Sunday, September 8, 2019

Source: https://www.gudayachn.com/2019/09/gudayachn-exclusive.html

ከጉባኤው ተሳታፊዎች በከፊል  ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ጳጉሜን 2/2011 ዓም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የቀድሞው አርበኞች ግንቦት 7 ዋና ፀሐፊ በኦስሎ፣ኖርዌይ የምስጋና ዝግጅት ተዘጋጅቶላቸው ነበር።በዝግጅቱ ላይ ቁጥሩ ከፍ ያለ የኖርዌይ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የቀድሞው አርበኞች ግንቦት 7 በኖርዌይ ለሚኖሩ እና ባለፉት ዓመታት ለዲሞክራሲ ትግል  አስተዋፅኦ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን  የምስክር ወረቀቱን የቀድሞው የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ሙሉዓለም እና አቶ አንዳርጋቸው ሰጥተዋል።

በዝግጅቱ ላይ አቶ አንዳርጋቸው በቅርቡ ያሳተሙትን ”ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” ቅፅ 1 መፅሐፍ ዙርያ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን ከመፅሐፉ ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ከመስጠታቸው በላይ በወቅታዊ ጉዳይ ዙርያ ያላቸውን ሃሳብ ለተሰብሳቢዎች አካፍለዋል።በእዚህ ዘገባ ላይ በተለይ በዋናነት  በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተናገሩትን እና በተወሰነ ደረጃ ደግሞ በመፅሐፋቸው ዙርያ ያነሷቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይደረጋል።

ወቅታዊ የኢትዮጵያን ሁኔታ በተመለከተ

አቶ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የገለጡበትን ዓረፍተ ነገር የኢትዮጵያ ጉዳይ ግልጥ ያልሆነ መንገድ ላይ ነው ያለው። የመፍረስ አደጋ ያንዣበባት ለመሆኑ ምክንያቱ ብሔርን መሰረት ያደረገው ህገ መንግስት ነው በሚሉ ዓረፍተ ነገሮች ሲሆን በመቀጠል ወቅታዊ የኢትዮጵያን ሁኔታን በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል።እነርሱም –

ለአቶ አንዳርጋቸው ስጦታ ሲበረከትላቸው ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር በተሰኘው መፅሐፍ በተመለከተየሚከተለውን ብለዋል –


በመጨረሻም አቶ አንዳርጋቸው በመርሃግብሩ ከመዘጋቱ በፊት የተዘጋጀላቸው ልዩ ስጦታ ተበርክቶላቸው የመርሃግብሩ ፍፃሜ ሆኗል።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com