September 4, 2019

Source: https://fanabc.com/2019

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከልክ በላይ ለረጅም ሰዓታት እንቅልፍ መተኛትም ይሆን በቂ እንቅልፍ አለመተኛት የልብ ህመም የመጋለጥ እድልን ከፍ እንደሚያደርግ ጥናት አመለከተ።

አንድ ሰው በቀን ውስጥ የሚተኛው እንቅል ቢያንስ 6 ሰዓት፤ ቢበዛ ደግሞ 9 ሰዓት ማለፍ  እንደሌለበት ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ነገር ግን በቀን ውስጥ ከ6 ሰዓታት ላነሰ ጊዜ መተኛት የልብ ህመም ተጋላጭነትን በ20 በመቶ ከፍ የሚያደርግ ሲሆን፥ ከ9 ሰዓት እና ከዚያ በላይ መተኛት ደግሞ የልብ ህመም ተጋላጭነትን በ34 በመቶ ከፍ እንደሚያደርግ ነው አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ካርዲዮሎጂ ይፋ ያደረገው ጥናት።

የኮሎራዶ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ባለሙያ ሰሊን ቬተር እንደተናገሩት፥ የጥናቱ ውጤት በእቅልፍ የምናሰልፈው ሰዓት ከልብ ጤንነት ጋር ግንኙነት እንዳለው ያረጋገጠ ነው፤ ይህ ደግሞ ለሁሉም እውነታን ይዞ የመጣ ነው ብለዋል።

ተመራማሪዎች ጥናቱን ለ7 ዓመታት ያካሄዱ ሲሆን፥ በጥናቱ ወቅትም እድሜያቸው በ40 እና 69 ዓመት መካከል በሆኑ በ461 ሺህ ሰዎች ላይ ክትትል አድርጓል።

በጥናታቸውም ተመራማሪዎቹ እንቅልፍን ከመጠን በላይ ማብዛትም ይሆን በጣም ለትንሽ ሰዓት መተኛት በልብ ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል አረጋግጠዋል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ከለጻ አነድ የአንድ ሰው ጤናማ እንቅል ሊሆን የሚገባው ከ6 ሰዓት አስከ 9 ሰዓት ብቻ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

በየቀኑ ለ5 ሰዓታት ብቻ እንቅልፉን የሚተኛ ሰው በቀን ለ7 እና 8 ሰዓታት ከሚተኛ ሰው ጋር ሲነፃፀር የልብ ህመም ተጋላጭነቱ በ52 በመቶ ጨምሮ መታየቱንም ገልፀዋል።

እንዲሁም በቀን ከ10 ሰዓት እና ከዚያ በላይ የሚተኙ ሰዎችም የልብ ህመም ተጋላጭነታቸው በእጥፍ የጨመረ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ www.upi.com/HealthFiled in: