September 10, 2019

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/96719

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዘመነ ዮዲት ጉዲትና ከግራኝ አህመድ ባልተናሰሰ መልኩ በዘመነ ወያኔ ብዙ መከራዎችን አሳልፋለች የችግሩን ብዛትና ጥልቀት ለመናገር ለቀባሪው አረዱት እንዳይሆንብኝ ነገሩ የኦሮሚያ ቤተክህነት ልንመሰርት ነው ሲኖዶሱ ፈቀደም አልፈቀደም ከመመስረት ወደ ኋላ ዝንፍ የሚያደርገን የለም በማለት ለሲኖዶሱ የአንድ ወር ጊዜ ሰተናል ብለው መግለጫ መስጠታቸው በእምነቱ ተከታዮች ላይ የፈጠረው ስሜት ይህ ነው ተብሎ አይገለጽም ላለፉት ዘመናት ወያኔ የፖለቲካውን አቅጣጯ ለማስቀየርና ትግሉን ወደፊት ለማስኬድ ሲል በየጊዜው የተለያዩ የቤት ስራዎችን ለህዝቡ ለተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሚዲያዎች ይሰጣል ዛሬም እንደተለመደው በዘመነ አብይ አስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ለመከፋፈል የተመሰረተ የሽብር ነጋሪት እያስጎሰመ በቤተክርስቲያን አባቶችና በእምነቱ ተከታዮች ምእመናን ላይ ተጽኖ እየፈጠረ ይገኛል።

በዘመነ አብይ የሁለት ዓመት እድሜ እንኳን ባልሞላው አስተዳደር ውስጥ ብዙ ቤተክርስቲያን ተቃጥለዋል ካህናት ታርደዋል ንዋየ ቅድሳት ተዘርፈዋል በእምነቱ ተከታዮች ላይ ድብደባ የመግደል ዛቻ እየተፈፀመባቸው ይገኛል ይህ ሁሉ ሲደረግ የአብይ አስተዳደር በቤተክርስቲያኗና በምእመናን ላይ የሚደርሰውን አደጋ አለመከላከሉና ጥበቃ እንዲደረግ አለማድረጉ ምን ይህል ለእምነቱ ያለውን ቦታ ያሳያል እንደው በአደባባይ እየወጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ሀገር ነች ክብራችን ነች እያሉ ማላዘኑ በሐይማኖትና በእምነቱ ተከታዮች ላይ መቀለድ ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እርሶ እንዳሉት ሀገር ብቻ ሳትሆን ከሀገር ትልቃለች ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ ሆና እንድትቀጥል ሀገሯንና ዳር ድንበሯ እንዲከበር ወራሪን ጠላት በመመከት ለስልጣኔ በር ከፋች በመሆን ለአፍሪካና ለዓለም ብርሃን የሆነች ናት እንዲሁም ክማይነጥፈው ዘላለማዊ በረከቷና ሰማያዊ ሕይወትን የምታሰጥ ስንዱ ቤተክርስቲያን ነች አሁንም ወደፊትም በዚሁ ስራዋ ትገፋበታለችም ትቀጥላለች ቤተክርስቲያንን ማቃጠል ካህናትን ማረድ ምእመናንን ማሳደድ ከንቱ የከንቱ ድካም ነው ምክንያቱም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም ነው የተመሰረተችው ሊቁ ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ስለ ቤተክርስቲያን እንዲህ ብሏል “ሰውን ብትታገልና ብትዋጋ ታሸንፈዋለህ፤ወይም ያሸንፍሃል፤ ቤተክርስቲያንን ግን ማሸነፍ አይቻልም፡፡ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ ትዋጋለች፤ተሸንፋም አታውቅም፡፡ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን ግን አልጎዳትም፡፡”

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰው ልጅን በዘሩ፣ በቋንቋው፣ በባሕሉ፣ እና በሀገሩ የተለያየ ማንነት ቢኖረውም ሁሉንም በአንድ አይን የምታይ ናት የሐይማኖቱ ማንነት ከሁሉ የበለጠ ማንነት ነው ብላ ታስተምራለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች ለሐይማኖታቸው ቀናዒና ሰማዕት የሚሆኑ ናቸው ታሪክም እንደሚነግረን ብፁ አቡነ ጴጥሮስ ለሀገራቸውና ለሐይማኖታቸው ሰማዕተ ጽድቅ ዘ ኢትዮጵያ የሆኑ አባት ናቸው ወደ ቀደመው ነገር እንመለስና መንግስት ወደ ፖለቲካ ስልጣን ለመውጣት ከሚጠቀምባቸው ተቋማት አንዱ ቤት እምነት ቦታዎች ነው ለዚህም ዋናዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነች በዚች ቤተክርስቲያን ውስጥ የእምነት ተከታዮች ብዛት በግምት ክ55–60ሚሊዮን የሚኖሩ ተከታዮች ይኖራሉ ይህን አሃዝ ከምን አግኝተኅው ነው ያስቀመጥከው ካላችሁኝ መነሻዬ በግምት ያልኩ ሲሆን ካነሰ ደምሩበት ከበዛም አባዙት ዳግማዊ ወያኔ ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘትና የድርጅቱን አላማ ለማራመድ ሲል ለዚህም በቂ ድጋፍ ለማግኘት ዋና ምርጫው አድርጎ የተነሳው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ነው ይኅውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሁለት ሲኖዶስ መከፈል ምክንያት በተደጋጋሚ ሲወያዩና ሲደራደሩ ነበር ይህ ውይይት ለመገባደድ የ አንድ ቀን ዕድሜ ስብሰባ ሲቀረው ዶክተር አብይ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ስማቸውንና ዝናቸውን ለማትረፍ በዚህ የእርቅ ጉባኤ ላይ የተገኙት እናም ምን ያህል በኦርቶዶክስ እምነት ዘንድ ቦታ ማግኘታቸው ያመለክታል እናም ያሰቡትና ያቀዱት ሃሳብ ተሳካላቸው ቅዱስ ሲኖዶሱን አንድ እንዲሆኑ ካደረጉት አንዱ ተብሎ የሳቸው ስም በሰፊው ይወራል ይዘከራል ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው የሁለቱ ሲኖዶስ አንድ የመሆን ጉዳይ በፈቃደ እግዚአብሔር የሆነ ብቻ ነው ዶክተር አብይ ለቤተክስቲያኗ በመቆርቆር በማስመሰል ለፖለቲካ ፍጆታ ተጠቀመባት እንጂ በሱ የስልጣን ጊዜ ቤተክርስቲያን አንዳችም ነገር አልተጠቀመችም እንደውም በዘመነ አብይ አንድነቷና ሰላሟ እንዲናጋ ዳርጓታል ስለ ዶክተር አብይ ሎሬት የትነበርሽ ስትናገር እንዲህ ብላ ነበር ዶክተር አብይ የመጽሀፍ ቅዱስ ጠቅሶ ቢነግራችሁ እንኳን አትመኑት ምክንያቱም ፖለቲከኛ ነው።

ወያኔ በኢትዮጵያዉያን ብሄረሰቦች መሃከል የዘራዉ የጥላቻ መርዝ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በኦሮሞና በአማራ ብሄረሰቦች መሃክል የመለያየትና የጎሪጥ እንዲተያዩ በማድረግ የጥላቻ ግንብ ገንብቶልናል ይህንን ግንብ በማጠናከር ዳግማዊ ወያኔ ኦሕዴድ የብሄር ተኮር ፖለቲካን የሚያራምድ የተረኝነት ስሜት ያደረባቸው የገዢውን መንግስት ሃሳብና ዓላማ የሚያራምዱ የኦሮሚያ ቤተክህነት እንዲመሰረት ጥያቄ ባነሱት ግለሰቦች ጀርባ ራሳቸውን የፖለቲካ ሊሂቃን ነን ብለው የሚያስቡና አክቲቪስት ነን ባዮች ጽንፈኞች ከሐይማኖት ቋንቋን የሚያስቀድሙ የወረደ አስተሳሰብ ያላቸው የተረኝነት ስሜት ያደረባቸው ፅንፈኛ አካሎች አሁን በማን አለብኝነት ተወጥሮና ገዝፎ የሚታየውን ከቋንቋ ማንነት አልፎ ወደ ዘርና ብሄር ተኮር እየሆነ ሀገራችንን አደጋ ውስጥ እየክተታት ይገኛል ይኅው ሰሞኑን እንዳየነው በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ሃሳብ (idology) ቋንቋን ብቻ ሳይሆን ብሔርን፥ሐይማኖትን፥ሀገርን፥ አንድነትን ያፈርሳል ለዚህም የኦሮሞና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም አክቲቪስት ነን ባዮች ለአማርኛ ቋንቋ ያላቸውን ጥላቻ በጉልህ ማሳየታቸው የሕብረተሰቡን መብት እኛ ብቻ እናውቅልሀለን ማለታቸው አምባገነናዊ ስርዓታቸውን አሳይተውናል ሐይማኖትን ከቋንቋና ከብሄር ማገናኛት በጣም ትልቅ ስህተት ነው ዳግማዊ ወያኔ የሚያራምደው ፖሊሲ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላይ ላለንበት ቀውስ ከቶናል የአማርኛ ቋንቋን እንደ ጠላት ሊታይበት የቻለበት ምክንያት ምንድን ነው ምክንያቱም የሀገሪቷን ሕዝብ በዚህ ቋንቋ ያስተሳሰረ ስለሆነ ነው።በተጨማሪ አማርኛን ቋንቋ የአማራ ቋንቋ ነው ብሎ ማሰቡ አሁን ላለንበት ለማሰተማርና የሐይማኖት አንድነትን ለመከፋፈል እንቅፋት እየሆነ እንዳለ ማሳያ ነው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሌሎች ሀገራት ልዩ የሚያደርጋት የራሷ የሆነ ፊደል ያላት እንዲሁም የራሷ ቁጥር ያላት ሀገር ናት ያለንን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት የራሳችን ነው ብሎ ከማውራትን የዘለለ ትርጉም የለውም።ቋንቋ መማር የሉዓላዊ ጉዳይ ነው ይህ ማለት እያንዳንዱ ቤተሰብ የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ነገር ለልጆቻቸው የሚወስኑት እነሱ ብቻ ናቸው እንጂ የክልል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም የፖለቲካ ሊህቃን ነን ባዮችና አክቲቪስት ነን ባዮች የሚፈቅዱልህም ሆነ የሚከለክሉህ አይደሉም በሌሎች ሰዎች ላይ ሕይወት መወሰን ፈጽመው አይችሉም!!!

ዳግማዊ ወያኔ ኦህዴዳዊ ተልኮ የሚያራምዱ የተረኝነት ስሜት ያደረባቸው የፖለቲካን ሊሂቃን አክቲቪስት ነን የሚሉ የኦሮም ፅንፈኞች የመሳሰሉት የሚያደርጉት ሀሰተኛ ንትርክና የተንሸዋረረ አመለካከታቸውን በተለያዩ አጋጣሚ በሚዲያ ቋንቋን መሰረት በማድረግ ህዝብንና ሐይማኖትን የመከፋፈል የጥላቻ ንግግራቸውን ሲያንቧርቁ ይገኛሉኢትዮጵያ የህዝቦች ሰባዊ መብት የሚከበርባት እኩልነት የተረጋገጠባት ሰላምና ብልጽግና የሰፈነባት ሃገር ሆና እንድትቀጥል ብቻ ነው የምንፈልገው ትላንት ህወሃት በህዝቡና በቤተክርስቲያን ላይ ያደረሰው በደል መቼም አንዘነጋውም ዛሬ ደግሞ የተረኝነት ስሜት ተፀናውቶአቸው በህዝብና በቤተክርስቲያን ላይ አደጋ እያደረሱ ይገኛሉ የትላንት ስርዓት ለመቃወም በአንድ ላይ እንደተነሳን የዛሬውን ስርዓት ዝም ብለን አናየውም እንታገለዋለን እንቃወመዋለን!!!