September 19, 2019


የጤና ለጣና  አውስትራሊያ – የዕምቦጭ አረም በጣና ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቅረፊያ ያግዝ ዘንድ ኢትዮጵያውያን – አውስትራሊያውያንን አስተባብሮ $33,536.56 ካሰባሰበ አንድ ዓመት ሊሞላው የአንድ ወር ፈሪ ላይ ይገኛል። ገንዘቡ አሁንም ድረስ ከአውስትራሊያ ባንክ ወጥቶ ለታለመለት ተግባር አልዋለም።

የጤና ለጣና አውስትራሊያ ሊቀመንበር – ዶ/ር አደራጀው ታክሎ፣ ጸሐፊ ዶ/ር ሱራፌል መላኩና ዐቃቤ ንዋይ ዶ/ር ሰሎሞን ዋስይሁን፤ ባለፉት 11 ወራት ጤና ለጣና አውስትራሊያ ስለከናወናቸው እንቅስቅሴዎቹ፣ ጥረቶቹና የወደፊት ትልሞቹ ያናገራሉ። የተሰባሰበው ገንዘብም ግብር ላይ እንዲውል ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።