18 ሴፕቴምበር 2019

“ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም። ለማድረግ ስሞክር በስለት የመወጋት አይነት ህመም ነው የሚሰማኝ” የምትለው ሃና ቫን ዲ ፒር ”ቬጂኒስመስ” የተባለ የጤና እክል አለባት።

ይህ የጤና እክል ሃናን ብቻ ያጋጠመ ሳይሆን፤ በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ ሴቶች የጤና ችግር ነው።

ብዙ ያልተነገረለት ”ቬጂኒስመስ” በሴቶች ላይ የሚከሰት የጤና እክል ሲሆን፤ ማንኛውም ነገር ወደ ብልት ሊገባ ሲል በፍርሃት ምክንያት ብልት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች በድንጋጤ ሲኮማተሩ የሚፈጠር ነው።

ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል?

እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ”ደካማ ነው” ተባለ

ይህ የጤና እክል ያለባት ሴት ወሲብ ለመፈጸም ስትሞክር፤ የሰውነት አካሏ ከቁጥጥሯ ውጪ በመሆን የወንድ ብልት ውስጧ እንዳይገባ በመኮማተር ይከለክላል።

ይህ ብቻ ሳይሆን በማህጸን ምርመራ ጊዜ፣ አነስተኛ ቁሶች ወደ ብልት እንዳይገቡ ሊከላከልም ይችላል።

“ተመሳሳይ የጤና ችግር ካለባቸውን ሴቶች ጋር ተገናኝቼ ተወያይቼያለሁ። ሁላችንም አንድ አይነት ስሜት ነው የምንጋራው” ስትል ሃና ትናገራለች።

የጤና እክሉ ተጠቂ የሆኑ አንዳንድ ሴቶች ወሲብ መፈጸም ይቅርና በወር አበባ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውል ከጥጥ የተሠራ ሹል የንጽህና መጠበቂያ ለማስገባት እንደሚቸገሩ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

አሁን የ21 ዓመት ወጣት የሆነችው ሃና፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ለመፈጸም ስትሞክር የተሰማትን ሰሜት ታስታወሳለች። “ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈጸም ህመም እንዳለው አስብ ነበር። በዚያ ወቅት የተሰማኝ ስሜት ግን በቢላዋ የመወጋት አይነት ህመም ነው” በማለት ታስዳለች።

ተመሳሳይ የጤና እክል ያለባቸው ሴቶች “በስለታማ ነገር የመቆረጥ ወይም በመርፌ የመወጋት አይነት ሰሜት አለው” በማለት ወሲብ ለመፈጸም ሲሞክሩ የሚሰማቸውን ህመም ያጋራሉ።

ይህ የጤና አክል ያለባቸው ሴቶች ይህን መሰል ንጽህና መጠበቂያ መሳሪያ ወደ ብልት ውስጥ ለማስገባት ይቸገራሉ።
አጭር የምስል መግለጫ ይህ የጤና አክል ያለባቸው ሴቶች ይህን መሰል ንጽህና መጠበቂያ መሳሪያ ወደ ብልት ውስጥ ለማስገባት ይቸገራሉ።

የማህጸን ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ለይላ ፍሮድሻም፤ ስለዚህ የጤና እክል ሰዎች በግልጽ እንደማይወያዩ ያስረዳሉ።

“ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ መፈጸም ሊያስፈራ ይችላል። ሁላችንም ያለፍንበት ጭንቀት ነው። “ቬጂኒስመስ” ያለባቸው ሴቶች ግን ሁሌም ጭንቀቱ አለባቸው” ይላሉ ዶ/ር ለይላ።

ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል?

በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኘው አሚና ይህ የጤና እክል ሕይወቷን ባላሰበችው አቅጣጫ እንደቀየረው ትናገራለች።

“ቬጂኒስመስ ትዳሬን ነጥቆኛል። ልጅ መቼ ልውልድ? የሚለውን ምርጫዬን ወስዶብኛል”

”ቬጂኒስመስ” መቼ እና እንዴት ሊከሰት ይችላል?

“ቬጂኒስመስ” በማንኛው የዕድሜ ክልል ያለችን ሴት ሊያጋጥም ይችላል።

አንዲት ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ለመፈጸም ሞክራ ሳይሳካ ሲቀር ይህ የጤና እክል ሊያጋጥም ይችላል። ከወሊድ በኋላ ሊከሰት ይችላል። አንዲት ሴት ማርገዝ የምትችልበትን እድሜ ስታልፍ ሊያጋጥምም ይችላል።

ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን?

ዶ/ር ለይላ ይህም ብቻ ሳይሆን የአስተዳደግ ሁኔታ ለዚህ የጤና እክል ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ። ” ‘የሰርግሽ ዕለት ወሲብ ስትፈጽሚ ህመም ይኖራል’ ወይም ‘ድንግልናን ለማረጋገጥ ደም መታየት አለበት’ የሚሉ አመለካከቶች ለዚህ የጤና እክል ይዳርጋሉ” ይላሉ።

ባለሙያዎች ለዚህ የጤና እክል ስልጠናዎችን እና የወሲብ የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣሉ
አጭር የምስል መግለጫ
ባለሙያዎች ለዚህ የጤና እክል ስልጠናዎችን እና የወሲብ የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣሉ

“የተማርኩት በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ወሲብ መፈጸም ብዙ ደም መፍሰስ፣ እርግዝና ወይም በሽታ እንደሚያስከትል ነው የተነገረኝ” የምትለው ሃና ቫን ድ ፒር ነች።

ሌላዋ የዚህ የጤና እክል ተጠቂ ኢስለይ ሊን፤ “ቬጂኒስመስ” ለአእምሮ ጭንቀት ዳርጓታል። “የሕይወት አጋሬ ከእሱ ጋር ወሲብ መፈጸም እንደማያስደስተኝ ያስብ ይሆን? እያልኩ እጨነቃለሁ። እሱን እንደማልወደው እና ከእሱ ጋር ወሲብ መፈጸም እንደማልፈልግ ነው የሚያስበው” ትላለች።

ሃና እና አሚና ካጋጠማቸው የጤና እክል ለመዳን ስልጠናዎችን እና የወሲብ የምክር አገልግሎቶችን እየወሰዱ ይገኛሉ። አሚና “የወሲብ የምክር አገልግሎት እና ስልጠናዎችን መውሰድ ከጀመርኩ በኋላ በራሴ ላይ ለውጥ እየተመለከትኩ ነው” ትላለች።

ሃና በበኩሏ የህክምና ድጋፉ ለውጥ ቢያመጣላትም የምትፈልገውን አይነት ለውጥ ግን እስካሁን እንዳላየች ትናገራለች።

“በወሲብ እርካታን ማግኘት እሻለሁ። እዚያ ደረጃ እስክደርስ ድረስ ንጽህና መጠበቂያውን ወደ ውስጥ ለማስገባት በመሞከር እቆያለሁ” ትላለች።