አቶ በቀለ ገርባ ብልጥ ነው ለካ ባካቹህ? እስክንድር ባልጠበቀው ደረጃ ጠንክሮበት ስላገኘውና ከጅምሩ ደጋግሞ በጠረባ ስለጣለው በዚህ ከቀጠለም በዝረራ ተሸንፎ መውጣቱ እንደሆነ ስለገባው ክርክሩ ሥርዓት ያለውና በተረጋጋ መንገድ ነጥብ በነጥብ እየተነሣ እንዳይደረግ እሱ ሲናገር ትንፍሽ ሳይል ጸጥ ብሎ የሚያዳምጠውን እስክንድርን በተራው ሲናገር የማይረቡ ነገሮችን ደጋግሞ እያነሣ በመነትረክና ጨርሶ አላናግር በማለት ወደ ተራ ንትርክና ጭቅጭቅ አውርዶ አደናቁሮ በብልጠት በዝረራ ከመሸነፍ ተርፎ ለማምለጥ ቻለ!!! ይሄንን ዘዴውን እንደ ትልቅ ብልጠት ቆጥሬለታለሁ፡፡

ወይ አቶ በቀለ ገርባ!!! ወይ ፖለቲካው ገብቶትና ችሎ በሥነሥርዓቱ አይከራከር ወይ ደግሞ አልችልም ብሎ አርፎ አይቀመጥ ምን ይሻለዋል ግን??? አቶ በቀለ ብዙ የተሳሳቱ ነገሮችን ነው የተናገረው፡፡ ኧረ እንዲያውም አንድም ትክክል የሆነ ነገር አልተናገረም፡፡ ሁሉንም ላንሣ ብል ጽሑፌ የመጽሐፍ ያህል መርዘሙ ነውና ሁለት ነጥቦችን ብቻ ላንሣ፦

አቶ በቀለ ገርባ እራስን በራስ የማሥተዳደር መብት የተሰጠው ለብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ስለሆነና የአዲስ አበባ ሕዝብ ደግሞ የአንድ ብሔረሰብ ሕዝብ ስላልሆነ እራሱን በራሱ የማሥተዳደር መብት የለውም!” ብሏል፡፡

ይታያቹህ አቶ በቀለ ገርባን የሚያክል ፖለቲካ የገባኝ ነኝ፣ የተማርኩ ነኝ!” ባይ ሰው እራስን በራስ የማሥተዳደር መብት ማንም ሊነፍገው የማይችለው ዓለማቀፋዊ የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ መብት ድንጋጌ መሆኑን አለማወቁ ሲበዛ ነው የገረመኝ፡፡

ሲቀጥል ደግሞ የወያኔ ሕገመንግሥትም ቢሆን እራስን በራስ የማሥተዳደር መብትን (self administration) እና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን (self determination) የሰጠው ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች!” እንጅ ለብሔር ብሔረሰቦች ብቻ አይደለም!!!

ብሔሮች የሚባሉት ምኖች ናቸው? ብሔረሰቦች የሚባሉትስ እነማን ናቸው? ሕዝቦች የሚባሉትስ እነማን ናቸው?” የሚለውን ጥያቄ ይሄ የወያኔ ሕገመንግሥት የመለሰው ወይም ያብራራው ወይም የገለጸው አለመሆኑና የአቶ በቀለ ገርባ ንቃተ ሕሊናም ዘገምተኛ መሆኑ ነው አቶ በቀለ ገርባን እንዲሳሳት ያደረገው፡፡

ይሁንና የወያኔ ሕገመንግሥት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሎ ነጣጥሎ ጠርቷቸዋልና ብሔሮች ማለት ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማለት አለመሆኑን፣ ብሔረሰቦች ማለትም ብሔሮችና ሕዝቦች ማለት አለመሆኑን፣ ሕዝቦች ማለት ደግሞ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ማለት አለመሆኑንና የማይተካኩ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ግን ከበቀለ ገርባና ከቢጤዎቹ በስተቀር ማንም ሰው የሚገባው ይመስለኛል፡፡

የወያኔ ሕገመንግሥት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች!” ሲል የገለጻቸው እነማንን እንደሆነ ለይቶ ባይገልጽም የአንድ ከተማ ሕዝብ የከተማው ስም እየተጠቀሰ ከተማ ሕዝብ!” እየተባለ ይገለጻልና የወያኔ ሕገመንግሥት ሕዝብ ብሎ ከገለጸው የቡድን ስብስቦች ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ አንዱ መሆኑ የሚያጠራጥር ሊሆን አይችልም!!!

በመሆኑም ከዓለም አቀፉ እራስን በራስ የማሥተዳደር ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብትና ድንጋጌ በተጨማሪ በወያኔ ሕገመንግሥትም ከሔድን ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብም እራሱን በራሱ የማሥተዳደር መብት አለው ማለት ነው!!! የገረመኝ አቶ በቀለ ገርባ ይሄንን የወያኔንና የኦነግን ሕገመንግሥት ሲያነብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች!” የሚለው ቃል ሳይነጣጠል በብዙ ቦታዎች ላይ ሰፍሮ የተቀመጠ ቢሆንም ሕዝቦች የምትለዋን ነጥሎ ትቶ እራስን በራስ የማሥተዳደር መብት የተሰጠው ለብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ነው!” ማለቱ ነው፡፡

ሌላው ነጥብ ደግሞ አቶ በቀለ ገርባ ለውጡን ያመጣው ቄሮ ነው!” ብሏል፡፡ ቆይ እንጅ እኔ የምለው ግን እነ በቀለ ገርባ እኛ ነን ታግለን ለውጡን ያመጣነው!” የሚሉት ነገር ግን የምራቸውን ነው???

እነኝህ ሰዎች የምር እንዲህ ሲሉ በጣም ይገርሙኛል!!! አቶ በቀለ ገርባ፣ ጃዋር መሐመድና ሌሎችም እንዲህ የሚሉት የኦሮሞ ብሔርተኞች የማሰብ የማገናዘብ ችሎታቸው ምን ያህል የወረደ መሆኑን ከሚያሳዩ ነገሮች ውስጥ አንዱ ይሄ አባባላቸው ነው፡፡

እውነታው እነሱ የሚሉት አይደለም!!! ዲሞክራሲ በሰፈነባቸውና የሕዝብ ድምፅ በሚደመጥባቸው ሀገራት ነው እንጅ እኛ ባለንበት አንባገነናዊ አገዛዝ ዓይነት ሀገር የተቃውሞ ሰልፍ ብቻውን የሥርዓት ለውጥ አምጥቶ አያውቅም!!! ከተቃውሞ ሰለፍ ባለፈ ከቀበሌ እስከ ሚንስትር ያሉትን የአገዛዙን ሹመኞችና ባለሥልጣናትን የሚበላ ሙሉ ሕዝባዊ ዐመፅ ካልተደረገ በስተቀር!!!

ወያኔን ለውጥ!” ብሎ የውሸት ለውጥ ጨዋታ እንዲጫወት ወይም እንዲያመጣ ያስገደደው እነ አቶ በቀለ ገርባ እንደሚሉት የቄሮ የጎዳና ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ሳይሆን የፋኖ ፀረ ወያኔ የሕቡዕ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ነው!!!

ወያኔ እውነት ቢናገር አስደንግጦት ለውጥ ብሎ ይሄንን የለውጥ ጨዋታ እንዲጫዎት ያስገደደው ውስጥ ውስጡን በአርበኞች ግንባር አደራጅነት የአማራ ወጣቶች ወይም የፋኖ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ በአማራ እየተቀጣጠለና እየጠነከረ መሔድ ነው!!!

ይህ የፋኖ እንቅስቃሴ የጀመረው ደግሞ ቄሮ የጎዳና የተቃውሞ ሰልፍ ከመጀመሩ በፊት ነው፡፡ እነ ጀግናው አበበ ካሴ 2006.ም ጥር ወር ላይ ለጥምቀት በዓል ጎንደር የሚገኙትን የወያኔ ባለሥልጣናት እነ በረከት ስምኦንን ለበዓሉ ሲታደሙ እዛው ላይ በጥይት ረፍርፎ ለመግደል ሲንቀሳቀሱ በአጋጣሚ በተፈጠረች ስሕተት ምክንያት ተይዘው ለማዕከላዊ እስርና ሰቆቃ ሲዳረጉና ሰቆቃ (ቶርቸር) እየተፈጸመባቸው ሰንሰለታቸውን እንዲያጋልጡ ሲጠየቁ በአስደናቂ ጽናትና ቁርጠኝነት ግደሉን እንጅ ሰንሰለታችንን አናጋልጥም!” ብለው በሰቆቃ (ቶርቸር) ብዛት አካላቸው ፓራላይዝድ (ሽባ) እስኪሆን፣ ብልታቸው እስኪኮላሽ፣ የእጅና የእግር ጥፍራቸው እስኪነቃቀል፣ ገላቸው በኤሌክትሪክ እስኪቃጠልና ሌላም አሰቃቂ ቶርቸር ተፈጽሞባቸው መራራ ዋጋ ሲከፍሉና በጽናታቸው ወያኔን ሲያስደነግጡ ሲያሸብሩ ቄሮ ገና የጎዳና ሰልፉን አላሰበም ነበር እኔም ቄሮን ለጎዳና ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ያወጣውን ጽሑፍ አልጻፍኩትም ነበር!!!

የእነ አበበ ካሴ አንድ ምሳሌ ነው፡፡ ጎንደር ከተማ የዚህ ሕቡዕ እንቅስቃሴ አባል በመሆናቸው ተጠርጥረው እጅ እንዲሰጡ ሲጠየቁ እጅ አንሰጥም!” ብለው ያውም በሽጉጥ ሁለት ሦስቱን እየገደሉ የተሠው ቆራጥ ጀግና ወጣቶች ቁጥር ጥቂት አልነበረም፡፡ የዚህ የቆረጠ ሕቡዕ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ በገጠሩ ደግሞ ይበልጥ የተጠናከረና በርካታ ገበሬዎችን ያቀፈ ነበር!!!

ይሄ የፋኖ በእጅጉ የቆረጠና የጨከነ ሞትንም በእጅጉ የናቀ የትግል እንቅስቃሴ በአማራ ሕዝብ በተለይም በወጣቱና በገበሬው ስር እየሰደደ እየተቀጣጠለ መሔዱ ነው ወያኔን ሱሪውን ያስፈታውና አይ ይሄንን ትግል የሚያመክን የሚያከሽፍ አንድ ነገር ማድረግ ካልቻልኩ ሊያልቅልኝ ነው!” እንዲልና ለውጥ ብሎ እንዲኮምክ ያስገደደው እንጅ በፍጹም በፍጹም ባዶ እጁን ወጥቶ ጮሆ የሚመለሰው ቄሮ ጎዳና ላይ ወጥቶ መንጫጫቱ አይደለም!!!

ወያኔ ግን አማራ የልብ ልብ እንዲሰማው ፈጽሞ ስለማይፈልግ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ለውጥ የሚለውን ድራማ በቄሮ መንጫጫት ያመጣው ማስመሰሉ ነው እነ አቶ በቀለ ገርባን፣ እነ ጃዋር ሞሐመድንና መሰሎቻቸውን አሳስቶ በማስተበት ያልሆነን ነገር እንዲያምኑና እንዲናገሩ ያደረጋቸው!!!

እነኝህ ሰዎች ጭንቅላት ቢኖራቸውና ማሰብ ማገናዘብ ቢችሉ፣ ትግል ማለትም ምን ማለት እንደሆነ የሚረዱ ቢሆኑ ግን ወያኔ በራሱ ምክንያት ዋሽቶ ቢል እንኳ ተሸውደው ለውጡን ያመጣነው እኛ ነን፣ ቄሮ ነው!” ባላሉ ነበር!!!

እነ አቶ በቀለ ገርባ እንደሚሉት ለውጥ ለሚሉት ሐሰተኛ ለውጥ እንዲመጣ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በሰው ሞት ብዛት ከሆነ መለካት የሚፈልጉት በዚህም ቢሆን ከእኛ ጋር የሰማይና የመሬት ያህል እርቀት ነው ያለንና ይሄም አያስኬዳቸውም፡፡ እነሱ ቁጥሩን አጋንነው በትግላችን አምስት ሽህ ሰው ገብረናል!” ይላሉ፡፡ እኛ ግን ሳናጋንን አብዛኛው እንዲያውም ያለአበሳው በባዶ ጥርጣሬና አማራ በመሆኑ ብቻ እየታደነ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ወገኖቻችንን ገብረናል!!!

እናም እነ አቶ በቀለ ገርባ ይሄ የምትሉት ነገር ጠልቆ ማሰብ ማገናዘብ ማሰላሰል አለመቻላቹህን ነውና የሚያሳየው ለውጡን ያመጣነው እኛ ነን!” እያላቹህ ሐሰት የሆነን ነገር ዘወትር በማላዘን እራሳቹህን ግምት ውስጥ ባታስገቡ መልካም ነው ብየ እመክራለሁ!!!

ለነገሩ እናንተ ሆን ብላቹህ በፈጠራ ተረቶቻቹህ ኢፍትሐዊ ጥቅማቹህን ለማስከበር የምትማስኑ የሞራል ጉዳይና መልካም የግል ሰብእና ጉዳይ ቢጠበስ የማይሸታቹህ ወይም ግድ የማይሰጣቹህ፣ ኃላፊነት የሚባል ነገርም ጨርሶ የማይሰማቹህ እፍረተቢሶች በመሆናቹህ ይሄ ምክሬ ጠብ የሚልላቹህ አይመስለኝም!!!

ቀድሞ ነገር ከላይ እንዳልኩት ማሰብ ስለማትችሉ እንጅ እኔ ነኝ እኔ ነኝ!” አባብሎ የሚያጣላን ምንም ዓይነት ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም!!! ከተታለልንበት ድራማ በስተቀር፡፡ መስሏቹህ ነው እንጅ ወያኔ አጃጃላቹህ እንጅ ያገኛቹህት አንድም ነገር የለም!!! እርግጥ ነው ወያኔ ተረኛ የሆናቹህ እንዲመስላቹህ ያደረገው ነገር አለ፡፡ ይሄ ግን ዓላማውን ካሳካ በኋላ ከእጃቹህ ነጥቆ የሚወስደው እንጅ ከእጃቹህ ገብቶ የሚቀር አይደለም!!! ይሄንንም አሁን አሁን በጥቂቱም ቢሆን እየገባቹህ ነው፡፡

እናም አዎ ወያኔ ለማወናበድ ፈልጎ ለውጥ!” የሚባል ድራማ ሲተውንብን ነበር፡፡ እሱም ትወና መሆኑ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ከተነቃበትና ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌለ እንደማይኖርም ከተረጋገጠ ከራረመ!!! እናንተ ዘገምተኛ ስለሆናቹህና ፈጥናቹህ ስለማትረዱ ነው እንጅ!!!

ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ ለውጥ የተባለው ውሸት መሆኑ በተራው ሕዝብ እንኳ በታወቀበት ጊዜ እናንተ ግን ከተራው ሕዝብ አንሳቹህ በሌለ ለውጥ አሁንም ለውጡን ያመጣነው እኛ ነን!” እያላቹህ የምታላዝኑት!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

አመሰግናለሁ!

የቴሌግራም ቻነሌ

https://t.me/Yeamsalu

ኢሜይሌ

amsalugkidan@gmail.com

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው