September 15, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/146302
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ምዕመናን በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና ጣልቃ ገብነት ተቃወሙ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚደርሱትን በደሎች በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ናቸው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚደርሱትን በደሎች በመቃወም በጎንደር፣ በደሴ፣ በደብረታቦር፣ በመቄት፣ በእስቴ፣ ወረታና በሌሎችም ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል። ሰልፈኞቹ በቤተ ክርስትያን ላይ የሚደርሰውን ቃጠሎ፣ በንብረት ላይ የሚደርሰውን ውድመት፣ በአማኞች ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም ድምፃቸውን አሰምተዋል።
መንግስት ግዴታውን እንዲወጣ የጠየቁት ሰልፈኞቹ በቤተ ክርስትያንና በአማኞቹ ላይ በደል የሚያደርሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።
በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ የነበር ቢሆንም እንዲተላለፍ መደረጉ ይታወሳል።