September 21, 2019

አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን የመጤዎች ስብስብ ብሔር ስላልሆኑ የራሳቸውን ዕድል የመወሰን ህገመንግሥታዊ መብት እንደለሌላቸው አቶ በቀለ ገርባ ሲያውጁ እስክንድር ነጋ እንዲያውም ስታሊን የብሄሮች ፅንሰሀሳብ አባት ያስተማረውን የጋራ ስነልቡናዊ ኢትዮጶያዊ ማንነት ያላት አዺስ አበባ ከኦሮሞ ብሄር የተለየ መገለጫ መሆኑንና አዲስ አበባ ማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ያለው መብት እንዳለው ለ አዲስ አበባ ነዋሪዎች መብት የቆመው ባለ አደራ ምክርቤት ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ በማስረጃ ተምዋግትዋል።አቶ በቀለ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የብሄር መብታቸው ያለው ከመጡበት ብሄር ነው የሚል አቅዋማቸው መሬቱ የኦሮሞ ነበር በመሆኑም አሁን ያለው አሰፋፈር አናይም ቢያስፈልግ እንለዉጠዋለን የሚለው ኦሮሞ፣ብሄርተኞች የሚስማሙበት አቅዋም ነው።የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የመምረጥ የመመረጥ መብት ሁሉ በኦሮሞ ብሄር ፈቃድ መሆን አለበት ነው የሚሉት። ለዚህም ነው አዲስ አበባን የኦሮሞ ዋና ከተማ ለማድረግ እንሰራለን ብለው የሚያዉጁት።ስድስት ሚሊዮን የ አዲስ አበባ ነዋሪዎች የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብቱን እውን ለማድረግ ላለፉት 28 ዐመታት ያለፉት 2 ዐመታት በ ኦሮሞ ኢህአዴግ 26 ዐመታት በ ወያኔ ኢህአዴግ ሹመኞች በ አፓርታይድ መሰል አገዛዝ ሲፈናቀል የጎዳና ተዳዳሪ ለማኝ ተደርግዋል።በተረኝነት ስሜት ኦሮሞ ብሔርተኞች በነዋሪው ላይ የሚያደርጉትን ኢ ሰብዐዊ ድርጊት ግድያና ማፈናቀል የማያወግዙ ፓርቲዎችን እንዳይመረጡ የማድረግ ዘመቻ በፍጥነት መጀመር አለበት።የባለ አደራው ምክርቤት አመራርን በሀሰት ክስ ወህኒ የወረወረው ኦዴፓ ኢህአዴግም ሆነ ደቡብ አዴፓ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በነፃ መሰብሰብ መደራጀት መብታቸዉን በማፈን የ አዲስ አበባ ነዋሪዎች በድምፃቸው ወያኔ ኢህአዴግን እንደቀጡ የ ዐቢይ አህመድን ኢህአዴግ በመቅጣት የራሳቸውን መማክርትና ከንቲባ በ ዚህ ዐመት ምርጫ ህያው ማድረግ ይኖርባቸዋል።ብሄረ ዘ አዲስ አበባ በ 2012 ህያው ይሆናል !!!!አዲስ አበቤነት ኢትዮጵያዊነት አፍሪካዊነት ይለምልም !!!!!