September 16, 2019
Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/96832
ከሁነኛ የመረጃ ምንጭ ያገኘሁትን አንድ አስደንጋጭ ዜና ላካፍላችሁ ብቅ ብያለሁ፡፡
በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ፡፡ ይህ የ2012 አዲስ ዓመት የብልጽግናና የመተሳሰብ እንዲሆንልን ከወዲሁ ተመኘሁ፡፡
የሀገራችን ጠላቶች ብዙ ነገሮችን ሞክረው በቅርቡ ደግሞ በሃይማኖቱ በመግባት ኦርቶዶክስን ለመከፋፈል እያሤሩ እንደሆነ የአደባባይ ምሥጢር ሆኗል፡፡ ሁሉም ዘዴያው ተሞክሮ ሲከሽፍ ወይም እንዳሳቡትና ባሰቡት ፍጥነት ሳይጓዝ ሲቀር ስስ ብልት በሆነው ሃይማኖት ገብተዋል፡፡
ይቀናቸዋል ወይንስ አይቀናቸውም ወደፊት የሚታይ ነው፡፡
እጅግ የሚገርመው ግን ቀሲስ በላይ የተባሉትን የኦሮምያ ቤተ ክህነት በሚል ከጃዋር ጋር ትልቅ የግንጠላ ሥራ እየሠሩ ያሉትን ዓለማዊ ካህን የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ባለቤት የሆኑት አቶ ድንቁ የተባሉ ሰውዬ ቦሌ መንገድ በሚገኘው ካምፓሳቸው ዘመናዊ ቢሮና የቢሮ ፋሲሊቲ መስጠታቸው ነው፡፡ በዚያ ቢሮ ውስጥ ምን ሲጎነጎን እንደሚውልና እንደሚያድር ግልጽ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ የሚመለከታችሁ የሚዲያ አባላት ሁሉ እንድትከታተሉትና ቢቻል አቶ ድንቁንም አነጋግራችሁ እንድታሳዉቁን በዜግነቴ አደራ እላለሁ፡፡ አቶ ድንቁ በኢትዮጵያ ሕዝብ ልጆች የከበሩና ኢትዮጵያ አንቀባርራ የያዘቻቸው ቅልጥ ያሉ ሀብታም መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ያላቸው ሀብት አልበቃ ብሎ በዘረኝነት አረንቋ ተዘፍቀው ብዙ ያልተገቡ ድርጊቶችን እንደሚፈጽሙ እንሰማለን፡፡ አሁን ደግሞ ምን ይሁን ብለው ለይቶላቸው ወደዚህ የዘቀጠ ተግባር እንደወረዱ ፈጣሪ ይወቅ፡፡
የኢትዮጵያ መበታተን ለዩኒቨርስቲያቸው ዕድገት አንዳች አስተዋፅዖ እንደማያደርግ ሊያውቁ በተገባቸው ነበር፡፡ ይህ የዘረኝነት ልምሻ ደግሞ እንደርሳቸው ላለ በትምህርት ዘርፍ ለተሠማራ ዜጋ አይመጥንም፡፡ ትምህርት አእምሮን ካላሳደገ፣ ትምህርት የኅሊና ሚዛናዊነትን ካልጠበቀ መማርና ማስተማር ከንቱ ነው፡፡
እነዘሀበሻና ሌሎችም በዩቲዩብና በፌስቡክ የምትሣተፉ ሁሉ በዚህ ነጥብ ዙሪያ የበኩላችሁን የማጣራት ሥራ ሠርታችሁ እውነቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንድታሳውቁ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡ እኛው ያሳደግነው ዐውሬ እኛኑ ሊበላን አይገባምና በትምህርቱ ጥራት ረገድ ከሚፈጽመው ሸፍጥ በተጓዳኝ ኢትዮጵያን ለማውደም የሚጣጣር ይህን ዓይት ሀኃላፊነት የጎደለው ተቋም ካለ ሕዝባዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል፡፡ በአዲሱ ዓመትም ተማሪዎች ለከፍተኛ ትምህርት ሲመዘገቡ ይህን ነጥብ ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡