የቤተክርስቲያኗ ላዕላይ አካል ሲኖዶስ የዕኩያኑ የቅጥረኞቹ የአሸባሪዎቹ የእነ በላይ መኮንን እንቅስቃሴ የቤተክርስቲያን ውክልና እንደሌለውና አጥብቆም እንደሚያወግዘው ገልጾ የሚመለከተው የሕግ አካልም ይሄንን ያለ ቤተክርስቲያኗ ዕውቅናና ፈቃድ የሚሰጥን መግለጫና እንቅስቃሴ እንዲያስቆም ቢጠይቅም ቅጥረኞቹ ግን የአገዛዙ ሙሉ ድጋፍ አላቸውና የተናገሩትን ከማድረግ የገታቸው አንድም አካል ሳይኖር ያውም በመንግሥት ጽ/ቤት ውስጥ (የኦሮሚያ ዕንባ ጠባቂ ቢሮ) እንሰጣለን ያሉትን መግለጫ ሰጥተዋል!!!

ከጉዟቸውም የሚገታቸው አንድም አካል እንደማይኖርና ዓላማቸውን ለማሳካት አይደለም ሕዝብ የሚሰማው ወገናችን!” ካሉት አሸባሪ ግለሰብ ጃዋር ጋር ይቅርና ከሰይጣንም ጋር ቢሆን እንሠራለን፣ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፣ በአዲስ አበባ አብያተክርስቲያናት በኦሮምኛ እንዲቀደስ እናደርጋለን….!” በማለት ለቤተክርስቲያን ነው ከሚሉት ጉዳይ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የጽንፈኛ ጠባብ የኦሮሞ ብሔርተኞች ተላላኪ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ነገሮችን ተናግረዋል!!!

እንግዲህ ይታያቹህ አንድ ክርስቲያን ነኝ!” ነኝ የሚል ሰው እንዴት ሆኖ ነው ከሰይጣን ጋር ሠርቶ ለቤተክርስቲያን ልማትና እድገት አመጣለሁ!” ብሎ ሊያስብ የሚችለው??? እግዚአብሔር አፋቸውን ከፍቶ ፊታቸውን ጸፍቶ በማናገር ማንነታቸውን ሲገልጥባቸው ነው እንጅ የቤተክርስቲያን ብቸኛ ጠላት የሆነው ሰይጣን አባሪ ተባባሪ ሆነው እንዴት ነው ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ነገር ሊያመጡ የሚችሉት???

እነኝህ ሰዎች እንዲያው የሚናገሩትንም ነገር ጨርሶ አያውቁም እንዴ??? ካህን እኮ ከአፉ የሚወጡ ቃላትን ለይቶ መርጦ ጠንቅቆ አራቆ ነው የሚናገረው፡፡ መደዴ የሆነ ነገር አይናገርም፡፡ ነው ወይስ ሰዎቹ ካህናት ናቸው!” ተባሉ እንጅ ሌላው ቀርቶ ስለሰይጣን ፀረ ቤተክርስቲያንነት እንኳ ከነአካቴውም የማያውቁ ባጠቃላይ ስለ መንፈሳዊ ነገር ጨርሶ የሚያውቁት ነገር የሌላቸው ወደ ቤተክርስቲያን ሆን ተብሎ እንዲገቡ የተደረጉ የጽንፈኛው ጠባብ ቡድን ጀሌዎች ናቸው???

ይሄ የእነ አቶ በላይ መኮንን ፀረ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው ሐቅ ቢኖር በፀረ ቤተክርስቲያንና በፀረ ኢትዮጵያ የጥፋት ትግል ዙሪያ አክራሪ እስላሞች ወይም አሸባሪዎች፣ መናፍቃኑና ጽንፈኛ ጠባብ ብሔርተኞች ተባብረውና ተቀናጅተው የሚሠሩ መሆናቸውን ነው!!!

ስለ እነዚህ ሰዎች እንቅስቃሴ የዛሬ ሁለት ሳምንት ምን ብየ ነግሬያቹህ ነበረ??? እስኪ ላስታውሳቹህ፦

“”እግዚአብሔር ግን በአጋንንት አሽከሎች በትግሬ ላይ የሚያወርደው መዓት ምን ይሆን???

የኢትዮጵያን ታሪክ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከጥግ እስከ ጥግ ብታነቡ አንድ የምታገኙት ጠቅለል ያለ መረዳት ምን መሰላቹህ አማራ ሲሠራ ትግሬ ሲያፈርስ፣ አማራ ሲሠራ ትግሬ ሲያፈርስ፣ ይሄ እየተመላለሰ ሲደጋገም እዚህ መድረሳችንን ነው፡፡

ትግሬ ትናንት በጣሊያንና በእንግሊዝ ወረራ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በፊት ከጥንት ጀምሮ ዕድሜ ዘመናቸውን እዚህች ሀገር ከገቡ ጊዜ ጀምሮ ወራሪ በመጣ ጠላት በተነሣ ቁጥር ከጠላት ጋር በመሰለፍ በባንዳነት እያደሩ አማራ የገነባውን ሲያፈርሱ ነው የኖሩት!!!

ሰሞኑን ኦሮሞ ነን!” የሚሉ ካህናት ተብየ የጃዋር ቅጥረኞች የራሳችን!” የሚሉትን የኦሮሚያ ቤተክህነት!” ለመመሥረት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው የኦነግ ቄስና ቆሞስ ትናንትና በአሸባሪው ጃዋር ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል፡፡

ይህ ተግባር ነፍሳቸውን ይማረውና እንደ እነ አቡነ እንድርያስ ላሉ በሕይዎት ለሌሉ ጠንካራ የኦሮሞ ተወላጅ ጳጳሳትና አሁንም በሕይዎት ላሉት ከአምስት በላይ የኦሮሞ ተወላጅ ጳጳሳት ትልቅ ስድብ ነው!!!

እነኝህ የኦነግ ተቀጣሪዎች ይሄንን የሚሉት ከራሳቸው አመንጭተው እንዳይመስላቹህ፡፡ እኔ ወያኔ ይሄንን ፈተና በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ በማምጣት ቤተክርስቲያንን ሊያፈርሳት እንደሆነ የገባኝ ገና አስቀድሞ ትግራይና ውጭ ሀገራት ባሉ ቅጥረኞቹ ከወራት ምናልባትም ከዓመት በፊት ክልሎች የየራሳቸውን ነጻ ቤተክህነት መመሠረት አለባቸው!” እያሉ መለፈፍ ሲጀምሩ ነው፡፡ ኧረ እነሱማ እንዲያውም “…የየራሳቸውን ሲኖዶስ!” ሲኖዶስ ነበር ያሉት፡፡

ቆየት አሉና ደግሞ ተጋዳላይ አቦይ ማትያስም ምንም ነገር በሌለበት የሌለ ነገር ፈጥረው በማውራት ዛቻ እየተሰነዘረብኝ ነው መንግሥት ደኅንነቴን የማያስጠብቅ ከሆነ ደኅንነቴ ወደሚጠበቅበት (ትግራይ) እሔዳለሁ!” በማለት የላይኛውን የወያኔን ሸፍጥ መሬት ለማስያዝ ሞከሩ፡፡ ከዚያም ውስጥ ውስጡን ብዙ ነገር ሲሠሩና ሲያደራጁ ቆዩና ይሄ አሁን የምናየው የኦሮሚያ ቤተክህነት ምንንትስ የሚባለው ውዥንብርና ሽብር እንዲፈጠር አደረጉ….!” ብያቹህ ነበረ፡፡

ሲኖዶስ ነኝ ከሚለው የቤተክርስቲያኗ የመጨረሻ ሥልጣን ካለው አካል ጀምሮ እስከ ታች ምእመናን ድረስ ያለው ግን ትኩረት ያደረገው ምንም በማያውቁትና ታዘው በሚሠሩት በእነ በላይ መኮንን ላይ ነው፡፡ ችግሩን ከምንጩ ማየትና መቅረፍ እስካልቻልን ድረስ አንድም የሚመጣ መፍትሔ እንደሌለና ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከመፍረስ እንደማናድናት ላረጋግጥላቹህ እወዳለሁ!!!

ከባድ ተልእኮ ተሰጥቶት የመጣው መናፍቁ ዐቢይ በአሜሪካ ጉብኝቱ ወቅት ኦርቶዶክስ ሀገር ናት!” ብሎ መናገሩን ታስታውሳላቹህ፡፡ ምናልባት አሁን ላይ ብዙ ሰዎች ዐቢይ እንዲያ ማለቱ ሲሸነግለን ነበር!” ይሉ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ነቃ ያለ ሰውም ምናልባት ይሄ መናፍቅ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት!’ እያለ ሸንግሎ እኛን አዘናግቶና አስተኝቶ ጉድ ሠራን እኮየሚል ይኖር ይሆናል፡፡

ዐቢይ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት!” ሲል ግን ማለቱ የነበረው ሀገር በመሆኗ ወይም የሀገር የጀርባ አጥንት በመሆኗ ዋነኛ ኢላማችን ናት፣ አከርካሪዋን እንደሰበርነው ሁሉ አቃጥለን፣ ገነጣጥለን እናፈራርሳታለን፣ አመዷንም በእጃቹህ እናስረክባቹሃለን!” ማለቱ ነው የነበረው፡፡ ይሄንን ማለቱ እንደነበር ቢያንስ አሁን በዚህ ጊዜ የማይረዳ ሰው ካለ የሰው ጭንቅላት ሳይሆን ድንጋይ እንደተሸከመ ይወቀው!!!

እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹህ? ይሄ ሁሉ የፀረ ቤተክርስቲያን የአሕዛብ፣ የመናፍቃንና የከሃድያን የጥፋት ተግባር በአንድ ጀምበር ለዚህ ደረጃ የደረሰ ይመስላቹሃል???

የኛ ነገር ሁልጊዜ ግርም የሚለኝ ነገር ቢኖር ሁል ጊዜ መዘግየት የሚያስከፍለውን ከባድ ዋጋ እያወቅንና እየከፈልንበትም ሳንማርና ሳንታረም እየቀረን ይች ጥሬ ካደረች…!” ማለት በነበረብን ጊዜ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ!” ብለን ለሽ ብለን ተኝተህ እንቆይና ጅቡ የሚበላውን በልቶ ከሔደ በኋላ የምንጮኸው ከንቱ ጩኸት ነገር ነው!!!

* የጥፋት ኃይሎች በሕገመንግሥታቸው የእምነት ተቋማት ለአምልኮ ከተፈቀደላቸው ስፍራ ውጭ በየመንገዱ፣ በየፌርማታው፣ በሕክምናና በትምህርት ተቋማት፣ በሌሎች ሕዝብ በሚሰባሰብባቸው ስፍራዎች ሰዎችን በመስበክ አባል ለማድረግ መንቀሳቀስ፣ ጥቅማጥቅምን በመደለያነት በማቅረብ የእምነት ተከታይ ለማድረግ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው!” ብለው ሕግ ደንግገው እኛን ካዘናጉና ካጃጃሉን በኋላ መናፍቃኑን ከተጠቀሱት ስፍራዎችም ባለፈ ቤት ለቤት እያንኳኩ በመስበክ፣ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ሳይቀር ወፍጮ ቤት፣ ትምህርት ቤት፣ የጉድጓድ ውኃ፣ የእህል የዘይትና የገንዘብ እርዳታ እየሰጡ የማስገደድ ያህል እየተጫኑ በጎችን (ምእመናንን) በመንጠቅ ከበረታቸው (ከቤተክርስቲያን) ጠርገው እንዲወስዱ ሲያደርጉና ተኩሎቹ እላያችን ላይ እንደዋርካ እንዲንሰራፉብን ሲያደርጉ ዛሬ ቤተክርስቲያን ተደፈረች!” ምንንትስ እያልክ የምትንጫጫው ከሲኖዶስ ተብየው እስከ ሰባኪ ነኝ!” ባዩ አስመሳይ የምላስ ነጋዴ ሁላ ያኔ ይሄ ሁሉ ጥፋት ሲፈጸም የት ምንስ እየሠራቹህ ነበር???

* ጭራሽ እንዲያውም በተባባሪነት ይሄ ሁሉ ጥፋት በቤተክርስቲያን ላይ እንዲደርስ ያደረገው ወያኔ ቤተክርስቲያንን እንዲቆጣጠር ወደቤተክርስቲያኗ ያስገባው በታጋይ አቦይ ጳውሎስ የሚመራው ፀረ ቤተክርስቲያን የወንበዴ ቡድን አልነበረም ወይ ይሄ ሁሉ የምእመናን ዝርፊያና ሌሎች ጉዳቶች በቤተክርስቲያን ላይ እንዲደርስ ሲደረግ የነበረው??? ይሄንን የማያውቅ አለ???

* ያኔ እኛ ይሄንን ሕገወጥ ፀረ ቤተክርስቲያን የምእመናን ዝርፊያና ውንብድና ከቤተክርስቲያን ዐውደ ምሕረት እስከ የሕትመት ሚዲያ፣ ሶሻል ሚዲያ ከመጣ በኋላም በሶሻል ሚዲያ እያወገዝንና እየተቃወምን ስንጮህና ስንት ዋጋ ስንከፍል ሰሚ አጥተን ዛሬ የምትንጫጫው አስመሳይ ሁሉ ያኔ በቤተክርስቲያን ላይ ዓይን ባወጣ ሕገወጥ አፈጻጸም ያ ሁሉ ጥፋት እንዲደርስባት ሲደረግ የትና ምንስ ስታደርግ ነበር??? መስለህ እያደርክና እየታዘዝክም ጭምር አልነበረም ወይ ቤተክርስቲያንን አብረህ ስታጠፋ የነበርከው???

* ከዚያ ሁሉ በኋላስ የኦርቶዶክስንና የአማራን አከርካሪ እንዳያንሠራራ አድርገን ሰብረነዋል!” ተብሎ አገዛዙ በአውራ ባለሥልጣኑ አቦይ ስብሐት አንደበት በአደባባይ ሲደነፋ እያንዳንድሽ ሰምተሽ እንዳልሰማሽ ዓይተሽ እንዳላየሽ በመሆን ምንም እንዳልተፈጠረ ኑሮሽን ትኖሪ የነበርሽ አይደለሽም ወይ??? ዛሬ ተቆርቋሪ መስለሽ የምትደነፊው ከጳጳሳት እስከ ተራ ምእመን ያለሽ እያንዳንድሽ ያኔ የትና ምንስ እያደረግሽ ነበር???

* እኛን ፖለቲካና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው!” እንድንልና ከፖለቲካው እንድንርቅ አድርገው ሲያበቁ ሥልጣን የተባለን ሁሉ በመናፍቅ በማስያዝና ሥልጣናቸውን በመጠቀምም እኛን ሌላው ቀርቶ በገዛ ሀገራችን ማተብ ማሰር እንኳ ሳይቀር ከልክለው ከተማሪዎች አንገት ላይ ማተብ እየበጠሱ እነሱ ግን ፓስተር ከአሜሪካ በማስመጣት ፓርላማ ውስጥ ሲያጎሩ የቤተክርስቲያን ክፉኛ መጎዳትን ዛሬ ገና የሰማህ መስለህ ዘራፍ!” የምትለው እግዚአብሔርንም እንደሰው ማታለል የምትችል የሚመስልህ ቀሳጢ ሁሉ ያኔ የትና ምንስ ስታደርግ ነበር???

በጊዜውም ያለጊዜውም በቦታውም ያለቦታውም ጸንቶ መገኘት ማለት ይሄ ነው ወይ??? 2ኛ ጢሞ. 42 አሁንም ቢሆን ቁጭታችን፣ መቆርቆራችን፣ መነሣሣታችን ከልብ ከሆነ ምንም ባልነበር፡፡ የቀደመው በደላችንም ባልታሰበብን ነበር፡፡ እኔ ግን ይሄ ሁሉ ጫጫታ ማስመሰል እንጅ ከልብ ተቆርጦና ተጨክኖ የሚጮህ የአማኒ ጩኸት አይመስለኝም!!! እውነተኛ ባልሆነ በተለያየ ምክንያት ነው ጩኸቱ ከየአቅጣጫው እየተጮኸ ያለው፡፡ ሁሉንም ከፊታችን የምናየው ይሆናል!!!

ከልብ የምር ለቤተክርስቲያን እዚህ ሁሉ ኪሳራና ምስቅልቅል መድረስ በማዘን ተጠያቂነት ተሰምቷቹህ እኔን ያስቀድመኝ!” እያላቹህ እየጮሃቹህ ያላቹህ ክርስቲያኖች ካላቹህ ግን ግፉ በርቱ!!! ዋጋቹህም በሰማይ ታላቅ ነውና ደስም ይበላቹህ!!!

ሲነቅፏቹህና ሲያሳድዷቹህ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባቹህ ብፁዓን ናቹህ። ዋጋቹህ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላቹህ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና!” ማቴ. 511-12

ድል ለቤተክርስቲያን!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ቴሌግራም ቻነል

https://t.me/Yeamsalu

ኢሜይል

amsalugkidan@gmail.com

አመሰግናለሁ!!!