September 2-2019
ምዕራብ አውሮፓ፣ ካናዳ፣ አሜሪካና አውስትራሊያ እየኖሩ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ የአንድነት ፀረ የሆነው ጠባብ ብሄርተኝነትን የሚስብኩና ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲዘምት የሚቀሰቅሱትን ቀኝ አክራሪ ኦነጎች እና ቀኝ አክራሪ ቄሮዎች ማለቶ ነውን?
የመደብለ የፖለቲካ ፓርቲዮች፣የመደብለ ባህሎችና ቋንቋዎች፣የወል፣የቡድንና የግል ወዘተርፈ መብቶችና ነጻነት በተከበሩበት እና የበሰለ ዲሞክራሲ (matured democracy)ባሉባቸው አገሮች ኖረው ወደ አገር ቤት ሲሄዱ እነዚኅን እሴቶች የሚጻረሩ ተግባሮች ሲከውኑ ይታያሉ ።
ያደጉና የሰለጠኑ አገሮችን ሸቀጦች/ኮሞዲቲስ በመግዛትና በመጠቀም ሰለጠኑ እንጂ ሥልጡንና ትላልቅ አስተሳሰባቸውን በመቅሰም አልሰለ ጠኑም ።
ያደጉ አገሮችን የመጀመርያ፣የሁለተኛ እና የሶስተኛ ደረጃ ድግሪ ያላቸው ቢኖሩም ፣ ያንን እውቀት (1) እንደሸቀጥ ሽጠው ማለት ተቀጥረው ደሞዝ ከማግኘት (2) እኛና እነዚያ፣ እኛና እነሱ ከማለት ጥላቻ ለላቀ ስልጡን አስተሳሰብ አላዋሉትም። አብሮ መታየት ያለበት –የካዳሚክ ትምህርት ምንም ያህል ቢቀጠቀጥ ብቻውን ሰብአዊነትና ሕዝብአዊነትን አያጎናጽ ፍም ።
በጣም የሚያስገርመው አገር ቤት የጎሰኝነትና የእስልማና ሃይማኖት አክራሪ ያልነበሩት ወደ በብስል ሊበራልና ሶሻል ዲሞክራሲ ዕርዮት የሚተዳደሩትን አገሮች ሲሄዱ ብሄርተኝነትና እስልምናን ሲያከሩ ይታያሉ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን –ቋንቋዎች፣ባህሎች፣ልማዶች፣የፖለቲካና የሰብ አዊ መብቶች እኩል በተከበሩበት፣የስልጣን ክፍፍል (separation of power)ባለበት በዲሞክራሲያዊ መተክሎች (principles)በሚተዳደር በአንድ ሉዓላዊ ኢትዮጵያ ሥር ስለመኖርን ሲንሳ ለመቀበል በጣም የሚከ ብዳቸው ጽንፈኛ ብሄርተኞች አጋጥመውኛል።
“መሠረታዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶች በሰባአዊ መብትነታቸው በአሁን ግዜ የሰው ልጆች ሁሉ የጋራ ሃብትና ተገቢ ፍላጎቶች ናቸው ተብለው ይታመንባቸዋል ። ……በሌላ አነጋገር በአሁን ግዜ ብሄርተኝነትም ሆነ ጎሰኝነት ተገቢነት የሚኖረው የጋራ ስብእናችንን በመቀበል እንጂ ይህንኑ በሚጻረር መንገድ ሊሆን አይችልም” (ዴቪድ ቢታም እና ኬቭን ቦይል ፣ ከዲሞክራሲ ጋር እንተዋወቅ በተሰኘ መጻፋቸው ፣1995)።
ነገር ግን ከአንዳንድ የኦነግ አባላት ፉከራ እንደተረዳሁት የአሁኑ የኦነግና ተከታዮቹ የፖለቲ ቅኝትና አቋም ተወደደም ተጠላ ማለት ኢ–ዲሞክራቲክ በሆነ መልኩ ኢትዮጵያ በእነሱ ሥር መገዛት እንዳለባቸው ነው ። ለዚህ የሚያቀርቡት ምክንያት ‘ኢትዮጵያ አገራዊ ኅልውና አግኝቶ የኖረው በኦሮሞች ደም እንደሆነና ይህ ውጥንቅጡን የወጣውም ለውጥ የመጣው በቄሮች ብቻ ትግል እንደሆነ ፤ በመሆኑ ያልተሸራረፈ ሥልጣን እንደሚፈልጉ’ ነው እንድምታቸው ።
ለ(ስብዕናን፣እኩልነትን፣ዲሞክራሲን፣አብሮነትን፣ወድማማችነትን፣አንድነትን) ወዘተርፈ መርሆች–አእምሯቸውን አልገባው አለ፣ ጆሮዋቸውም አልሰማ አለ ። ለእነዚህ ተቃራኒዮች ግን አእምሯቸውም፣ ጆሮዋቸውም ክፍት ነው ።
ለዚህ ቁልፍ ምክንያት ድንቁርና ነው ። “We are barred from ultimate knowledge,from ultimate explanation…..If we wish to progress beyond, we have to embrace a different concept of “understanding” from that of rational explanation” (physicist Paul Davis, in his The Mind of God book) ከመጠቀ እውቀት፣ከመጠቀ ገለጻ/አስረድኦት ተሸብበናል/ታጥረናል። ካለንበት ወደ ከፍ ያለ እውቀት መሻሻል የምንመኝ/የምንፈልግ ከሆነ፣ ለመማር ወይም ነገሮችን ለመረዳት እንጠቀምበት ከነበረው ምክንያታዊ ጽንሰ ሃሳብ የተለየአማራጭ መፈለግ ያስፈልገናል/ይኖርብናል ማሉቱ ይመስለኛል።
ስለሆነም ዳውድ ኢብሳን፣ ጃዋር መሃመድን፣ ፕ/ፌሰር ኢስቂያስን፣በቀለገርባን፣ጸጋዬ አራርሳን እና ጭፍሮቻችውን የ(ስብዕና፣እኩልነት፣ ዲሞክራሲ ፣ አብሮነት፣ ወንድማማችነት ፣አንድነት) ወዘተርፈ መርሆችን/እሴትችን ትርጉም እንዲገባቸው ለየት ያለ የማስተማርያ ዘዴ ወይም ፍልስፍና መቀየስ ያስፈልገናል ማለት ነው ። ንቃተ ኅሊና–በጡጦ መግታት ይቻል ይሆን ? ስለስብዕናና መቻቻልን የሚያስተምሩ –የጋንዲን፣ የኪንግ ጁኒየር ማርቲንን፣የማንዴላን፣የቫካል ሃቫልን፣ የቡዳሃን ወዘተርፈ መጽሃፍት ሰብስበን ብንልክላቸው ፋይዳ ይኖረው ይሆን? እስቲ ሌላም ሌላም መላ በሉ ።
በሃገራችን በየአካባቢዩ የሚታየው የስላም መደፍረስ ከመንግሥት ቁጥጥር አቅም በላይ ሆኖ ሳይሆን መንግሥት ሆንብሎ የሚያደርገው ይመስላ።በሚቀጥሎ ዓመት ለሚደረገው አገራዊ ምርጫ ከኢህአደግ ጋር ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች፦
1.ያለገድብ በነፃ ተዘዋውረው ፖሊሲያቸውን (ቢመረጡ በምን ምን ሕዝብና አገር እንደሚጠቅሙ) እና ርዕዮታቸውን ምረጠኝ ለሚሉትን ሕዝብ እንዳያስረዱና ከሕዝብ ጋር እንዳይወያዩ እንቅፋት ለመፍጠር
2.በምርጫ ጣቤያዎች ሕዝብ ለተፎካካሪዮች የሚሰጠውን ድምጽ ታዛቢ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ለሚፈጠረው ሁከትና ማስፈራራት፤መንግሥት በአገ ራችን ካለው የፀጥታ መደፈረስ ጋር የተዛምዱ ችግሮች እንደሆኑ አድርጎ ለማቅረብ ።
3. ለኢህአድግ ተወዳዳሪዮች ለደኅንነታቸው ጥበቃ ስለሚደረግላቸው ያለፍርሃትና ያለገደብ ተንቀሳቅው ይምረጡኝን ዘመቻ ማድረግ ይችላሉ ። በመሆኑም ኢህአደግ እንደለመደው የፓርላማ ወንበሮች በመኖፖል ለመያዝ ከታቀዱ እቅዶች አንዱ ሳይሆን አይቀርም ።
4.አብዛኞቹ የሰላም መደፍረስ ያሉት በኦሮሚያ ክልል በመሆኑ የኦሮሞ የፖለቲካ ተፎካካሪዮች የመመረጥ ዕድል ያሰፋል። ስለሆነም የ‘ኦብኮ’ን መሪ ዶ/መረራም ጨምሮ ሁሉንም የኦሮም የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዮች የምርጫውን መራዘም ያልፈለጉት ።
መንግሥት በምርጫው ለሚሳተፉ የፖለቲካ ተፎካካሪዮች ሁሉ ለይም ረጠኝ ዘመቻ ሲንቀሳቀሱ ያለድሎ በእኩል ደኅንነታቸውን የሚያስጠብቁ ከሆነ የኔ ግምት (speculation) ውድቅ ይሆናል ።
ያም ሆነ ይህ– በዲሞክራሲያዊ የአስተዳደር ሥርዓት አንድ ሉዓላዊ ኢትዮጵያና አንድ ሉዓላዊ ሕዝብ እንዲኖሩን የምንታገል ሁሉ ጠንካራ የስነልቦና ዝግጅት ያስፈልገናል። ከእውነት ጋር በብርቱ ስነልቦናና በትግል ጽናት የታነፀ ሕዝብ ዘመናዊ ሮኬትና ምሳኤል አይበግሩትም ።