September 10, 2019

* የኦሮሚያ ፖሊስን “እወቅልኝ” ብሏል ጃዋር፣

* እስክንድር አሁንም ጥሪውን በመሰረዝ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው ማድረግ አለበት እንላለን፣

” ባልደራስ” የተባለው እንቅስቃሴ መሪ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይና ከአዲስ አበባ ጋር በተገናኘ መግለጫ ለመስጠት ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ “ይህ ሰውዬ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው። ልክ እንደ አባይ ጸሃዬ ነው። እነሱ ያወሩትን ወሬ ያወጣል። በር ዘግተው ያሴሩትን ሴራ እሱ አዳባባይ ያወጣል” ሲል በፌስቡክ ገጹ አስተያየት የሰጠው ጃዋር መሐመድ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን “እንዲያውቁት” ግልባጭ አድርጎላቸዋል። የጃዋር “አስተያየት” እንደ “ትእዛዝ” እንደሚቆጠር በብዙ ገጠመኞች እንደታየ ማስታወስ እንችላለን።

ሌሎችም ቢያነብቡት ይጠቅማል ብለው ካሰቡ ሼር ያድርጉ። ከጽሑፉ ውስጥ እርስዎ በግልዎ ሊያደርጉት የሚገባዎ ነገር ያለ ከመሰልዎ ከማድረግ ወደኋላ አይበሉ። ያነበቡትን በሚጠቅም መልክ ሥራ ላይ ማዋል ሃይማኖታዊም ሀገራዊም ግዴታ ነው።

ቀሲስ ኤፍሬም