሽን አሥተዳደር እንደሚከተሉ ሀገራት ሁሉ የሀገሪቱን መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲማሩ የማድረጉ ጉዳይ ጥያቄና መልስ የሚያስነሣ ጉዳይ ባልሆነ ነበር፡፡

እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ብናስብ፣ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት ቢኖር ሁላችንም እንደ የአንድ ሀገር ሕዝብነታችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁሉም ጎሳና ብሔረሰብ ከሀገሪቱ ቋንቋዎች ውስጥ ብቃት ያለውን መርጠው እርስበርስ የምንግባባበት አንድ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ይኖረን ዘንድ የውዴታ ግዴታ ነውና የላቀ ብቃትና የተሟላ ቋንቋ የሆነውን አማርኛን የመማሩ ጉዳይ የሚያጠያይቅ ባልሆነ ነበር፡፡

ይህ እንዳይሆን ያደረገውና የሚያሳዝነው ነገር የሀገሪቱ አሥተዳደር ሥርዓት የፌዴሬሽን አሥተዳደር ነው!” ይባል እንጅ በተግባር እየተፈጸመ ያለው ግን የኮንፌዴሬሽን አሥተዳደር በመሆኑ ነው የምታዩት ሁሉ ውጥንቅጥና ምስቅልቅል ሊከሰት የቻለው!!!

መጀመሪያ እንደ አንድ ኃላፊነት እንደሚሰማውና ተጠያቂነት እንዳለበት አካል በሀገሪቱ እየሠራ ያለውን የአሥተዳደር ሥርዓት ፌዴሬሽን ነው ወይስ ኮንፌዴሬሽን???” የሚለውን ለይተው ይወቁ እኛንም ያሳውቁና ከዚያ ሕገመንግሥቱ ይከበር!” ይበሉ፡፡ አሁን ግን እያደረጉ ያሉት ፌዴሬሽን ነው!” ብለው ሲያበቁ የኮንፌዴሬሽንን ክዋኔና ተግባራት ነው እየፈጸሙ ያሉት፡፡ ይሄንን እያደረጉ ባሉበት ሁኔታና ሕገመንግሥታቸውም እንዲህ ውሉ የጠፋበት፣ የተደናበረና የተሳከረ በሆነበት ሁኔታ በሀገሪቱ ሕዝብ መሀከል ብሔራዊ መግባባትን (national consensus) ማምጣት፣ የሕግ የበላይነትንና ተጠያቂነት ማስፈን፣ ሀገርን እንደ ሀገር፣ ሕዝቧንም እንደ ሕዝብ አረጋግቶ ማሥተዳደርና ህልውናቸውን ማስቀጠል እንዴት ይቻላል???

በኮንፌዴሬሽን አሥተዳደር እንጅ በፌዴሬሽን አሥተዳደር ሥርዓት ውስጥ በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ!” የሚባል ነገር የት ሀገር ነው ታይቶና ተሰምቶ የሚታወቀው??? ልክ እኮ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከዚህ በፊት ያልነበረች፣ በታሪክ የማትታወቅ አሁን በዚህ ዘመን የሆኑ ሀገሮች በመፈቃቀድ ተሰባስበው በኮንፌዴሬሽን የፈጠሯት አዲስ ሀገር እኮነው የሚያስመስሉት!!!

በፌዴሬሽን ሥርዓት ውስጥ ሉዓላዊ ሀገር እንጅ ሉዓላዊ ክልል የሚባል ነገር አለ እንዴ??? “ክልሎች ሉዓላዊ ናቸው!” ካላቹህ በግልጽ የኮንፌዴሬሽን ሥርዓት ውስጥ ነው ያለነው!” በሉ እንጅ የፌዴሬሽን ሥርዓት ውስጥ ነው ያለንበት!” እያላቹህ ሕዝብን አታወናብዱ አታጭበርብሯ ታዲያ???

ይሄ ዓይን ያወጣ ውንብድናና ዕብደት አይደለም ወይ ወገኖች??? ይህ ተግባር የጤነኛ ተግባር መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል ወይ??? እንዴት ሆኖ??? ይሄ ሆኖ ሲያበቃ ታዲያ የምናየው ምስቅልቅል ባይፈጠር ነው የልቅስ ሊገርመን የሚገባው!!!

እውነትን በማይቀበል፣ ከተጨባጭ ሀቅ ጋር በተጣላ በውንብድና አሥተዳደር ውስጥ ፍትሕን፣ መብትን፣ ሰላምና መረጋጋትን የሚጠብቅ ሰው ካለ ሲበዛ ቂል መሆኑን ልነግረው እወዳለሁ!!! አዳሜ የልቅስ ቶሎ ነቅተህ ጨክነህ ተነሣና ይሄንን የውንብድና ጨቋኝ አገዛዝ የከፋ ነገር ሳያመጣብህ ቅደምና ነቅለህ ብትጥለው ነው የሚያዋጣህ!!!

ወይ ደናቁርትነታቸውን፣ ጨቋኝና አንባገነን ተፈጥሮ ያላቸው፣ ዘመኑን የማይመጥኑ ከንቱዎች መሆናቸውን አውቀው አልቻልንበትምና፣ ዘመኑም አልተቀበለንምና ተረከቡን!” አይሉ፣ ወይ ደግሞ ችለው አልቻሉበት በምን ሒሳብ ነው ታዲያ ሀገርና ሕዝብ ፍዳቸውን ሊያዩ የሚገባው???

ለፍትሕ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለዕኩልነት ቆመናል፣ እንታገላለን!” የምትሉ ከፖለቲካ ድርጅት እስከ የእምነት ተቋም፣ ከሰብአዊ መብት ተሟጋች እስከ ጋዜጠኛ፣ ተንታኝና አክቲቪስት ያላቹህ ሁሉ ይሰሟቹህ ከሆነ አዲሱ ዓመት ብቶ የትምህርት ዘመኑ ከመጀመሩና ችግር ከመፈጠሩ በፊት እነኝህን ለዘመኑ የማይመጥኑ ጥጋበኛ፣ ጨቋኝ፣ ደናቁርትና ቢጤዎቻቸውን አንድ ትሏቸው ዘንድ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!!

ይህ ከታች ያለው ሊንክ የቴሌግራም ቻነሌ ነው ተቀላቀሉኝ አመሰግናለሁ!

https://t.me/Yeamsalu

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com