ከዓመታት በፊት የዚህን የእናት ጡት ነካሽ ምንደኛ የወያኔ/ኦነግ ቅጥረኛ ክህደት፣ ቅሰጣና አደገኛ አካሔድ ዘርዝሬ በማስቀመጥ ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ በተለይም ደግሞ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ያሉባቸው ገዳማትና አድባራት ይሄንን ተኩላ ከአጠገባቸው እንዳያስጠጉ አበክሬ አስጠንቅቄ ነበር፡፡

የፈራሁት አልቀረም ይሄ ተኩና መጻሕፍትን ቆነጻጽሎ ያልነበረን እንደነበረ፣ የነበረን እንዳልነበረ አድርጎ ታሪክን ለሚፈልገው ዕኩይ ዓላማ አምታትቶ በዐፄ ዳዊት (1374-1406..) ዘመን የተጻፈ ነው የሚለውን የአቡነ ቀውስጦስን ገድል ቆነጻጽሎና ቀስጦ ቀርቦላቹሃል!!!

ተኩላው በቀደም ለት (27,12,2011..) Deacon Danielkibret በሚለው የፌስቡክ አካውንቱ (የመጽሐፈገጽ መዝገቡ) ላይ የኦሮምያ ቤተ ክህነት፡ለትክክለኛ ጥያቄ የተሳሳተ መልስ!” በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ ለጥፎ ነበር፡፡ ይሄንን በሐሰተኛ መረጃ የታጨቀ ጽሑፍ በርካታ ድረ ገጾችም ተቀባብለው ለጥፈውታል፡፡ ተኩላው በዚህ ጽሑፉ ላይ የሚከተለውን ሐሰተኛ መረጃ ጠቅሶ አቅርቧል፦

“”….እኔ ባለኝ መረጃ በኦሮምኛ ቋንቋ በማስተማር ቀደምቶቹ አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግልና አቡነ አኖሬዎስ ናቸው፡፡ በአቡነ ቀውስጦስ ገድል ውስጥ አቡነ ቀውስጦስ ያስተማሯቸው የተለያዩ የኦሮሞ ጎሳዎች ተጠቅሰዋል፤ ያስተማሩባቸው ቦታዎች ሲጠቀስ አንዳንዶቹ የኦሮምኛ ስም ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህን ሕዝቦች ያስተማሯቸው በቋንቋቸው ነው፡፡ ገድለ አቡነ ቀውስጦስ በአንድ ቦታ ላይ ‹ዘሀለወት ደብር ወበል ስማ ሰገሌ ሰገሌ የምትባል ደብር ነበረች› ይላል፡፡ በሌላም ቦታ ‹ደብረ ሰገሌ› ይላታል (Gli Atta di Qawsetos, 240) ሰገሌ ኦሮምኛ ነው፡፡ ‹ድምጽ› ማለት ነው፡፡ ‹ግበር ሎቱ(ለገላውዴዎስ) መልዕልተ የይ፤ ወለቴዎድሮስ ላዕለ ደብረ መንዲዳ ለገላውዴዎስ በየይ ተራራ ላይ (ቤተ መቅደስ) ሥራ፤ ለቴዎድሮስ ደግሞ በመንዲዳ ተራራ ላይ› ይላል(ገጽ 119139)፤ መንዲዳ ኦሮምኛ ነው፡፡ ‹የዱር ቤት› እንደማለት ነው፡፡ ዛሬ ከደብረ ብርሃን ከተማ ወደ ጅሩ በሚወስደው መንገድ መንዲዳ የምትባል ከተማ አለች፡፡ ‹ወለፊቅጦርኒ በሀገረ ለሚ ዘትሰመይ ደብረ ዲባናው ፊቅጦርንም ደብረ ዲባናው በምትባል በለሚ ሀገር› ‹ለሚ›፣ በኦሮምኛ ‹ዜጋ› ማለት ነው፡፡ ‹ወይብሉ ርእዩ ሰብአ ገላን ወየይ የገላንና የየይ ሰዎችን ተመልከቱ አሉ›(ገጽ 121)፤ ገላን የኦሮሞ ጎሳ ስም ነው፡፡ ‹ወአጥመቆሙ በህየ ሰብአ የይ፣ ወመሐግል ወገላን፣ ወሰብአ ጋሞ ወወላሶ ወቀጨማ የየይን፣ የመሐግልንና የገላንን፣ የጋሞን፣ የወላሶ(ወሊሶ)ና የቀጨማን ሰዎች አጠመቃቸው›(ገጽ 137)፡፡ ወላሶ(ወሊሶ) ዛሬ በስሙ ከተማ የተሠራለት የኦሮሞ ማኅበረሰብ ስም ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በሸዋ ከወግዳ አጠገብ የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህን ሁሉ አቡነ ቀውስጦስ አስተምረዋል፡፡ በግራኝ ጊዜ ነው ብዙ ነገር የጠፋው፡፡ አቡነ አኖሬዎስም በባሌ አካባቢ ሲያስተምሩ ኦሮምኛን ይጠቀሙ እንደነበር መዛግብቱ ይነግሩናል፡፡ የተዳከመው ደግሞ በሁሉም አካባቢ ነው….!”” ብሏል፡፡

ተኩላው ይሄንን ሐሰተኛ መረጃ በአቡነ ቀውስጦስና በአቡነ አኖሬዎስ ስም አምታቶ ሲያቀርብ ይሄ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም፡፡ ይሄንን ሐሰተኛ መረጃ ከዚህ ቀደም ተጠቅሞበት እንደሆነ ብየ ሰርች ሳደርግ (ስፈትሽ) ከወራት በፊት ኦሮሞ በ16ኛው መቶ ክ/ዘ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሳይሆን ከመጀመሪያውም እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረ ነው!” ብሎ ሐሰተኛ ድምዳሜ ያስቀመጠበትን ሸዋ፡የጥንትና ዛሬ መገናኛ!” በሚል ርእስ በጻፈው በጣም ረጅም ጽሑፍ ላይ ይሄንኑ ሐሰተኛ ወይም የተጭበረበረ ቅሰጣውን እንደተጠቀመበት አገኘሁ፡፡ ልዩነቱ እዚያ ላይ የኦሮምኛ ቃላት ናቸው!” ብሎ የጠቀሳቸውን ጨንጌ፣ ጎርፎ፣ ሰኮሩ፣ ሠረቲ እዚህኛው ላይ አለመጥቀሱ ነው፡፡

ይሄ ተኩላው የሚለው ነገር ሐሰተኛና የተጭበረበረ መረጃ መሆኑን ለማሳየት ሦስት ነጥቦችን እጠቅሳለሁ፦

1. ኦሮሞዎች የግራኝ አሕመድን ወረራ ተተግነው ወይም ወረራው የፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው አሁን ላይ ሰፍረው የሚገኙበትን የሀገራችን ስፍራዎች በወረራና በመስፋፋት በመያዝ የሀገሩን፣ የወንዙን፣ የተራራውንስም ሁሉ እየቀየሩ የራሳቸው ከማድረጋቸው በፊት አንድም ሰነድ የትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ፣ ወንዝና ተራራ የኦሮምኛ ሥያሜ እንደነበረው የሚያረጋግጥ ከዚህ ዳንኤል ቀስጦ ወይም ቆነጻጽሎ ወይም አወናብዶ ካቀረበው ገድል በስተቀር ሌላ የሀገር ውስጥም ይሁን የውጭ ጸሐፍት ትተውልን ካለፉት የታሪክ መዛግብት ይሄን ተኩላው የሚለውን የሚደግፍ ወይም የሚገልጥ አንድም የሌለ መሆኑ ነው፡፡

የሀገር ውስጥ መዛግብትን ትተን ቅድመ ግራኝ ወረራ የነበረውን የሕዝብ አሰፋፈር፣ የቦታ ስሞችና ተያያዥ ጉዳዮችን በሰፊው ዘግበው ካለፉትና አዘውትረው ከሚጠቀሱት ከውጭ የታሪክ ጸሐፍት ሁለቱን ማለትም በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን (1500-1530..) ሀገሪቱን ከ1520-1527.. የጎበኘውን የፖርቹጋል መንግሥት መልእክተኛ ፍራንቼስኮ አልቫሬዝ በጉዞ ማስታወሻ መጽሐፉ እንደጻፈው እና ግራኝ አሕመድን ለማገዝ ከገባው የዓረብና የቱርክ ጦር ጋር የገባው ዓረቡ የግራኝ አሕመድ ዜና መዋዕል ፀሐፊ ዓረብ ፋቂህ ፋቱል አል ሐበሽ!” በሚለው መጽሐፉ እንደጻፈው የእነኝህን ሙሉ መረጃ ሰጭ ጸሐፍት መጻሕፍትን ብንመለከት እንኳንና ተኩላው ዳንኤል አጭበርብሮ ባቀረበው በዐፄ ዳዊት ዘመን (1365-1395..) ነበሩ በሚላቸው አቡነ ቀውስጦስ ዘመን (1374-1406..) እነኝህ ኦሮምኛ ሥያሜዎች ሊኖሩ ይቅርና እሱ ከሚለው ዘመን ከመቶ ዓመታት በኋላ እንኳ እነኝህ የኦሮምኛ ሥያሜዎች ብቻ ሳይሆኑ አንድም የኦሮምኛ ሥያሜና ኦሮሞ እንዳልነበረ እነኝህ ጸሐፍት ያረጋግጣሉ!!!

16ኛው መቶ ክ/ዘ በፊት የታሪክ መዛግብት ከኦሮሞ ጋር የተገናኘ ነገር የጻፉት ነገር ቢኖር ኦሮሞዎቹ ለከብት ዝርፊያና ጥቃት ለመፈጸም ከነበሩበት ከቤናዲር ሱማሌ እየተነሡ ሲገቡ በጦርነትም ተማርከው ይቀሩ ከነበሩትና በቤተመንግሥት አካባቢ ባለሟልነትን አግኝተው ሲያገለግሉ የነበሩ በታሪክ መዛግብት ስማቸው ተጠቅሶ ከሚገኙት ከሁለት ሦስት የኦሮሞ ተወላጆች በዐፄ ዐምደጽዮን (14ኛው መቶ ክ/) አዛዥ ጫላ፣ የግራኝ ወረራ ሊፈጸም አካባቢ በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን (16ኛው መቶ ክ/) የንጉሡ ተዋጊ ባለሟል ቱሉ በስተቀር ኦሮሞና ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ትውውቅ አልነበራቸውም!!!

2. ይሄንን ተኩላው ከአቡነ ቀውስጦስ ገድል ላይ አገኘሁት!” የሚለውን የኦሮምኛ ሥያሜዎች ናቸው!” የሚላቸውን ቃላት ልብ ብላቹህ ብታዩዋቸው ግእዝ ውስጥ በሌሉ ፊደል የተጻፉ ቀጨማ፣ ጨንጌ!” የተባሉ ሥያሜዎችን ታገኛላቹህ፡፡ ግእዝ ጨ የሚባልን ፊደል አያውቅም፡፡ ግእዝ እንደ ሸ፣ቸ፣ኘ፣ዠ፣ጀ፣ጨ፣ፐ ያሉ ኩሻዊ የአማርኛና የላቲን ድምፆች ያሉበት ቃላት ሲያጋጥመው ሸን በሰ፣ ቸን በተ፣ ኘን በነ፣ ዠን በዘ፣ ጀን በደ፣ ጨን በጠ፣ ፐን በጰ እየለወጠ ነው የሚጽፈው፡፡ ተኩላው ግን ይሄንን አታውቅምና ተጋለጪ ሲላት ቀጨማ፣ ጨንጌ!” የሚል የኦሮምኛ ሥያሜ ናቸው!” ያላቸውን ቃላት በጥንታዊ የግእዝ መጽሐፍ ላይ አስቀምጣ መረጃ አገኘሁ!” ብላ ልታታልለን፣ ልታምታታን፣ ልታወናብደን ትፈልጋለች፡፡ አልተሳካልሽም ሌቦ!!! ለማጭበርበርም እኮ ጭንቅላት ይፈልጋል፡፡ እንደ ዳንኤል ዓይነቱ ድፍረት ያገነነው ደደብ ፈጽሞ ሊያታልለን ወይም ሊያጭበረብረን አይችልም!!! ግእዝ የማይጠቀመውን ፊደል ያውም በራቀ ዘመን የተጻፈ ነው በተባለ መጽሐፍ ላይ ማስቀመጥ በቀላሉ ሊያስነቃ ወይም ሊያጋልጥ የሚችል የሚችል ቅጥፈት ወይም ቅሰጣ ነው፡፡ ተኩላው ይሄንን ማድረጓ አጋልጧታል ነው እያልኩ ያለሁት፡፡

3. አሁንም ይሄንኑ ተኩላው አቡነ ቀውስጦስና አቡነ አኖሬዎስ በኦሮምኛ መስበካቸው መዛግብቱ ዘግበዋል!” የሚለውን ነገር ልብ ብላቹህ ስትመለከቱ ወይም ስትመረምሩ ሐሰት መሆኑን የምትደርሱበት አንድ እውነት ወይም ሐቅ አለ፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ተብለው የሚጠሩት ብሔረሰብና ኦሮምኛ ተብሎ የሚጠራው ቋንቋቸው የጀርመኑ ሚሽነሪ የነበረው ዮሐን ክራፍ (Johann Ludwig Krapf) የሕይወት ዘመኑ እንደ ፈረንጅ አቆጣጠር (January 11, 1810 – November 26, 1881) የኖረው ኦሮሞዎችን በመያዝ ጀርመን በምሥራቅ አፍሪካ የቅኝ ግዛት እንዲኖራት አደርጋለሁ ብሎ ሲማስን የነበረ ጀርመናዊ የፕሮቴስታንት ሰባኪ በጊዜ ብዛት አሁን ኦሮሞ!” የሚሉትን ሥያሜያቸው ያደረጉትን ቃል ኦርማን!” በማለት ሰፍረው ያሉበትን የሀገራችንን ክፍልና በጊዜ ብዛት ኦሮሚያ!” ያሉትን ደግሞ ኦርማኒያ!” ብሎ ከመሠየሙ በፊት ቋንቋቸውም ሆነ የብሔረሰብ መጠሪያ ሥያሜያቸው በዚህ ሥያሜ አይታወቁም፡፡

ታዲያ ተኩላው አቡነ ቀውስጦስና አቡነ አኖሬዎስ በዚያ ዘመን በኦሮምኛ ሰብከዋል!” ሲል ኦሮምኛ የሚባል የቋንቋ ሥያሜ ሳይኖር እንዴት በኦሮምኛ መስበካቸው ተዘግቧል!” ሊል ቻለ??? ብላቹህ ብትጠይቁት መልስ አይኖረውም፡፡ ምናልባት ጋላና ጋልኛ የሚለውን ወደ ኦሮሞና ኦሮምኛ ወደሚል ቀይሬው ነው!” ሊል ይችል ይሆናል፡፡ ይሁንና ግን የቤተክርስቲያን መዛግብት ጋላ ወይም ጋላት (ጋሎች) ሲሉ ከእስልምና ተከታዮች (ከአሕዛብ) ውጭ ያሉትን ያላመኑ ያልተጠመቁና ያልሠለጠኑ አረማውያንን በሙሉ ለማለት እንጅ እንደሚመስለን አንድን ብሔረሰብ ለይተው ለመጥራት የሚጠቀሙበት መጠሪያ ሥያሜ አይደለም ጋላ ወይም ጋላት ሲሉ፡፡

ለምሳሌ ያህል ውዳሴና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ ላይ ዛሬ ሊብያ ተብላ በምትጠራው ሀገር ስለ ነበረው ሐዋርያ ተፍጻሜተ ሠማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲተርክ ሠማዕቱን አርዮስ በጋላ አንገቱን አስቆርጦ እንዳስገደለው ይተርካል፡፡ ተአምረ ማርያምም ግብጽ ሀገር የነበረችውን ደብረምጥማቅ ማርያም የተባለችውን ቤተክርስቲያን ጋሎች እንዳፈረሷት ይገልጻል፡፡ እንግዲህ መረዳት እንደምትችሉት መጻሕፍቱ እንዲህ ሲሉ ኢአማንያን ወይም አረማውያን ይሄንን አደረጉት ሲሉ እንጅ ሊብያ ውስጥ አርዮስ ተፍጻሜተ ሠማዕት ቅዱስ ጴጥሮስን ሲያስገድል በኦሮሞ ነው ያስገደለው፣ ግብጽ ውስጥ ደብረ ምጥማቅን ያፈረሷት ኦሮሞዎች ናቸው፣ ኦሮሞዎች ሊብያና ግብጽ አሉ!” ማለታቸው እንዳልሆነ ማንም ሊረዳው የሚችለው ጉዳይ ነው፡፡

በመሆኑም ተኩላው የጠቀሰው የአቡነ ቀውስጦስ ገድል የተለያዩ ኢአማንያን ነገዶችን በየቋንቋቸው እንዳስተማሯቸው ይገልጻል እንጅ ጋላ የሚለው ሥያሜ የአንድ ብሔረሰብ መጠሪያ ባልሆነበት ሁኔታ በልሳነ ጋላ ሰበኩ አስተማሩ!” ሊል አይችልም፡፡ በመሆኑም ተኩላው ጋልኛ የሚለውን ኦሮምኛ ወደ ሚል ለውጨው ነው ሊል አይችልም፡፡ ጋላ የአንድ ብሔረሰብ መጠሪያ አይደለምና፡፡ ታዲያ ይሄ ተኩላ ከየት አምጥቶ ነው እነ አቡነ ቀውስጦስን በዚያ ዘመን በኦሮምኛ ሰብከዋል!” ሊል የሚችለው??? ብላቹህ ብትጠይቁ ተራ የማጭበርበር ተግባር መሆኑን ብቻ ነው ልትረዱ የምትችሉት፡፡

እናም ወገኖቸ ሆይ! ከዓመታት በፊትም በእነኝህ ከታች ሊንካቸውን ባስቀመጥኩላቹህ ጽሑፎች ላይ፦

https://www.zehabesha.com/amharic/archives/39677

እና

https://www.satenaw.com/amharic/archives/5429

ላይ ይሄ ፀረ አማራ ተኩላ የአማራን ገናና ታሪክ ደብዛ ለማጥፋት ገድለ አቡነ ተክለሃይማኖትን እንዴት አድርጎ እንደቆነጻጸለ በማሳያነት በማቅረብ አበክሬ እንዳስጠነቀኳቹህና የወያኔ ቅጥረኛ መሆኑን እንደገለጥኩላቹህ ሁሉ ይሄው አሁን ደግሞ እንደለመደው የአቡነ ቀውስጦስንና የአቡነ አኖሬዎስን ገድል በዚህ መልኩ ቆነጻጽሎ በከፍተኛ ደረጃ ታሪካችንን እያሳከረ፣ እያምታታ፣ እያቃወሰ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሁንም በድጋሜ አበክሬ ማስጠንቀቅ እወዳለሁ!!! ይሄንን ምንደኛ ተኩላ የታሪክ ጠላት እንደጠላትነቱም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ!!!

ይሄ አጭበርባሪ ሌባ ሕይዎቱ በሙሉ በማጭበርበር የተሞላ ነው፡፡ ዲቁና እንደሌለው ወይም ዲያቆን እንዳልሆነና ጭራሽ እንዲያውም ባሕርዳር በልጅነቱ የአካል ጉዳተኛ ከሆነች ሰንበት ተማሪ የወለዳት ልጅ እንዳለችው ከሚያውቁት ሰዎች ሲነገርበት ሸምጥጦ እየካደ ሲያስተባብልና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት!” እያለ በመጽሐፎቹ ላይ ሳይቀር እራሱን እየጠራ ሲያጭበረብር ኖሮ ከወራት በፊት የጄቲቪ እንግዳ ሆኖ በቀረበበት ጊዜ ስለ ዲቁናው ሲጠየቅ አይ ሰንበት ት/ቤት ሳገለግል ሳለሁ ሰዉ ዲያቆን እየመሰልኩት ዲያቆን ይለኝ ነበር፡፡ ያ ተለምዶ ቀረና ሰዉ ዲያቆን ይለኛል እንጅ ዲያቆን አይደለሁም!” ብሎ ከተናዘዘ በኋላም ሳያፍር አሁንም በየስፍራው ዲያቆን!” እያለ እራሱን ያስጠራል፡፡

ይሄንን ያህል የሰውን ተውትና እግዚአብሔርን እንኳ ሳይፈራና ሳያፍር በሌለው ሥልጣነ ክህነት የሚነግድና የሚያጭበረብር ትንሽ ሰው ነው ዳንኤል ማለት፡፡ ይሄ ታዲያ እግዚአብሔርን ያላፈረና ያልፈራ ተራ አጭበርባሪ ማንን ያፍራል ይፈራልስ??? እንዴትስ ለእውነትና ለሕሊናው ይታመናል??? ለዚህም ነው በዚህ ደረጃ እየተዳፈረ ለርካሽ ጥቅሙ ሲል የሀገርንና የቤተክርስቲያንን ታሪክ እየናደ እየቆነጻጸለ የሚገኘው!!! በዚህ እንዲቀጥል ግን ፈጽሞ ልንፈቅድለት አይገባም!!!

አመሰግናለሁ!

የቴሌግራም ቻነሌ

https://t.me/Yeamsalu

ኢሜይሌ

amsalugkidan@gmail.com

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው፡፡