2019-09-20
መንጋው ይምረረው፣ ይቆምጥጠው እንጂ አዲስ አበባዊ ማንነት አለ !!!
ቴዲ ፍቅሬ
እስክንድር፦ 6 ሚልየን ህዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የለውም ነው የምትለኝ?በቀለ ገርባ ፦ “የአዲስ አበባ ነዋሪ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የለውም ። ምክንያቱም የአዲስ አበባ ነዋሪ ብሄር ብሄረሰብ አይደለም ። ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያላቸው ብሄር ብሄረሰብ ብቻ ናቸው ። ” ..♦እስክንድር፡- ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንደምትጠይቁት ሁሉ ከሐረርና ከሌሎች ከተሞች ላይ ለምን አትጠይቁም?♦በቀለ ገርባ: እንን እንን ለውይይት የተገኘኸው አዲስ አበባን ወክለህ መሰለኝ አቶ እስክንድር ? .♦እስክንድር፡- የአዲስ አበባ ሕዝብ ‹‹የራሴን ዕድል በራሴ ልወስን›› የሚል ጥያቄ ቢያነሳ መልሱ ምንድን ነው?.♦በቀለ፡- ‹‹ምን እድል አለውና ነው የሚወስነው?››
–‘ ተወልጄ ያደኩባት ማንነቴን የቀረፅኩባት ከተማ … ማንንም በጎጥ ፣ በቆዳ ቀለም ፣ በኃይማኖት ፣ በባህልና በቋንቋ ለያይቼ ፣ ከፍ ዝቅ አድርጌ እንዳላይ ፣ ተካፍዬ እንድበላና ለሰው ሁሉ ክብር እንድሰጥ ፣ ለታላላቆቼ መታዘዝን ለታናናሾቼ ክብርን እንድሰጥ ያስተማረኝ ህዝብ… ጎረቤት ፣ መንደር ሰፈሩ እንደልጅ ስታጠፋ አርሞ ፣ ስታለማ አጎብዞ… ከሌለው ላይ ከገዛ ልጆቹ ያካፈለ ፣ ስትታረዝ ሊወድቅ አንድ ሃሙስ በቀረ ዛኒጋባው ያስጠለለና ያኖረ ፣ አብሮህ ጨፍሮ አብሮህ የሚያለቅስ ምስኪን የከተማ ህዝብ… ከምንም በላይ አገርና አገር ብቻ ለዚያውም ኢትዮጵያ ትቅደም ! ብሎ ያስተማረኝ ስልጡን የከተማ ህዝብ … የዚህ ሁሉ አስተሳሰብና የማንነት መቅረጫ መንገዶች የቀረፀኝን እኔን ” ማንነት የለውም” ሲል አፉን ከፍቶ የልቡን ክፋትና ጥልቅ ጥላቻውን በፊት ለፊት ተናግሮታል ። አየህ… ይሄ ሰውዬም ሆነ እሱን መሳይ መንጋዎቹ ፣ የቆመለት አላማ ተልዕኮና ግብ ፣ የቆመለትና ውክልና የሰጠው ድርጅት ፣ በተመሳሳይ መንገድ ላይ ያሉና በቅንጅት እየሰሩ ያሉት የሱን መሰል የጎጥ ድርጅቶችና መሪ ግለሰቦች የሚያስቡት ፣ የሚያቅዱት ፣ የሚተገብሩት የትኛውም አይነት አላማ ይኑር ፣ የትኛውንም አይነት ስትራቴጂ ይንደፉ ፣ የትኛውንም አይነት ግለሰብ ይሰይሙ ስድስት ሚሊዮን አዲስ አበቤ ማንነት የለውም ነው ። “ማንነት የለውም” … በአለም ውስጥ ለቁጥር እስኪታክት ድረስ የደረሱ ፣ እየደረሱ ያሉና ወደፊትም እንደ አደጋ ተጋርጦ ያለው “ማንነት የለውም” በሚል አደገኛና ህዝብ ፈጂ ጨካኝና ፋሺስታዊ አመለካከት መነሻ ሃሳብ ነው ። … ” ማንነት የለውም” ሲባል እዚህ ግባ የማይባል ፣ ከሰው በታች የወረደ “ሰውነት” ያለው ፣ ስትፈልግ ምታኖረው ካልሆነ የምትፈጀው ከተራ የመገልገያ ዕቃነት ያልዘለለ ጥቅም የሌለው ወዘተ ወዘተ ማለት ነው ። በቀለ ገርባ ዛሬ ” ማንነት የለህም” ሲልህ ከላይ እንዳየኸውና አንተም እንደምታውቀው ነገ ሊሆን ስለሚችለው በገደምዳሜ ሳይሆን በቀጥታ እየነገረህ ነው። ለዚህ አይነተኛ መፍትሄው ረስህን ከሚሆነው ነገር ጋር ማቆራኘትና ምን እየሆነ እንዳለ ልትከታተልና ልትነቃ ይገባል ፣ ዛሬ በጅምላ የተነገረህ እያደር በርህን አንኳኩቶ እንዳይገባ ከወገንህና ከህዝብህ ጋር ልትመክር ፣ ሃሳብ ልትካፈል ፣ ልትጠባበቅ ፣ ልትደራጅና መብትህ ለማስከበር ዛሬ ልትነቃና ልትያያዝ ይገባሃል ። … አቶ በቀለም ሆነ መሳይ መንጋዎቹ ሊያደርጉትና ሊተገብሩት የሚያስቡትን ነግረውሃል… በአጉል አጉል የዋህነተና አጉል ” ምናለበትና ምንም አያመጡም” መሃል ተሰንቅረህ አትወዝወዝ … ሚናህን ለይ !! መስመር አትቀላቅል !! ተደራጅ !! … የአዲስ አበባን ጉዳይ እየተከታተለና እያጋለጠ ያለውን “ባልደራስ” ውክልና አልተሰጠውም ፣ ማነው የሰጠው ፣ ሃሳቦቹ አይሰማሙኝም ፣ ለገንዘብ በለው ነው ፣ እስክንድር ችግር አለበት ምንትስ ምናምን እያልክ አትቀባጥር አትወሽክት !!… ሃሳቡና አካሄዱ ከተስማማህ ተቀላቀል ፣ ደግፍ !! የተሻለ ካለህ በራስህ ተንቀሳቀስና ለከተማህ ፣ ለህዝብህ ለቤተሰብህና ለራስህ ቁም !! … ይሄ ሁሉ አያገባኝም ፖለቲካና ምንትስ እያልክ ገሸሽ ማለት ከፈለክ ቢያንስ ዝም በል !! Filed in:Amharic